፠ ቅቤ የዋጡና ቅቤ ያልዋጡ ካድሬዎች!!!
የገደል ማሜቶ!!!
– ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት–ኢኮኖሚ)
ሙሉጌታ ገብረህይወት፣ሴኮ ቱሬ ጌታቸውና አሌክስ ደ ዋል (They have Destroyed Tigray)
‹‹አልነገርኩሽም ወይ፣ በአጥር ተንጠልጥዬ፣
ውሻ በቀደደው፣ ጅብ ይገባል ብዬ!!!››
‹‹ትግራይን እያወደሟት ነው!ሙሉጌታ ገብረህይወት (ጫልቱ) ከትግራይ ተራሮች ላይ ሆኖ ተናገረ›› (1)
ይህ ዲጂታል ኦዲዬ ፋይል በኢንተርኔት የድምፅ ክምችት የተሰናዳው በዓለም ሠላም ፋውንዴሽን ድርጅት በኢትዮጵያ የትግራይ ጦርነትን በስልክ አነጋግሪኝ በቀጭኑ ሽቦ ከትግራይ ገጠራማዋ ሥፍራ ከሙሉጌታ ገብረህይወት በርሄ ጋር አሌክስ ደ ዋል በጀንዋሪ ሃያ ሰባት 2021 እኤአ ያደረገው ቆይታ ነው፡፡ ከምንጭ ድረ–ገጾቹ በመክፈት ቃለመጠይቁን እንድትሰሙትና ንግግራቸውን በፁሁፍ የቀረበውን ያንብቡት፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ሙሉጌታ የህወሓት አባል በመሆን በሽምቅ ተዋጊነት ከ1975 እስከ 1991 እኤአ ያገለገለ ሲሆን ፣ በኢህአዴግ ውስጥ በከፍተኛ ሥልጣን ከ1991 እስከ 2000 እኤአ የሠራ ቅቤ የዋጠ ፖለቲከኛ ነው፡፡ ለጥቆም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሠላምና የደህንነት ጥናት ኢንስቲቲውት (Institute for Peace and Security Studies) በመመሥረትና የአፍሪካ የሠላምና ደህንነት የጣና ከፍተኛ ፎረም እንዲቆቆም አስተዋፅኦ አበርክቶል፡፡ ሙሉጌታ ‹‹የድሮውን እናስተኛው ይረፍ›› (Laying the Past to Rest: The EPRDF and the Challenges of Ethiopian State-building) እንዲሁም በጋራ የፃፈው ብሔርተኛነትና እራስን በእራስ ማስተዳደር በአሁኖ ኢትዮጵያ “Nationalism and Self-Determination in Contemporary Ethiopia,”) የተባለ ፁሁፍ በጋራ አበርክቶል ይለናል ጎደኛው አሌክስ ደዋል፡፡ ሙሉጌታ በወርሃ ኖቨንበር መቐለ ነበር ጦርነቱ ሲካሄድ፣ ከመቐለ ከተማ ኮብልሎ ወደ ተራራዎቹ ሸሸ፡፡ ይህ የስልክ ግንኙነት ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር ስለ እሱ ስንሰማ፡፡
ሙሉጌታ፡– ‹‹ውጤቱ ምን እንደሚሆን ታውቃለህ? ቃል በቃል ለመግለፅ፣ ትግራይን እያወደሞት ነው!!! በህብረት የኤርትራ ህዝብ አርነት ግንባር፣ የኤርትራ መከላከያ ኃይል እና የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በጋራ ሆነው፡፡ የትግራይ መከላከያ ሠራዊት ለጦርነት አልተዘጋጀም ነበር ሆኖም የጠላትን ከፍተኛውን መከላከያ ሠራዊት ለመመከት ብሎም አጠፌታውን ለመመለስና ለማጥቃት ተሰናዳ፡፡››
‹‹በጠላት ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሩኛል፣ እንደ ተዓምር ነበር፡፡ ትግራይ ያላት መከላከያ 23 (battalions) የሻለቃ ጦር ብቻ ነበር፡፡ የኤርትራ መከላከያ ኃይል 42 (divisions) ክፍለ ጦር እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል 12 ክፍለ ጦር በትግራይ ጦርነት ተሳትፈው ነበር፡፡ ይህ አሃዝ አስር ሽህ የሚቆጠር የአማራን ልዩ ኃይል አይጨምርም፣ እንዲሁም የኦሮሚያ፣ የሶማሌ እና ሌሎች ልዩ ኃይሎችን አያካትትም፡፡ በሁለቱ መኃል ያለው የኃይል ሚዛን እኩል ያልሆነ ወይም ያልተስተካከለ ነበር፡፡ …. ቀጥሎም የኢምሬትስ ሰው ዓልባ ድሮውኖች (Drones) እየተምዘገዘጉ መጡ!!! የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ድሮውኖች ትግራይን ትጥቅ አስፈቱ!!! የኢምሬትቶች መግደል ጀመሩ፣ ድሮውኖች ታንኮቹን ገደሎቸው ቀጥሎም ድሮውኖች ቅርብ እርቀት የሚተኮሱ ድግን መትረየሶችን ደመሰሶቸው፣ ብሎም ድሮውኖች የነዳጅ ክምችቶችን አነጠፎቸው፣ ለጥቀውም ድሮውኖች የመሣሪያ ግምጃ ቤቶቹን አወደሞቸው፡፡ በተመሳሳይ ድሮውኖች እያነፈነፉ አነስተኛ መኪኖችን ማጋየት ጀመሩ፡፡ በአጠቃላይ የሰው አልባ ጢያራዎቹ ኢላማቸው የህወሓት መሪዎቹ ላይ ያነጣጠረ ነበር:: ይህ መደናገጥ ረብሻና ሥርዓት አልበኛነትን ነበር የፈጠረው ፡፡ የጦርነት ዝግጅቱ ዋና ድክመት ይሄ ነበር፡፡ ብዙ ህዝብ ከመቐለ ከተማ ወደ ተለያየ ገጠር ሥፍራ ተሰደደ፣ የትግራይ መከላከያ ሠራዊቱን እየተከተለ ህዝቡም አብሮ ተመመ፣ አንዳንዶቹ ቤተሰቦቻቸውንም ይዘው ነበር፡፡ ወያኔ ህወሓት በሁለት አጣብቂኝ ውስጥ ወደቅን ከከተማ ከነቤተሰባቸው የተሰደዱትን ሰዎች መጠበቅና መከላከል አለብን ወይስ መዋጋት አለብን ድርጅቱ መከላከልን በመምረጥ ስደተኛውን ህዝብ ሩቅ ሥፍራዎች ሄዶ እንዲቆይ ተደረገ፡፡ ቀጥሎም አንተም የሰማህው አሳዛኝ ዜና ተሰማ:: ››
‹‹ታውቃለህ፣ ትግራይን እያወደሟት ነው!!! ቃል በቃል ለመግለፅ፣ በጋራ ሆነው የኤርትራ ህዝብ አርነት ግንባር (ሻብያ)፣ የኤርትራ መከላከያ ኃይል እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል፡፡ በትግራይ ምድር በአለፈው ሠላሳ ዓመታት የተከማቸውን ኃብትና ንብረት እንዲያው በደፈናው ሁሉንም አውደመውታል፡፡ ትምህርት ቤቶችና ክሊኒኮች ተቃጥለዋል፣ እያንዳንዱን ቤት ዘርፈውታል፡፡ ወታደሮቹ በመቀጠልም የገበሬዎችን ምርቶች ዘረፉ፣ በሁሉም መንደሮች የሚገኝ ኃብትና ንብረት ተዘረፈ፣ ወደ ኤርትራ የትግራይ መንደሮቹን ከሚያቆርጠው ጥቁሩ አስፋልት መንገድ በስተቀር ሁሉም ተዘርፎል፡፡ ወታደሮቹ በየትኛውም መንደር እንደደረሱ፣ ያገኙትን ማንኛውንም ሰው ሁሉ ይገላሉ፡፡ ትላንትና አንድ ትንሽ መንደር ውስጥ ነበርኩኝ 21 ሰዎቸን ገድለዋል፣ ከነዚህ ውስጥ ሰባቱ የዛች መንደር ቄሶች ነበሩ፡፡ የትም ሲሄዱ እንደዛ ነው የሚያደርጉት፡፡ በትግራይ በአለፈው ሠላሳ ዓመታት የተከማቸውን ተፈጥሮዊና ሰው ሰራሽ ኃብትና ንብረት ሁሉንም አውደመውታል፡፡ ይሄ ወታደራዊ ኃይል ከመንደሩ ሲገባ፣ ማንኛውም ገበሬ ከቤቱ ሸሽቶ አይኖርም ነበር፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ምክንያት ሁሉም የትግራይ ገበሬዎች ተፈናቅለዋል፡፡››
‹‹ ጦርነቱ ትግራይን የማውደም ዘመቻ ብቻ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊትን የማውደም ዘመቻ ጭምር ነው፡፡ አሁን ኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የሌላት ሃገር ሆናለች፡፡ በእኛ ግምገማ መነሻ መሠረት የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት 85 በመቶ ቀንሶል፡፡ አብይ አስራሰባት በመቶ የሚሆነውን ኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ቀንሶታል ምክንያቱም 17 በመቶ የትግራይ ተወላጆች ናቸው፡፡ 17000 (አስራስባት ሽህ) የትግራይ ወታደሮች ከወታደራዊ ማዕረጋቸው ሥልጣን ተሸረዋል፣ በዴዴሳ የእስር ቤት ካንፕ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ወታደሮች ከፍተኛ ሚና በሃገሪቱ ሠራዊት ውስጥ ይጫወታሉ፣ መካከለኛ ደረጃ ሥልጣን ላይ ያሉት የሰለጠኑ ሙያተኞች ሲሆኑ በቴክኒሻንነት፣ በታንከኛነት፣ በማህንዲስነት ወዘተ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ነበሩ፡፡ ስልሳ በመቶ የሚሆነውን ኃይል አጥተዋል፡፡ የኤርትራን ኮማንደሮች ኃይል ይልካሉ፣ የሞርታል ጥይት አጉራሾች ናቸው፣ መጀመሪያ እነሱን ይልካሉ እነሱ ሲያልቁ፣ የእነሱን ወታደሮች ይልካሉ፡፡ ስለዚህ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት ትግራይን ለቆ ቢወጣ ኖሮ፣ ኢትዮጵያ ያለ መከላከያ ሠራዊት ኃይል በአሁኑ ጊዜ ተገኝ ነበር፡፡
››
‹‹የተቆረጠው የስልክ ንግግር እንደቀጠለ ሙሉጌታ የኤርትራ መከላከያ ኃይል ትግራይን ለቆ ቢወጣ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ውስጥ ለጥቂት ቀናት እንኳን መቆየት አይችልም ነበር፡፡…..
አሌክስ ደ ዋል፡– እስቲ ንገረኝ፣ ህዝቡ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል? መመገብ ትችላላችሁ? የህክምና አገልግሎቶች ታገኛላችሁ? ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ምንድናቸው?
ሙሉጌታ፡– እስከዚህም ነው፡፡ ታውቃለህ በሃገሪቱ የአንበጣ ወረራ ተከስቶ ነበር፣ ምርት አልተሰበሰበም ነበር በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም ተቆረጠ፡፡ ይሄ ቀውስ በመጀመሪያ የተከሠተው የምርት መሰብሰቢያ ጊዜ ላይ ነበር፣ በተለይ የኤርትራ መከላከያ ኃይል ሆን ብለው ምድሩ ላይ እንደደረሱ፣ እህሉን ማሳው ላይ ያለውን ያቃጥሉ ጀመር፣ አሊያም ምርት ከመሰብስቡ በፊት ያለውን ስላጋዩት የምርት ሊቀንስ ችሎል፡፡ መንግስት ያደርገው የነበረው የእህል እርዳታ ስርጭት ተስተጎጉሏል፡፡ በጥቂቱ ነው ያለው፣ የምግብ፣ የህክምናና ሌሎቹም አቅርቦቶች ችግር ገጥሞታል፡፡ በኤርትራ ድንበር አካባቢ የሚገኙ ሩቅ ሥፍራዎች ያሉ ገበሬዎች በርሃብ ቸነፈር ተጠቅተዋል፡፡ በኤርትራ መከላከያ ሠራዊት እህላቸው በብዛት ተዘርፎል፡፡ ማንኛውም ምርት በጎተራቸው ያለውን ሁሉ ተወስዶባቸዋል፡፡ በቅርቡ በጣም ከፍተኛ የስብዓዊ ቀውስ ይከተላል፡፡››
አሌክስ ደ ዋል፡– የኢትዮጵያ መንግስት እንዳለው 85 በመቶ የሚሆነውን የረድኤት እህል ማከፋፈያ፣ ለህዝብ መድረሻ መግቢያ መንገዶች ተጠቅመን ለብዙኃኑ ህዝብ ማድረስ እንችላለን ብለዋል ይህ ትክክል ነው?
ሙሉጌታ፡– ለብዙኃኑ ህዝብ መንግሥት፣ የረድኤት ድርጅቶች እንደገመቱት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 4.5 ሚሊዮን ህዝብ ይገመታል፡፡ ይሄም ግምት በቂ አይደለም፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምን ያህል የረድኤት እህል ማከፋፈል ይቻላል? በትግራይ ኃይል በተያዘው ሥፍራዎች በኩል ምን ያህል የረድኤት እህል ማከፋፈል ይቻላል?
ሙሉጌታ፡– በከተማ ውስጥ የሚኖረው ህዝብና በዋናው የጎዳና መንገዶች የሚገኙት ብቻ፣ ምክንያቱም በሁሉም በኩል ጦርነት ስላለ ነው፡፡ እንደምታውቀው የተወሰነ ህዝብ በስተ ደቡብ ትግራይ በማይጨው ወይም አላማጣ በኩል ያለው የረድኤት እህል ማከፋፈል ይቻላል፡፡ ቀሪው ሥፍራዎች የረድኤት እህል ማከፋፈል አይቻልም፣ የሆነ ስምምነት መግባባት እስካልተደረስ ድረስ ፡፡ የስብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ለህዝቡ ምግብ እንዲደርሱ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመንግሥት በኩል ለሚቀርበው ማንኛውም ስብዓዊ ዕርዳታ ብዙኀኑ የትግራይ ህዝብ ከሚኖርበት ሥፍራ አኮያ አመቺ የሚሆን አይመስለኝም፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– ግን እኛ እስካሁን ምንም ነገር አልሰማንም? እኛ ስለ ህወሓት አመራሮች ምንም ነገር አልሰማንም?
ስለ ምን?
ሙሉጌታ፡– አውቃለሁ! ትልቁ ችግራችን እሱ ነው፡፡ የህወሓት አመራሩ ትልቅ መናጋት ደርሶበታል፡፡ ያም መሰረታዊ እንቅፋትና መሰናክል እንደሆነ እናውቃለን፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– ምክንያቱም …ዛሬ ደህና ትላንትም እንደሰማህው፣ የአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በመጀመሪያ ደረጃ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት እንዲወጣ ጠይቆል፣ ቀጥሎም የፖለቲካ ውሳኔ ውይይት እንዲደረግ አስፈላጊነቱ ታምኖበታል፡፡ አሁን በአላችሁበት ሁኔታ ውስጥ፣ እንዴት መነጋገር ይቻላል?
ሙሉጌታ፡– እንደማስበው በስልክ ከሌሎች ሰዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡ ግን ያልገባኝ ነገር ለምን እንደተሸኮረመሙ ለህዝብ እንደማይናገሩ፣ ህዝባዊ መረጃ እንደማይሰጡ አልገባኝም፡፡ የመገናኛ ችግር እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ቪ–ሳት (V-SATs) የሳተላይት መገናኛቸውን አጥተውታል፣ ቱራያ( Thurayas) የሳተላይት ስልክ ብቻ ነው ያላቸው እንዲሁም የሬዲዬ ትራንስሚተራቸውም የለም፡፡ የያዙት የቴሌቪዝን ጣቢያም ቆሚ ሠፈር ሳይገነባ አገልግሎት መስጠት አይችልም፡፡ የመገናኛ አገልግሎት ስርጭት ችግር እንዳለ አውቃለሁ፣ የእነሱ ችግር ከዛም የበለጠ ነው፡፡ ነግሬቸዋለሁ፣ ህዝቡም ነግሯቸዋል፣ ተስፋ እናደርጋለን፣ በቅርቡ ለህዝቡ ይከሰቱ ይሆናል፣ በግልፅ አደባባይ ይወጣሉ፡፡ በትግራይ ይህ ሁሉ ችግር ነው፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– እንዲሁም ምንም ነገር አልሰማን ስለ ፖለቲካ ጥያቄችሁ፡፡ ማለቴ አጀንዳችሁ ምንድነው? የፖለቲካ ፕሮግራማችሁ ምንድነው? በሁለታችሁ መኃል መነጋገር፣መደራደርና መስማማት ቢኖር ማለቴ ነው፡፡ የቱ ነው የመጀመሪያው ነጥብ? እኛ እስካሁን ድረስ፣ ምንም ነገር አናውቅ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፡፡
ሙሉጌታ፡– አዎ፣ አውቃለሁ፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡–የሆነ ሆኖ፣በየቀኑ የምንሰማው ዜና በጣማ አሳዛኝና ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ በስዩም፣ በዓባይና በአስመላሽ ሞት ብዙ ሰው ደንግጦል፡፡ እንደማስበው ዜናውን የሰሙ፣ ብዙ ሰዎችን በዓለም ዙሪያ የሚገኙትን አሳዝኖል፡፡ ታውቀው ይሆናል እኔ ለስዩም መታወሻ ትሆን ዘንድ የጻፍኩት በስፋት በኢንተርኔት ድረ–ገጾች ተሰራጭቶል፣ ግን እስካሁን ድረስ ስለአሟሟታቸው ሁኔታ ምንም ነገር አናውቅም፡፡ ስለ ሁኔታው የምታውቀው ነገር አለ?
ሙሉጌታ፡– በመንደር ውስጥ ነው ያገኞቸው፡፡ በመንደሮ ውስጥ ቆይታ አድርገው ነበር፣ ምንም ሠራዊት አብሮቸው አልነበረም፡፡ እነሱ በገለልተኛ ሥፍራ ላይ ነበሩ፡፡ ያዞቸውና ገደሎቸው፡፡ ኢፒኤኤፍ (ሻብያ) ነበር የገደላቸው፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– ስለዚህ ይህ ታሪክ በተኩስ መኃል ጦርነት ውስጥ ሞቱ ወዘተ የተባለው አይደለማ
ሙሉጌታ፡– አይደለም፣ አይደለም፣ አይደለም፡፡ እርባና የሌለው ወሬ ነው፡፡ ህወሓት እንደዛ ያለ ኃይል ይጠቀማሉ ብሎ ቢተነብይ ኖሮ፣ ትንሽ ቢገምት ብዙ ነገር ማድረግ ይችል ነበር፣ ለመተንበይ አይከብድም ነበር፡፡ ታውቃለህ ይሄ ጦርነት ፀረ ትግራይ ጦርነት ነው፡፡ ዐብይ ከኢሣያስ ጋር ሆነው ያቀነባበሩት ነው፡፡ ኢሣያስን ማንም እንደሚያውቀው መናቅ አይገባም፡፡ ኢሣያስን አጥፊ ኃይል በማስናዳትና በማደራጀት የተካነ ነው፡፡ ሰለዚህ በወታደራዊው ዘርፍ ያልተሰማሩ፣ በወታደራዊ ጥቃት በመከላከል ሙያ የማያገለግሉትን ሰዎች በሚመለከት ብዙ አማራጮች ነበሩ ወደ ሱዳን ወይም ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወር ይቻል ነበር፡፡ ብዙ ነገሮች ማድረግ ይቻል ነበር ግን ለዛ ምንም ዝግጅት አልነበረም፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– በዚህ በኩል ከፍተኛ የስሌት ስህተት የተፈጸመ ይመስላል፤ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ስትረቴጂ የለም፣ የመገናኛ ስትራቴጂ የለም፣ የደህንነት ስትራቴጂ አልተነደፈም፡፡
ሙሉጌታ፡– ምንም የለ፣ አዎ ምንም የለ፡፡ ጠንፍ አጥ ድህነት፣ ህዝቡ ለምኖቸው ነበር፡፡ ምንም ነገር አልነበራቸው፡፡ ህዝቡ እቅድ አውጥቶ እንዲተገብሩት ይህን ስሩ ይህን አድርጉ ብሎቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ትግራይን በቁመታቸው ልክ ሠፎት፣ድንክ አደረጎት፡፡ ሌላ ምን ማለት ይቻላል፡፡
በዚህ የህዝቡ ስሜት ተስፋ የመቁረጥ፣ ንዴትና ቁጣ መሆን አለበት
ሙሉጌታ፡–ቁጣ ፣ ንዴት፣ ከፍተኛ ሁሉን ጠል ንዴትና ቁጣ፡፡ አንድ አማራጭ ብቻ ነው ያላቸው መዋጋት ብቻ፡፡ ጦርነቱ ገና ተጀመረ፡፡ በከተማ አካባቢም ያለው ስሜት ተመሳሳይ ነው፣ በገጠሩ አካበቢ ያለው ቁጣ ይብሳል፡፡ የትም ብትሄድ ፣ ደርዘን ወጣቶች ታገኛለህ አደራጁን እያሉ ይጠይቁሃል፣ለመሰልጠንና ለመታጠቅ፡፡ ህወሓት ምንም ዓይነት የሰው ኃይል ችግር አይኖርበትም፣ መደራጀት ለሚፈልጉ ሁሉ፡፡ ስለዚህ ይህ ቁጣና ንዴት ያለአንዳች አማራጭ አስቀራቸው፣ አማራጫቸው ያ ብቻ ነው፣ ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ መከላከያ ኃይል ግልፅነት የሌለው ግንኙነት በመለማመጥና ማባበያ በመስጠት ላይም አልተመሠረተ አንዲሁም የህዝቡን ፍቃድና ቀልብ ለመግዛት አልቻሉም፣ ምንም ነገር ለማድረግ አልሞከሩም፣ በደፈናው ከዚህ ሁሉ ውጭ ናቸው፡፡ የዘር ማፅዳት በአዋጅ!!! በየትም ቦታ በተንቀሳቀሱበት ስፍራ፣ ማንኛውንም ሰው ሲያገኙ ይገሉታል፣ ይገሎታል፣ሽማግሌ፣ ህፃን፣ መጫት አይለዩም፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡–ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንሰማው ታሪክ በተለይ የኤርትራውያን ነው፡፡ ሁሉም ሰው የሚለው በተለይ ስለ ኤርትራዊያን መከላከያ ሠራዊት አይደል?
ሙሉጌታ፡– ሁሉም ሰው ነው! ነገር ግን መጥፎው ነገር የኤርትራ ኃይል ነው፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡–እስቲ ንገረን፣ ለቀሪው ዓለም ለማሰማት ትችላላችሁ ይሄ ጉዳይ ተሸፋፍኖ እንዳይቀር? ከዜናዎች የምትወስዱት ነገር አለ ከሬዲዬ፣ ከኢንተርኔት ድረ–ገፆች ወይም ከሌላ?
ሙሉጌታ፡– አዎ! አንድ አሮጌ ትራንዚስተር ሬዲዬ አለኝ ከአንድ መሊሽያ የገዛሁት፡፡(ሳቅ) ያ ነው ከዓለም ጋር የሚያገናኘኝ፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– ወደ ድሮው ጊዜ ተመልሳችሆላ፡፡
ሙሉጌታ፡– በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ አንዳንዴ የባትሪ ድንጋዩ ሰርቶ ያልቃል፣ ከዛም ከዓለም የዜና መረጃ ጋር ለሁለት ሦስት ቀናቶች፣ ግንኙነቴ ያከትማል በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡– ስለዚህ እኛ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው፣ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ስለ ጦርነቱ ለማሳወቅና ሚዲያና ሰው ለመሳብ፡፡ ምክንየቱም እንደምታውቀው የጦርነቱ ሁኔታ በድብቅ ለማከናወን ሙከራ አለ፡፡ ጦርነት እንዳልሆነ ለማስመሰል ይሞክራሉ፡፡ የአሜሪካ መንግስት ትራምፕ አስተዳደር በግብረአበርነት ተባብሮል፣ የአፍሪካ ህብረት ሙከራ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ሆኖል፣ እንደዛም ሆኖ አሁን ዜናው በመደመጥ ላይ ይገኛል፡፡
ሙሉጌታ፡– ሁሉም ነገር ደህና ነው፡፡ አንድ ነገር አለ የስብዓዊ እርዳታ ጣልቃገብነትን መግፋት አለባችሁ፡፡ አለበለዛም ጥብቅ ቁጥጥር መደረግ ያሻል፡፡ ‹‹የኤርትራ ኃይል እዚህ ይቆይ ይሆናል፡፡ በአለፈው ሳምንት ስብሰባ ነበራቸው፡፡ ከሠራዊቱ ከፍተኛ ኮማንደሮች በሰማንው መረጃ መሠረት በትግራይ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች ለምን ያህል ጊዜት እንደሚቆዩ ጥያቄ ነበር፡፡ የሰጡት ምላሽ ‹‹ትግራይን ለቀን ብንወጣ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ በትግራይ ውስጥ ለአንድ ሣምንት አይቆይም፡፡ ስለዚህ ትግራይን ለወያኔ (ህወሓት)በማስረከብ እንዲያገግም እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ እዚህ እንቆያለን፣ የብልፅግና ፓርቲ ከብዙ ወራቶች በኃላ ተጠናክሮ እስኪረከበን ድረስ፡፡›› ይህንን መልስ ነበር የሰጡት፡፡ ስለዚህ ይህ የስቴት ዲፓርትመንት ውሳኔ ዘግይቶል፣ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ካውንስል የኤርትራን ኃይል ከትግራይ እንዲወጣ ማድረግ አይችሉም፣ ቅድሚያ ለህዝብ የረድዔት እርዳታ እስካላቀረቡ ድረስ፣ ኮሶቮ እንዳደረጉት፣ ጥቂት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ነገሮችን ያሳልጣል፣ በትንሹ በምድሪቱ ላይ ሆነው ቁጥጥር ማድረግ ያሻል፡፡››
አሌክስ ደ ዋል፡–ኢምሬቶች እንዴት ናቸው? ኢሚሬቶችን ጠቅስሃቸው ነበር፣ የሰው ዓልባ ትንሽ አይሮፕላናቸው?
ሙሉጌታ፡– አዎ! አሁን ምንም ዓይነት ኢላማ የሚገባ ነገር የለንም፡፡ ታንኮች የሉንም፡፡ ምንም ነገር የለንም፣ በኢላማቸው ለዓይን የሚገባ ትልቅ ነገር የለንም፡፡ እኛ የሰው ልጆች ብቻ ነን በዙሪያችን የምንቀሳቀስ፡፡ ይሄ በመሆኑ ብቻ ነው ከድሮዎኖቹ ድብደባና ጥቃት የተረፍነው፡፡ አለበለዛ ድሮዎኖቹ በሙሉ ኃይላቸው እዚህ ይሆኑ ነበር፡፡ እነሱ ድሮዎኖቹን በኦፕሬተሮቻቸው በኩል ያሰማሮቸዋል፣ ድሮዎኖቹ ናቸው እኛን ትጥቅ ያስፈቱን፡፡
አሌክስ ደ ዋል፡–አንድ ነገር አለ እስካሁን ያልተጨበጠልኝ፣ እንዳልከኝ ኤርትራዊያን ይቆዩ አንድነገር እስኪያገኙ እንበል፣ የኤርትራ መንግሥት በዚህ ጦርነት ዓላማው ምንድነው አንተ እንዳየህው?
ሙሉጌታ፡– ምንም አያውቁም! መቼ ብልጽግና ፓርቲ በእግሮቹ ቆሞ ትግራይን መዋጋት እንደሚጀምር አያውቁም! እንደዛ ነው የሚሉት፡፡ እነሱ እንደሚሉት እዚህ የምንቆየው ብልፅግና ፓርቲ ጠንክሮ ወያኔን መዋጋት እስከሚጀምር ድረስ ነው፡፡ መቼ እንደሚሆን ግን አያውቁም፡፡ እንደተለመደው መቼም አይሆን፡፡ እኔ እንዳየሁት፣ እዚህ መሬት ላይ ሊሆን አይችልም፡፡ በቀሪው ኤርትሪያ ምድርም አይሆንም፣ ተያይተናል፣ በበርሃ እንተዋወቃለን፡፡ የትም ቦታ ተጋጥመናል፣ ሰምተህ ይሆናል ከሁለት ሳምንት በፊት በእደጋ ሃርቢ በተደረገ ጦርነት ሙሉ ብርጌድ ኃይል፣ የ33ኛው ግብረኃይል ድጋፍ ሰጭ ብርጌድ፣ ሜካናይዝድ ብርጌድ ነው፣ የድጋፍ ሰጭው ብርጌድም የሜካናይዝድ ድጋፍ ሰጭ ነው ለዲቪዚኑ፡፡ በ15 ደቂቃዎች ውስጥ አወደሞቸው፡፡ በአስራአምስት ደቂቃ ውስጥ ስድስት 107 ኤም ኤም ሮኬት ላውንቸሮች፣ስድስት 120ኤም ኤም፣ አራት 122 መትረየሶች ተማረኩ፣ ሰባት መኪኖች ተማረኩ፣ 167 ወታደሮች የጦር ምርኮኞች ሆኑ፣ በ15 ደቂቃ የጦርነት ኦፕሬሽን፡፡››
አሌክስ ደ ዋል፡– እነዚህ የጦር ምርኮኛች ምን ይደረጋሉ? የት ይቀመጣሉ? እንዴት ይጠበቃሉ?
ሙሉጌታ፡– ወደመጡበት ነው የምንመልሳቸው፡፡ ይዘናቸው መዞር አንችልም፡፡ የምናደርገው ነገር ቢኖር የፖለቲካ ትምህርት ለሁለትና ሦስት ቀናቶች ከሰጠናቸው በኃላ ወደ መቐለና አዲግራት እንመልሳቸዋለን፡፡ አንድ ኮነሬልና አንድ ሌተናንተ ኮነሬል መመለስ አልፈለጉም‹‹ይገሉናል መመለስ አንፈልግም አሉ›› እኛም የእኛ ወታደሮች አትሆኑም አልናቸው፣ መጠለያ አንሰጣችሁም፣ ነፃው ግዛታችን ውስጥ መኖር ትችላላችሁ ብለናቸው፣ በዚህ ሁኔታ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በአጠቃላይ በዚህ ሁኔታ ላይ እንገኛለን አሌክስ፡፡
‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹‹ተፈፀመ›››››››››››
አሌክስ ደዋልና ሙሉጌታ ሆን ብለው የደበቁት ምስጢር ውስጥ የትግራይን ጦርነት ማን ጀመረው የሚለውን በመሸሽ ያደረጉት የስልክ ውይይት ነው፡፡ የሁለቱ ውይይት ውስጥ ብዙ ቁምነገሮችና ወደፊት ወያኔ ለማድረግ የተዘጋጀውን ማወቅ ይቻላል፡፡ ይህንን ሚስጢር በግልፅ በቴሌቪዝን ለህዝብ ያሰማው ሴኩ ቱሬ ጌታቸው ‹‹የትግራይ ልዩ ኃይል በክልሉ ወታደራዊ ቤዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ፣ በሰሜን ዕዝ ላይ የ45 ደቂቃ መብረቃዊ ዘመቻ ማካሄድ ነበረብን ብሎል፡፡›› ምንጭ (/Sekoture Getachew admits TPLF attacked Northern Command/“We had to preemptively conduct the operation as lightning strike against Northern Co…) የሴኩ ቱሬን ንግግር ከዩቲዩቡ ይመልከቱ)
ሙሉጌታ በቃለ ምልልሱ ‹‹ ጦርነቱ ትግራይን የማውደም ዘመቻ ብቻ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊትን የማውደም ዘመቻ ጭምር ነው፡፡ አሁን ኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የሌላት ሃገር ሆናለች፡፡›› ብሎ ይመሠክራል፡፡ የኤርትራ ሠራዊት የገባው በዛ ምክንያት እንደሆነ በተዘዋዋሪ ይመሠክራል፡፡ ‹‹አልነገርኩሽም ወይ፣ በአጥር ተንጠልጥዬ፣ ውሻ በቀደደው፣ ጅብ ይገባል ብዬ!!!›› በእርግጥ ወንጀሉን ፈፅማችሁታል፡፡
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሽብርተኛነት መፈረጅ አለበት፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፤ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (Tigray People’s Liberation Front) በግራ ዘመም የማርክሲስት ሌኒኒስት የኮምኒስት ርዕዮት ተከታይነት በፌብሪዋሪ 18 ቀን 1975 እኤአ በኢትዮጵያ ምድር በደደቢት በርሃ ተመሠረተ፡፡ ህወሓት በሊቀመንበር መለስ ዜናዊ ሃያ ሰባት ዓመታት አገዛዝ ቆይታ በኃላ በህወሓት/ኢህአዴግ ተሸንፎ በኖቨምበር 24 ቀን 2018 እኤአ በህግ ሊታገደ ይገባል እንላለን፡፡ ህወሓት በኢህአዴግ ምርጫ ህወሓት ተሸንፎል፣ በብልፅግና ፓርቲም ምሥረታ ራሱን አግልሎል፡፡ በኖቨምበር 24 ቀን 2020 እኤአ በህግ ሊታገድ የሚያስችሉ የሃገር ክህደት ወንጀሎች በመፈጸም በህግ ተሠርዞል፡፡ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በስብዓዊ ጋሻነት አፈናና ጭቆና ከተያዘበት የባርነት ሠንሠለት ከአርባ ስድስት አመታት በኃላ ነፃ ወጥቷል፡፡ የብልፅግና ፓርቲ በትግራይ ለሚገኙ ታጣቂዎችና ወጣቶች የምህረት አዋጅ በማወጅ በሰላማዊ መንገድ ህይወታቸውን እንዲመሩ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የውች ጉዳይ ሚኒስትር የሃገሪቱን ውች ጉዳይ ፖሊሲ መመሪያ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ችግር ሊያስረዱ የሚችል ጥናታዊ ፊልም (ዶክመንተሪ) አሰርቶ ልምድ ባላችው የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ምሁራን ለዓለም ህብረተሰቡ እንዲያስረዱ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ቅቤ የዋጡ የህወሓት ካድሬዎች፣ ፍስሃ አስግዶም፣ ቴውድሮስ አዳሃኖም፣ብርሃነ ገብረክርስቶስ፣ አሌክስ ደዋል፣ማርቲን ፕላውስ፣ ዊልያም ዴቪድሰን፣ ወዘተ ባህር ማዶ የሚኖሩ ዲያስፖራዎች እውሸትን በመደጋገም እንደ የገደል ማሚቶ በተራቸው ይጮሃሉ፡፡ የኢትዮጵያን ዲፕሎማቶች ባህር ማዶ የሞኖሩ ምሁራንን በማወያየት በያሉበት ሃገር የትግራይን ሁኔታ ለዓለም አቀፍ ህብረተሰቡ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችና ጋዜጠኞች በነጻነት ገብተው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ መንግስት ስለኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ መኖር ያለውን ሁኔታ ለህዝብ መግለፅ ይጠበቅበታል እንላለን፡፡
‹‹መብረቃዊ ጥቃት!!!›› ኢትዮጵያን የፌዴራል መንግሥት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ምድር የተወሰነ ኃይልና የጦር መሣሪያ ወደ መኃል አገር ለማዘዋወር በሞከረ ጊዜ የሕወሓት ፖለቲከኞች ህዝቡን በማስተባበር አገዱ፡፡ የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ሹም አንቀበልም በማለት የህወሓት የትግራይ ክልል መንግሥት ተሸሚውን መለሰ፡፡ መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፣ የሃገር መሪ ይሾማል ይሻራል፣ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ዘላለም ይኖራል፡፡ የህዝቦችም ግንኙነት ዘወትር ህያው ነው፡፡ ኢትዮጵያን የፌዴራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የመከላከያ ሠራዊቱ መርሆዎች ‹‹የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኃን ያከናውናል፡፡›› ይላል አንቀጽ 87 ቁጥር 5፡፡ ወያኔ ያወጣውን ህገ መንግሥት በመሻር በጥቅምት 24 ቀን 2013ዓ/ም የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) የትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች መንግስት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረማርያም በትግራይ ውስጥ የሚገኘውን ኢትዮጵያን የፌዴራል መንግሥት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ከወያኔ የፖለቲካ ድርጅትን እንዲደግፍ በማስገደድ በሠራዊቱ ላይ የመሣሪያ ጥቃት በመፈፀም የአማራ ተወላጅ ወታደሮችን በመግደል፣ ሰባት ሽህ የሠራዊቱን አባላት በማገት፣ የሃገሪቱን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በመዝረፍ የተራ ወንበዴ ሥራ በመስራት ህገመንግሥቱን ጥንብ እርኩሱን አውጥተውታል፡፡ ወያኔ በዚህ ሥራው የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ጀነራል መኮንኖችን፣ ከፍተኛ የመስመር መኮንኖችን በመግደልና በማሰር የሃገር ክህደት ወንጀል ፈጽሞል፡፡ ወያኔ የሽብርተኛነት ወንጀል በመፈጸም ብዙ ወታደሮችን በመግደል፣ ሰባት ሽህ ወታደሮች በማገት፣ የእዙን ከባድ መሣሪያዎች በመዝረፍ ወንጀል ተጠያቂ ናቸው፡፡ ወያኔ በዘር ማጥፋት ወንጀል (ጆኖሳይድ) በተለይም በማይካድራ ከስድስት መቶ አማሮችን በአስቃቂ ሁኔታ በስለት በማረድና በጅምላ መቃብር በመቅበር ወንጀል ተጠያቂ ናቸው፡፡
የወያኔ ጁንታ በሃገር ክህደት በመንግሥት ግልበጣ ወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡ ኢፌዲሪ ሕገ–መንግሥት የክልል ሥልጣንና ተግባር ‹‹የክልሉን የፖሊስ ኃይል ያደራጃል ፣ይመራል፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ያስጠብቃል፡›› ይላል አንቀጽ 52፡፡ በህገ–መንግሥቱ መሠረት ክልሎች የፖሊስ ሠራዊት ኃይል ብቻ ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ የትግራይ ክልል 250000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ልዩ ሓይል፣ የአማራ ክልል 300000 (ሦስት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የኦሮሚያ ክልል 400000 (አራት መቶ ሽህ) ልዩ ኃይል፣ የሱማሌ ክልል 40000 (አርባ ሽህ) ፣ የጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሃረሪ፣ አፋር፣ ደቡብ (ሲዳማ ክልል አንድ ሽህ ልዩ ኃይል)፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት 250000(ሁለት መቶ ሃምሳ ሽህ) ይገመታል፡፡ ሁሉም ክልሎች የራሳቸው ሚሊሽያና ፖሊስ ኃይል በተጨማሪ አላቸው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ስህተት ለመማር የየክልሉን የፖሊስ ኃይል ማደራጀት መምራት ፣የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ማስጠበቅ ኃላፊነት ብቻ ሊኖራቸው ይገባል እንላለን፡፡ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ( ትህነግ) ህገመንግሥቱ በመጣስ ክልሎች ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አደረጃጀቶች እንዲኖራቸው አደረገ፣ ቀስ በቀስ እየተጠናከሩ በመሄድ በክልሎች መኃል ተጨማሪ ኃይል የማሰባሰብ ክልሎች እርስበእርሳቸው የጎሪጥ እንዲተያዩ አደረጋቸው፡፡ በትግራይ ክልል የሚገኘውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን በዘርና በብሔር አደረጃጀት ከፋፈለው የትግራይ ተወላጆች ሌሎችን የሰራዊቱ አባሎችን በመግደል፣ በማገትና መሳሪያ ዘርፈዋል፡፡ ወያኔ የሠራዊቱን ሃገራዊ ፍቅሩንና ብሄራዊ ክብሩን በማዋረድ ሠራዊቱን በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን በመቀስቀስና የዘር ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ሃገሪቱን እንደ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊቢያ ሊያፈርሳት ሞክሮ ነበር፡፡ ወያኔ የፖለቲካ ሴራ ዳግም የማዕከላዊ መንግሥት ስልጣን ለመጨበጥ የሰሜን እዝ ላይ ወንጀል ቢፈፅምም እንኳን ሃገር ለማፍረስ ሠራዊቱን ተባባሪ ማድረግ አልተቻለውም፡፡ ትግራይ ክልል የሚኖር የኢትዮጵያ ሠራዊት የወያኔ ተባባሪ ሳይሆን፣ የወያኔ መሪዎችን አስሮ ለፌዴራል መንግስት እንደሚያስረክባቸው ምንም ጥርጥር የለንም፡፡ የብልፅግና ፓርቲ በትግራይ ለሚገኙ ታጣቂዎች የምህረት አዋጅ በማወጅ በሰላማዊ ህይወታቸውን እንዲመሩ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የትግራይ ወጣቶች በሠላማዊ መንገድ ሌሎች አማራጭ መንገዶች እንዳሎቸው በውይይት ማሳመን አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ እንደነ ሙሉጌታ ቅቤ የዋጡ የትግራይ ካድሬዎች ያለ ደሞዝ፣ ያለ ቪ ኤይት፣ ያለ ቪላቤት፣ በሰባ አመታቸው መሬት ነክሰው ይታገላሉ፡፡ የወጣቶቹን ቁጣ ፣ ንዴት፣ ሁሉን ጠል ንዴትና ቁጣ ላይ ክብሪት ይጭራሉ፡፡ የትግራይ ወጣቶች አንድ አማራጭ ብቻ ነው ያላቸው መዋጋት ብቻ፡፡ጦርነቱ ገና ተጀመረ፡፡በከተማ አካባቢም ያለው ስሜት ተመሳሳይ ነው፣ በገጠሩ አካበቢ ያለው ቁጣ ይብሳል፡፡›› ይሎቸዋል፡፡ ኦዲፒ የብልጽግና ፓርቲ ቅቤ ያልዋጡ ካድሬዎች የትግራዩን ሳይጨርሱ ኦሮሞውን ከአማራ፣ አንዱን ከሌላው ያጋጫሉ፣ በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ኦሮሞ ያልሆነ ይውጣ እያሉ ያስፈራራሉ፣ በቤኒ ሻንጉል መተከል በአማራ ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል ይፈፅማሉ፣ በደቡብ ህዝብም በግጭት የታመሳል ወዘተ በተረኛነት የወያኔ ሥልጣን የእኛ ነው ብለው ሲሻሙ፣ መሬት ሲዘርፉ፣ ወርቅ ሲዘርፉ፣ ዳጎስ ያለ ደሞዝ፣ ቪ ኤይት፣ ቪላቤት፣ ሲሻሙ ይስተዋላሉ፡፡ ዳግም ወያኔ መጥቶ ጉድ እንዳይሰራቸው ከወዲሁ እንዲጠነቀቁ እናሳስባለን፡፡ የወያኔ ጁንታ በሃገር ክህደት በመንግሥት ግልበጣ ወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡ ወያኔ በህዝብ የተጠላው በአንድ ዘር ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ፖሊስ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ እያለ በክልሎች የዘር ፖለቲካ በመትከልና በከፋፍለህ ግዛው ብሂል በመጠቀም ለሃያ ሰባት አመታት ገዝቶ ወደቀ፡፡ ወታደራዊ ሳይንስ ዓለም አቀፋዊ ሙያ ሆኖ ለአንድ አገር ይቆማል እንጂ ለይቶ ለአንድ ዘር የመቆም ቃል ኪዳን ገብቶ አያውቅም ለዚህ ነው ‹‹ወታደር ሀገር እንጂ ብሔር የለውም!!!››የሚባለው፡፡
ምንጭ
“They Have Destroyed Tigray, Literally”: Mulugeta Gebrehiwot Speaks from the Mountains of Tigray/BY AFRICAN ARGUMENTS/JANUARY 29, 2021
Listen to the Interview/Interview Transcript/Because the quality of the recording is poor, we are also providing a transcript.27 January 2021 Call between Mulugeta Gebrehiwot and Alex de Waal [The first minute of the call was not recorded. Mulugeta started by describing the onset of the war.]
ፌብርዋሪ 6 ቀን 2021 ተፃፈ…..መሸ ደህና ደሩ!
ከፌስ ቡክ የተገኘ