ምሳሌያዊ አገላለፆች

ከአቶ ብስራት ኢብሳ ፌስ ቡክ የተወሰደ

ሁሉም አይነት ቋንቋዎች የየግላቸው የሆነ ምሳሌያዊ አገላለጽ እንዳለቸው ሁሉ፣ አንዳንዴ እረዥም ጊዜንና ወረቀትን አባክኖ ከሚተነተን አረፍተ-ነገር፣ ባጭሩ በምሳሌና በገደምዳሜ የሚነገሩ ወይም ፍሬ ሃሳቡን በተሻለና መንገድ የሚገልጹ ውብ የሆኑ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን ወደ ተከታዩ ትውልድ፣ በተለይ ውጪ ሀገር ለሚኖሩት ማስተማር ጠቃሚ ነው፡፡
አንዴ አግኝቼ ክምችቴ ውስጥ ሳስቀምጠው ምንጩን ስላላገኘሁት፣ የምታስታውሱት እንደምትነግሩኝ ተስፋ በማድረግ፣ ደክመው ላዘጋጁት በዚህ አጋአጣሚ ምስጋናዬን
አቀርባለሁ፡፡፡ (የስእል ቅንብሩ ቦኋላ የተጨመረ ነው)
መልካም ንባብ
የሀምሌ ብራ የባልቴት ወብራ
• የሀምሌን ውሀ ጥም የህዳርን ራብ የሚያውቅ ያውቀዋል
• የሀምሌ ጭቃ ቅቤ ለጋ
• የሀር ገመድ የበቅሎ ክበድ
• የሀብታም ልጅ ሲጫወት የድሀ ልጅ ይሞታል
• የሀብታም ልጅ ወደ ቦሌ የድሀ ልጅ ወደ ባሌ
• የሀጢአት ክፉ ጉቦ የበሽታ ክፉ ተስቦ
• የሀጥኡ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ
• የሁለት ሴቶች ባል ይሞታል ይበላል ሲባል
• የሁለት አገር ስደተኛ
• የሁለት እዳ ከፋይ
• የኋላ የኋላ አይቀርም ዱላ
• የህልም ሩጫ የጨለማ ፍጥጫ
• የሆነ አይመለስ እሳት አይጎረስ
• የሆድ ማበድ ያስቃል በግድ
• የሆድ ምቀኛ አፍ ነው
• የሆድ ምቀኛው አፍ ነው
• የሆድ ብልሀት የጋን መብራት
• የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል
• የለመነ መነመነ
• የለመነ ያገኛል የነገደ ያተርፋል
• የለመኑትን የማይረሳ የነገሩትን የማይረሳ
• የለመደ ለማኝ ቁርንጮዬን ቀማኝ
• የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማእድ
• የለመደ ልማድ ያሰድዳል ከማእድ
• የለመደ መደመደ
• የለመደ እጅ ጆሮ ግንድ ያስመታል
• የለመደ ፈረሰኛ ዛብ አይጨብጥ እርካብ አይረግጥ
• የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ
• የለማኝ ስልቻ ሲንከባለል ከለማኝ እጅ ይወድቃል
• የለማኝ ቅንጡ ይላል በወጥ አምጡ
• የለም ቀሪ ካለ ፈጣሪ
• የለበሰ የማንንም ጎረሰ
• የለበሱት ያልቃል የሰጡት ያጸድቃል
• የለጋስ ምስክሩ መስጠቱ
• የላሜ ልጅ ያውራዬ ውላጅ
• የላም መንጃ የሰማ መከንጃ የማር መቅጃ
• የላም ወተቱን የጌታ ከብቱን
• የላከ እንደ አፉ ያከከ እንደ እጁ አይሆንለትም
• የላይ ለምጡን የውስጥ እብጡን ባለቤቱ ያውቀዋል
• የላይ አልጋ የውስጥ ቀጋ
• የላይኛው ከንፈር ለክርክር የታችኛው ከንፈር ለምስክር
• የላጭ ልጅ ጸጉሩ ድሬድ ሆነ
• የላጭን ልጅ ቅማል በላት
• የላጭን ልጅ ቅማል በላው ያናጢን ልጅ ጅብ በላው
• የሌለው ልብም የለው
• የሌለው ልብ የለው ወዳጅ የለው
• የሌለው ሚስት የለው ወዳጅ የለው
• የሌሊት ግስገሳ የቀን ዘለሳ
• የሌላት እራት ደግሞ ምሳ አማራት
• የሌባ መኝታው አመድ መታሰሪያው ገመድ
• የሌባ ምኝታው ካመድ መታሰሪያው ገመድ
• የሌባ ሞኝ ከጎተራ ስር ይገኝ
• የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ
• የሌባ እጁን የፍየል ልጁን
• የሌባ ዋሻ የቀማኛ መሸሻ
• የሌባን ጠበቃ አደባልቀህ ውቃ
• የሌባን ጠበቃ ደርበህ ውቃ
• የልመና በሬ ትክክል አይሄድም
• የልመና እንጀራ ምንጊዜም ከልመና አያወጣም
• የልቡ ሳይደርስ እድሜ ይደርስ
• የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩትን ያህል ይስቃል
• የልቡን አድራጊ አይናደድም
• የልብህን ቢያናግሩህ አለ እዳ ቢለቁህ
• የልብህን ቢያናግሩህ አለ እዳ ቢሰዱህ
• የልብስ ቀላል ባለቤቱን ያቀላል
• የልጅ ልጅ እህል ፈጅ ኋላም ጅብ ያስፈጅ
• የልጅ ልጅ ጅብ አስፈጅ
• የልጅ መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ
• የልጅ ሞት የእግር እሳት
• የልጅ ስጋ በናቷ ቅቤ
• የልጅ ቀላቢ የአህያ ጋላቢ
• የልጅ ብልጥ እየቀደመ ይውጥ
• የልጅ ብልጥ የፊት የፊቱን
• የልጅ ብልጥ የሰጡትን
• የልጅ እናት አባይ ናት
• የልጅ ተሟጋች በፊት ሰማይ ያያል ኋላ መሬት
• የልጅ ተሟጋች ጠዋት ሰማይ ማታ ምድር ምድር ያይ
• የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ
• የልጅ ነገር ጥሬ በገል
• የልጅ ክፉ ዲቃላ የቤት ክፉ ሰቃላ የልብስ ክፉ ነጠላ
• የልጅ ክፋቱ አለመከማቸቱ
• የልጅ ጥፉ በስም ይደግፉ
• የልጅ ፍቅር የሴት ከንፈር እናትን አያስቀብር
• የልጅቷን ስጋ በእናቷ ቅቤ
• የልጅ ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ
• የሎሌ አልቃሽ የሴት ቀዳሽ
• የሎሌ አልቃሽ የሴት ቀዳሽ የቄስ አውደሽዳሽ
• የመልኳን ሲሏት የጠባዩዋን
• የመሬት ሴሰኛ ከመንገድ ዳር ይተኛ
• የመሬት እርጥብ እሸቱን ደረቅ ምርቱን
• የመስከረም ውስጡ በጋ ያረመኔ ልቡ ቀጋ
• የመቀናጆ በሬ ሲመሽ ወደ ቤቱ ይስባል
• የመበደሪያ አፍ መክፈያ አይሆንም
• የመተሩበት እጅ ይወዛል የተማከሩት ዳኛ ያግዛል
• የመታሰር ምልክቱ መጋዝ የመዳኘት ምልክቱ መያዝ
• የመነነ ከዱር የሞተ ከመቃብር
• የመነነ ከዱር የሞተ ከመቃብር አይወጣም
• የመነኩሴ ሎሌ የክረምት አሞሌ
• የመንማና የለው ገናና
• የመንታ እናት ተንጋላ ትሞት
• የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት
• የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት ለማንም ናት
• የመንዝ ልጅ እራያ ሂዶ ብልቱን አያወዛውዝም
• የመከሩበት ሞተ የወርወሩበት ተሳተ
• የመከራ ልጅ ሁል ጊዜ መከራ መስሎ ይታያል
• የመከራ ሌሊት አያልቅም
• የመከራ ሎሌ መከራ መስሎ ይታያል
• የመከራ ውዝፍ ያለበት ነጋዴ ከሚወረር አገር ይደርሳል
• የመከራን ጉድጓድ ሚዳቋ አትዘለውም
• የመኮንን ልጅ በከተማ የድሀ ልጅ በውድማ
• የመኮንን ልጅ አዘን ቢነግሩት አደን
• የመዝሙር መጀመሪያ ሀሌታ የዘፈን መጀመሪያ እስክስታ
• የመጠጡት ቅልጥም ከብርንዶ ይጥም
• የመጣ ሳይመጣ የውሃ ቦይ ጥረግ
• የመጣው ቢመጣ ወይ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ
• የመጣ ቢመጣ ከቤቴም አልወጣ
• የመጥረቢያ ልጅ መዝለፊያ
• የመጥረቢያ ልጅ ጥልቆ አይደል የሚባለው
• የሙሽራ እድሜ ቢያጥር የሰርጉ ድግስ ሆነ ለተዝካር
• የሙት ቀናተኛ ሚስቴን አደራ ይላል
• የሙት አልቃሹ የቁም ወራሹ
• የሙት አልቃሹ የቁም ወራሽ
• የሙት የለውም መብት
• የሚሆን ቢሆን ዝሆን ይበላ ቢሆን
• የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ሳልወጣሽ
• የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ
• የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ
• የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ የለውም
• የሚመጣውን እንድታውቅ ያለፈውን እወቅ
• የሚሞት ልጅ አንገቱ ረጅም ነው
• የሚሮጡበት ሜዳ የሚወጡበት ቀዳዳ
• የሚሰራ ምንም አያወራ
• የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባ
• የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባል
• የሚሰርቅ ሰው አደራ ቢያስቀምጡት እጅ ይነሳል
• የሚክድ ሰው አደራ ቢያስቀምጡት እጅ ይነሳል
• የሚሰጥም እሾህ ይጨብጣል
• የሚሰጥም ገለባ ይጨብጣል
• የሚስት መናኝ የእናት አገር ለማኝ
• የሚስት አንባሻ የጎረቤት ውሻ የደጅ እርሻ
• የሚስት አሳቢ የጥንድ በሬ ሳቢ ይስጥህ
• የሚስት ወይዘሮ እርሻው ጋራ ዞሮ
• የሚስት ዘመድ የማር አንገት
• የሚስት ዘመድ የማር እንጎቻ
• የሚሸሹበት አምባ ሲሸሽ ተገኘ
• የሚበላው ካጣ ይበላለት ያጣ
• የሚበላው ካጣ ይበላበት ያጣ
• የሚበጀውን ባለቤት ያውቃል
• የሚከርመውም የማይከርመውም ባንድነት ዝናብ ይለምናል
• የሚከርመውም የማይከርመውም አንድነት ዝናብ ይለምናል
• የሚካኤል ስለት ለገብርኤል ምኑ ነው
• የሚካኤል እለት ለገብርኤል ምኑ ነው
• የሚወዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ
• የሚወዱትን አቅፎ የሚጠሉትን ነቅፎ
• የሚወዱትን እቅፍ የሚጠሉትን ንቅፍ
• የሚወጋ ጦር ከእጅ ሲወጣ ያስታውቃል
• የሚውል ሆድ ማለዳ ያረግዳል
• የሚውል ሆድ ማለዳ ይርበዋል
• የሚወጡበት ገደል የሚንጠለጠሉበት ቅጠል
• የሚጠጉበት ገደል የሚንጠለጠሉበት ቅጠል
• የሚዛንን አባይ ለእሳት የዳኛን አባይ ለሰንሰለት
• የሚያልቅ እህል ከማያልቅ ዘመድ ያጣላል
• የሚያልፍ ቀን የማያልፈውን ስም ያወርሳል
• የሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስም ያወርሳል
• የሚያልፍ ነገር የማያልፍ ስም ይሰጣል
• የሚያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ
• የሚያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ አለች ልጅዋን ጎርፍ የወሰደባት
• የሚያልፍ ዝናም አይምታህ የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ
• የሚያልፍ ዝናም አይምታህ የሚያድግ ልጅ አይጥላህ
• የሚያማ ጠበኛ ዘወር ይበል ከኛ
• የሚያስፈራውን ለሚነግርህ የሚያስቀዝነውን ንገረው
• የሚያስፈሳውን ለሚነግርህ የሚያስቀዝነውን ንገረው
• የሚያብረቀርቅ ሁሉ ወርቅ አይደለም
• የሚያድግ ልጅ በእናቱ እጅ
• የሚያድግ ልጅ አትበድል የሚሞት ሽማግሌ አታቃልል
• የሚያድግ ልጅ አትበድል የሚሞት ሽማግሌ አታቅል
• የሚያድግ ልጅ አይጥላህ የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ
• የሚያድግ ልጅ አይጥላህ የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ
• የሚያድግ ዛፍ በቁጥቋጦው ያስታውቃል
• የሚያድግ ዛፍ ከቁጥቋጦው ያስታውቃል
• የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ
• የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ ያስታውቃል
• የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
• የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት
• የሚዳቋ ብዛት ለነአቶ ውሻ ሰርግ ነው
• የሚዳቋ ብዛት ለውሻ ሰርግ ነው
• የሚዳቋ ግርግርታ ለውሻ ሰርጉ ነው
• የሚዳቋ ግርግርታ ለውሻ ሰርግ ነው
• የሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት
• የሚጣፍጥ ምግብ ሲርብ የበሉት ነው
• የሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት ነው
• የሚፈልግ ያገኛል የሚተኛ ያልማል
• የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት
• የሚፈርስ ከተማ ነጋሪት ቢመታ አይሰማ
• የሚፈታ ከተማ አዋጅ ቢነግሩበት አይሰማ
• የማህበር አሽከር በልቶም አይጠገን ታሞም አይድን
• የማሚቴን እጅ ያላየ በእሳት ይጫወታል
• የማሽላ ዘር ከነአገዳው ቸር
• የማታ ማታ እውነት ይረታ
• የማታ ማታ ጭምት ይረታ
• የማታ ምግብ ለእንግዳ የጠዋት ምግብ ለአገዳ የጠዋት መጠጥ ለእዳ
• የማታ ሩጫ እንቅፋት ትርፉ
• የማታርፍ ጣት አር ጠንቁላ ወጣች
• የማታድግ ውርንጫ እናትዋን ትመራለች
• የማታድግ ጥጃ እናቷ ን ትመራለች
• የማታ አፍ ከጋን ይሰፋል
• የማታድግ ፍየል አምስት ትወልዳለች ልጆቹዋም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች
• የማታፍር ድመት ስሜ ገብረማሪያም ነው ትላለች
• የማትሄድ መበለት ዞራ ዞራ ትሰናበት
• የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ዘጠኙም ያልቁና እሷም ትሞታለች
• የማትሰማው ስድብ ከቀረርቶ ይቆጠራል
• የማነው እህል ያሰኝሃል ክምር የማነው ቤት ያሰኝሃል አጥር
• የማን እርሻ ብለህ እረስ የማን ሚስት ብለህ ውረስ
• የማን ገበሬ ሹሩባ ይሰራል
• የማን ዘር ጎመን ዘር
• የማያልፍለት ዘበኛ ከዋርካ ስር አይጠፋም
• የማያልፍ ነገር የለም ምሽትም በማለዳ ይተካል
• የማያመሽ ባል ቅንድብ ይስማል
• የማያስተኛ ነግረውህ ተኝተው ያድራሉ
• የማያስተኛ ነግረውት ሳይተኛ አደረ
• የማያበላ ቢገላምጥ አያስደነግጥ
• የማያበድር ደመና የማይመልስ ቀማኛ
• የማያበድር ገዳይ የማይመልስ አባይ
• የማያዋጣ ማህበር በጠጅ ይጀመራል
• የማያዋጣ ባል ቅንድብ ይስማል
• የማያውቁት ስድብ ከዘፈን ይቆጠራል
• የማያውቁት አገር አይናፍቅም
• የማያውቁትን መስራት ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብስ
• የማያውቁት ምን ያውቅ
• የማያዛልቅ ጸሎት ለቅስፈት
• የማያደርግ እንትን ከቤተክርስቲያን ይቆማል
• የማያድግ ልጅ ባራስ ቤቱ ዳንኪራ ይመታል
• የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል
• የማያድግ ልጅ ቅዘን ይበዛዋል የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
• የማያድግ ጥጃ ከበሬ ፊት ይነጫል
• የማያግዙ በፈር ያግዛሉ በከንፈር
• የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
• የማያፍር እንግዳ ባለቤቱን ይጋብዛል
• የማይሆን ነገር የተገላቢጦሽ ያችን ላንቺ ማናለሽ
• የማይመለስ ማር ሹመኛ ይበደረዋል
• የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር
• የማይመስል ነገር ለሴት አትንገር
• የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል
• የማይመቱት ልጅ ቢቆጡት ያለቅሳል
• የማይሰማ ሰው ልቤን አፈረሰው
• የማይሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
• የማይሰራ አይብላ የማይረዳ አይጥላ
• የማይስማሙ ዝንቦች ጥምብ ይልሳሉ የሚስማሙ ንቦች ማር ይጎርሳሉ
• የማይቀርልህን እንግዳ አጥበቀህ ሳመው
• የማይቀና ባይወለድ የማያስብ ባይነግድ
• የማይቀና ባይወለድ የማያስብ ባይነግድ ይሻላል
• የማይቀና ባይወልድ የማያስብ ባይነግድ
• የማይቀና ባይወልድ የማያስብ ባይነግድ ይሻላል
• የማይበሉት እህል ከአፈር እኩል ነው
• የማይበላ የለም የማይጠግብ ባሰ
• የማይተማመኑ ባልንጀሮች በየወንዙ ይማማላሉ
• የማይተማመኑ ባልንጀሮች እየወንዙ ይማማላሉ
• የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል
• የማይተች አይፍረድ የማያተርፍ አይነግድ
• የማይቻል ጠላት ስለ ወዳጅ ይቆጠራል
• የማይቻል ጠላት ከወዳጅ ይቆጠራል
• የማይችሉት ድንጋይ ሲያወጡት ደረት ሲያወርዱት ጉልበት ይመታል
• የማይከፍል ባለእዳ የሰጡትን ይቀበላል
• የማይነጋ መስሏት እቋቱ ላይ አራች
• የማይዘልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል
• የማይዘልቅ ማህበር አሜሪካ ይጀመራል
• የማይዘልቅ ባል ቅንድብ ይስማል
• የማይዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት
• የማይደርሱበትን አያኩም
• የማይድን በሽተኛ በጥር እሸት አምጡ ይላል
• የማይድን በሽተኛ በበጋ እሸት አምጡልኝ ይላል
• የማይድን በሽተኛ የማይመለስ ሀጢአተኛ
• የማይድን ባህታዊ ወተት አምጡ የማይድን ፉቅራ ጠላ ስጡ
• የማይገባ ሱሪ የማይበቅል ዘሪ
• የማይጠረጥር ቤቱን አያጥር
• የማይጣሉ መላእክት የማይታረቁ አጋንንት
• የማይጽፍ ደብተራ ክንፍ የሌለው አሞራ
• የማይፈርስ ምሽግ የለም
• የማይፈወስ ድዉይ የማይመለስ ጊጉይ
• የሜዳ ንስንሱን የቤት ጉስጉሱን
• የሜዳ ንስንሱን የቤት ጉዝጓዙን
• የምህረት ጎደሎ የባሪያ ወይዘሮ
• የምላስ ወለምታ ሪፈር የለውም
• የምላስ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
• የምላስ ጦር ቢታከም አይድንም
• የምመክተው ጋሻ የምጠጋበት ዋሻ
• የምሮጥበት ሜዳ የምወጣበት ቀዳዳ የለም
• የምስራች በቃሏ መላች
• የምስራች በቃሏ መጣች
• የምበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ
• የምበላው ሳጣ ማእቀብ ሊጣል ነው
• የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ሮጠ
• የምትለብሰው የላት ሻንጣ ቆለፈች
• የምትለብሰው የላት የምትከናነበው አማራት
• የምትመክተው ጋሻ የምትሰወርበት ዋሻ
• የምትሮጥበት ሜዳ የምትገባበት ቀዳዳ
• የምትበላው እህል ከማታየው መሬት ይበቅላል
• የምትታጠቀው የሌላት የምትከናነበው አማራት
• የምትነቃነቅ ግንድና የምትስቅ ሴት ልብ ሩቅ ነው
• የምትኮነን ነፍስ ጎረቤት ያውቃታል
• የምትጠላው ሰው ፈሱ እሆዱ ውስጥ ሳለ ይሸታል
• የምትጠላውን የምትወደውን ሰጥተህ ሸኘው
• የምትጠባ ጥጃ አትጮህም
• የምትጠባ ጥጃ አትጮህም የማይደርሱበትን አያኩም
• የምኞት ፈረስ ልጓም አይገታውም
• የምናውቃትን ክምር በድባብ ሸፈኑዋት
• የምድሩን በአፍ የሰማዩን በመጣፍ
• የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ
• የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ
• የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጫጫ
• የምጥ መድሀኒቱ አንድ እግር ማስቀደም ነው
• የሞላለት ድመት በሞዝቮልድ ይተኛል
• የሞላለት ድመት ሳንባ ያማርጣል
• የሞተ ልጅ አንገቱ ረጅም ነው
• የሞተ ቢሞት ያለን እንጫወት
• የሞተ አይከሰስ የፈስስ አይታፈስ
• የሞተው ባልሽ የገደለው ውሽማሽ
• የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ)
• የሞተ ያልነበረ ይመስላል ያለ የማይሞት ይመስላል
• የሞተን አትርሳ የወደቀን አንሳ
• የሞተውን አያ ይለዋል
• የሞት በደለኛ አያይዞ በዳኛ
• የሞኝ ለቅሶ መልሶ መልሶ
• የሞኝ ልቅሶ መልሶ መልሶ
• የሞኝ ልጅ ባባቱ ምን ይጫወታል አሉ
• የሞኝ ሚስት በምልክት
• የሞኝ ምስጋና የግንቦት ደመና
• የሞኝ ቄስ ጸሎት ዘወትር አቡነ ዘበሰማያት
• የሞኝ በትር ሆድ ይቀትር
• የሞኝ እጁን ሁለት ጊዜ እባብ ነከሰው አንድ ጊዜ ሳያይ ሁለተኛው ሲያሳይ
• የሞኝ ዘመድ ያፍራል
• የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ
• የሞኝን ጠላ በለው በአንኮላ
• የሞኝ ጀርባ ሲመታ ለአዋቂ ይስማማል
• የሞኝን ጥርስ ብርድ ፈጀው
• የሞኝ ገበሬ እርሻ በሰኔ
• የረጋ ወተት ምርጫ ይደገምለታል
• የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል
• የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች
• የራስህን አትበላ ገንዘብ የለህ የሰው አትበላ ዐመል የለህ
• የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች
• የራስዋ እያረረባት የስው ታማስላለች
• የሰማ ያውራ ያየ ይናገር
• የሰካራም ግጥም ሁልጊዜ ቅዳ ቅዳ
• የሰው አመሉ ዳውላ ሙሉ መቼ ያስታውቃል አብረው ካልዋሉ
• የሰው አገሩ ምግባሩ የከብት አገሩ ሳሩ
• የሰው አገር ዝናብና የእንጀራ አባት አይምታህ
• የሰው እንጂ የቃል ውሸት የለም
• የሰው ወርቅ አያደምቅ
• የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል
• የሴት ምራቋ ወፍራም ነው
• የሴትን ብልሀት የጉንዳንን ጉልበት ይስጥህ
• የሴት አገር ባልዋ
• የሴት አጭር ወይዘሮ የወንድ አጭር አውራ ዶሮ
• የሴት ጠጭና የአህያ ፈንጪ አያድርስ ነው
• የሴት ልባም ያህያ ቀንዳም
• የሴት ልቧ እንጂ ሆዷ አይመርጥም
• የሴት መልኳ ምንድር ነው እጅዋን ታጥባ እንኩ ስትል ነው
• የሴት መጠጥ ደፋር የወንድ አይን አፋር
• የሴት ምክር ማሰሪያው አሽከቴ
• የሴት ምክር የሾህ አጥር
• የሴት ሞቷ በማጀቷ
• የሴት ረዥም የማቅ ውዥምዥም እንብዛም አያስጎመጅም
• የሴት ስካር ያጭር ሰው ኩራት አይታይም
• የሴት ብቻዋን ሂያጅ የቄስ አርፋጅ ሁለቱም ነገር ወዳጅ
• የሴት አመዳም የአህያ ሆዳም
• የሴት አመዳም የአሮጌ ሆዳም
• የሴት አገሩዋ ባሏ
• የሴት አገሩዋ ባሏ ማደሪያዋ አመሏ
• የሴት እንግዳ የመርፌ ጎዳ
• የሴት ቀበጥ የበቅሎ መድን ለመሆን ገበያ ትወጣለች
• የሴት ትንሽ የለውም
• የሴት ጉልበት ምላሱዋ
• የሴት ጠጪ የግመል ፈንጪ
• የሴት ዘበናይ የፊትዋን እንጂ የኋላዋን አታይ
• የሽማግሌ ፍቅር እና የክረምት አበባ አንድ ነው
• የሽሮ ድንፋታ እንጀራው እስኪመጣ ነው
• የሽሮ ድንፋታ እስኪቀርብ ድረስ
• የቀረ ይቀራል እንጂ ቀርቅር ብዬ አልጣራም
• የቀበሮ ባህታዊ የለም
• የቀበጠች አይጥ በድመት ጭራ ዘፈን ትዘፍናለች
• የቀበጠች አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች
• የቀበጠ እንትን ቅቤ ቀቡኝ ይላል
• የቀበጡ እለት ሞት አይገኝም
• የቀን ጠማማን ሚዳቆ አትዘለውም
• የቀጣፊ እንባ ባቄላ ያክላል
• የቂጥ አጋሚ ፈስ ነው ወሮታው
• የቃመ ተጠቀመ ያልቃመ ተለቀመ
• የቃርያ እልክ አወፈረኝ
• የቄስ ጠበቃ ዳዊት ይጠቅሳል
• የቅርብ ጠበል የልጥ መንከሪያ ይሆናል
• የቅድሙ በዛ ያሁኑ ተንዛዛ
• የቆጡን አወርድ ብላ መሰላል አመጣች
• የቆጡን አወርድ ብላ ቤቷን ከርቸሌ አደረገች
• የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
• የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷ ጸጉር ታየ
• የቆጡን አወርድ ብላ የጣራውን አወረደች
• የበላ በለጠኝ የሮጠ አመለጠኝ
• የበላ ባይማታም ዱላ ይችላል
• የበላችው ያገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል
• የበላና የተደገፈ ወድቆ አይወድቅም
• የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም
• የቡና ስባቱ መፋጀቱ
• የባለጌ ባለሟል ቂጥ ገልቦ ያያል
• የባሪያ ደግ የቁልቋል ዘንግ የለውም
• የባስ አለ ሚስትህን አትፍታ
• የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ
• የቤቴ መቃጠል ለትኌኔ በጀኝ! አለች አሉ!
• የባህር ዳር ሲታረስ ጓጉንቸር ሆድ ይብሳታል
• የባልቴት ወብራ የክረምት ብራ
• የባል ደግነቱ ውሽሜን መርሳቱ
• የባል ደግነቱ ውሽምን መርሳቱ
• የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ
• የባእድ ፍቅር የውሀ ጌጥ አንድ ነው
• የቤት ቀጋ የደጅ አልጋ
• የተለጎመ በሬ ከቀንበሩ ቢያመልጥ ቢላዋ ይጠብቀዋል
• የተመረረ ድሀ ይገባል ከውሀ
• የተማረና ታጥቦ የተቀመጠ ብርጭቆ ፈላጊ አያጣም
• የተጠማ ከፈሳሽ የተጠቃ ከነጋሽ
• የተናቀ ሰፈር በአህያ ይወረራል
• የተናቀ ብእር ይገነፍላል
• የተናቀ እንትን ያስረግዛል
• የተናቀ ያስረግዛል
• የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
• የተናገሩት ከሚጠፋ ጽፎ ማስቀመጥ
• የተናጠ ወተት ቅቤ ይወጣዋል
• የተንቀለቀለች አፍሳ ለቀመች
• የተንቀዠቀዠች ውሻ ላፏ ሊጥ ለወገቧ ፍልጥ አታጣም
• የተከፋ ተደፋ
• የተገነዘች ነፍስ የተለጎመች ፈረስ
• የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው
• የት ትሂጃለሽ ቢላት በታክሲ አለች
• የት ትሂጃለሽ ቢሏት በታክሲ
• የት አውቅሽ ብሎ አጥብቆ ሳመኝ
• የቸኮለ አፍስሶ ለቀመ
• የቸገረው እርጉዝ ያገባል ስትወልድበት ገደል ይገባል የባሰበት እመጫቷን
• የቸገረው ዱቄት ከንፋስ ይጠጋል
• የነሀሴ ውሀ ጥሩ ነው የሚጠጣው የለም የድሀ ነገር ፍሬ ነው የሚሰማው የለም
• የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም
• የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
• የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ብሎኬት
• የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው አስቤስቶስ
• የነቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ጭራሮ
• የነቶሎ ቶሎ ቤት በሊዝ ተሸጠ
• የነቶሎ ቶሎ ቤት ዘበኛው ቶሎሳ
• የነፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
• የእናት እርግማን ወለምታ ነው
• የእናት ሞትና የግር እሳት እያደር ያንገበግባል
• የእናት ልጅ ቢጣላ እውነት ይመስላል ለሌላ
• የእናት ልጅ የሌለው አይበላ ሽሮ የሌለው ምንቸት አይፈላ
• የናት ሆድ ዥንጉርጉር
• የናት ሆድ ዥንጉርጉር ወላጅ ቀይና ጥቁር
• የናት ልጅ የጎን አሳጅ
• የናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል
• የናትን ክፋት የደመናን ውሀ ጥማት ባለቤቱ ያውቀዋል
• የናት ድሀ የለውም
• የንግዳ አይን አፋር ባለቤቱን ይጋብዛል
• የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም
• የአህያ “እቃው” ሆዱ ውስጥ ነው
• የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ
• የአሳ ግማቱ ከወደ ጭንቅላቱ
• የ10 አለቃዬ ምክትሌ ሆይ አንተም እንደ መቶ ትኮራለህ ወይ
• የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ
• የአባይ ልጅ ኩሬ
• የአባይን ልጅ ወዳቂ የዞማ ልጅ ሳቂ
• የአባይን ልጅ ውሀ ጠማው የላጭን ልጅ ቅማል በላው
• የአንዱ ሀገር ዘፈን ለአንዱ ሀገር ለቅሶ ነው
• የአንድ ቀን መዘዝ ያለ ዘጠኝ ወር አይመዘዝ
• የአይጦች አድማ ምርጫ እስኪደርስ ነው
• የአገሬ ሰዎች ተጠንቀቁ የሰረቁት ስጋ ያስይዛል መረቁ
• የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
• የአፍ ወለምታ በፖሊስ ይታሻል
• የእህል ክፉ አጃ የሳር ክፉ ሙጃ የነገር ክፉ እንጃ
• የእህል ጣም በጉረሮ የነገር ጣም በዦሮ
• የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል
• የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል
• የእንጨት ምንቸት እራሱ አይድን ሌላ አያድን
• የክፉ ሰው ተዝካር ውሀ ያስወስዳል በህዳር
• የክረምት ጥማትና የመከር ጊዜ ረሀብ አለባለቤቱ የሚያውቀው የለም
• የወረት ውሻ ስሟ ወለተኪሮስ
• የወረቀት ላይ ነብር የተግባር ስንኩል (አንሁን)
• የወንድ አልጫ የእንዶድ ሙቀጫ
• የወንድ አጭር ዝንጀሮ የሴት አጭር ወይዘሮ
• የወንድም ልጅ ባይወልዱትም ልጅ
• የወንዶች ባል አይተህ ማር
• የወንድ ልጅ ሞት ያደረገውን የዘነጋለት
• የወንድ አልጫ እንዶድ ሙቀጫ
• የወንድምህ ጢም ሲላጭ ጢምህን ውሀ አርስ
• የወጣ ቢገባ የገባ ይወጣል
• የወደቀ ዛፍ መንገዱን ዘጋ
• የወደደና የአበደ አንድ ነው
• የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ
• የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም
• የወጋ ቢረሳ ፖሊስ ያስታውሳል
• የወጌሻ ልጅ ዛፍ ላይ ያድራል
• የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል
• የዋኘ ይሻገራል የሰራ ይከብራል
• የውሀ ሽታ የእባብ ፍለጋ የለውም
• የውሀ ውሀ ምን አለኝ ቀሀ
• የውሀ ጡር በእድፍ ያስታጥባል
• የውድማ ዘንዶ ይቀጠቀጣል እንደበረዶ
• የዘመድ ዘመድ ወንዝ ያሻግራል
• የዘመድ ጥል የስጋ ትል
• የዘሬን ብለቅ ይቆማምጠኝ አለ ቆማጣ
• የዘንድሮውስ ብርድ ቆማጥ ያሳቅፋል
• የዘገነ አዘነ ያልዘገነ አዘነ
• የዝንጀሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ
• የዝንጀሮ ስብሰባ በውሻ ጩኸት ይበተናል
• የዝንጀሮ ንጉስ እሱ ይከምር እሱ ያፈርስ
• የየጁ ቄስ አንደዜ ቅኔው ቢጎልበት ቀረርቶ ሞላበት
• የየጁ ደብተራ ቅኔ ቢያልቅበት ቀረርቶ ጨመረበት
• የደላው ሙቅ ያኝካል
• የደላው ወርቅ ያስራል
• የደመና ውሀ ጥምና የእናት በደል አይታወቅም
• የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መልሶ
• የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ
• የደንቆሮ ሰርግ በሽብሸባ ያልቃል
• የድመት ልጅ መቧጨሯን አትረሳም
• የድሮው ኮንጎዬ ካሁኑ ስቶኪንጌ ተሻለኝ
• የድፍድፍ ኩራቱ ውሀ እስኪገባበት
• የድፍድፍ ኩራቱ ውሀ እስኪገባ ነው
• የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል
• የጅብ ችኩል ቶሎ ያፏጫል
• የገበያ ሽብር ለሌባ ሰርጉ ነው
• የገበያ ግርግር ለሌባ ይበጃል
• የገንዘብን ነገር ካሰላሰሉት አባ ሀናም ሞቱ እንደጨበጡት
• የገጣጣ ሚስት ችግሩን አልቅሶ ካልነገራት አይገባትም
• የጉልበት ግማሹ አፍ ነው
• የጉድ አገር ገንፎ በጣም ይጣፍጣል
• የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል
• የጉሮሮን መታነቅ ያይን መደንቆል ያስጥለዋል
• የጎረምሳ መልኩ እንጂ አነጋገሩ አያምርም
• የጎጃም አዝመራ ሽንብራ ነው አሉ እኛም እንዳንበላ ተነቀለ አሉ
• የጊዜ ግልባጭ እግር ሰውነት ያካል
• የግመል ሽንት ይመስል ሁሌ ወደኋላ
• የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
• የጥቅምት ቀን እና የቆንጆ ሳቅ አያታልልህ
• የጥንት ወዳጅክን በምን ሽኘኸው በሻሽ አዲሱ እንዳይሽሽ
• የጨለማ አፍጣጭ የእውር ገልማጭ
• የጨለማ አፍጣጭ የእውር ገልማጭ አይረባም
• የጨረቃ ሂያጅ የምስክር ፈራጅ
• የጨረቃ ሂያጅ የምስክር ፈራጅ
• የጨረቃ ንጋትና የእውር ሞት አይታወቅም
• የጨርቅ ነጩ የበራ ልጩ
• የጨነቀው እርጉዝ ያገባል
• የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ስትወልድበት ገደል ይገባል
• የጨነቀው ይዋጋል ያልደረሰበት ያወጋል
• የጨዋ ልጅ ሁሉ አርግዟል ሆዱ
• የጨዋ ልጅ ሁሉ አርግዟል በሆዱ
• የጨዋ ልጅ ሲያዝን አሳ በወንዝ ይመክን
• የጨዋ ልጅ ሲያዝን ውሀ በወንዝ ይመክን
• የጨዋ ልጅ ሲፋታ ይጋባ ይመስላል
• የጨዋ ልጅ ከከተማ የድሀ ልጅ ከውድማ
• የጨዋ ልጅና ቅል ተሰባሪ ነው
• የጨው ገደል ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልህ ያለቅሳል
• የጨው ገደል ሲናድ ብልህ ያለቅሳል ሞኝ ይልሳል
• የጨውን ባለእዳ በጨው ቢያባብሉት ጨዌን ማለቱ አይቀርም
• የጨጌ ከብት በየወገኑ ይከተት
• የጫማ ጠጠርና የእንጀራ ልጅ እያደር መቆርቆሩ አይቀርም
• የጫማ ጠጠርና የእንጀራ እናት እያደር መቆርቆሩ አይቀርም
• የፈላ ጠጅ የደረሰ ልጅ
• የፈረሰኛ ማቅ ለባሽ የሴት ትምባሆ ቀማሽ
• የፈረሰኛ ማቅ ለባሽ የሴት ትምባሆ ጎራሽ
• የፈረሰ አልጋ የተሸበረ ዜጋ
• የፈረንጅ አሽከር ነጭ ለባሽ ሳህን አመላላሽ
• የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል
• የፈሪ ዱላ ሰላሳ ነው
• የፈሪ ዱላ አያዳግምም
• የፈሪ በትር አስር
• የፈሪ ገዳይነት ለማታ
• የፈሰሰ ውሀን ማቆር ይጠቅማል
• የፈሰሰ ውሀ አይታፈስ
• የፈሰሰ አይታፈስ የሞተ አይመለስ
• የፈሲታ ተቆጢታ
• የፈሳ የጥጋብም አይደል ሲረሳ
• የፈስ ማደናገሪያው ዳባ
• የፈስ ማደናገሪያው ዳቦ
• የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ ነው
• የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ ናቸው
• የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
• የፊተኛውን አሳረርሽ ቢሏት የኋለኛውን ጥሬ አወጣች
• የፊት መሪ የኋላ ቀሪ
• የፊት ምስጋና ለኋላ ሀሜት ያስቸግራል
• የፊት እድፍ በመስታወት የሀጢአት እድፍ በካህናት
• የፊት ከብት የእጅ ወረት
• የፊት ወዳጅህን በምን ቀበርከው በሻሽ የኋለኛው እንዳይሸሽ
• የፊት የፊቱን አለ ጓያ ነቃይ
• የፋቂ ልጅ ሰነፍ አንዱን ሳይፍቅ አንዱን ይዘፍቅ
• የፋቂ ሰነፍ አንዱን ሳይፍቅ አንዱን ይዘፍቅ
• የፋቂ ቆንጆ ቡድነቱን አይተውም
• የፌጦ መስሎሽ ሰናፍጭ ትቀምሽ
• የፌጦ ብቅል የብሳና ጌሾ የተልባ አሻሮ ይህን ጠምቆ ለማ የሰው ነገር ለማይሰማ
• የፍቅር ጣእሙ በመሳለሙ
• የፍቅር ጣእሙ አልጋ ላይ
• የፍቅር ጣእሙ ተቃቅፈው ሲተኙ
• የፍቅር ደስታው ከሴት ጭን መሃል ይገኛል ፈልጉ
• የፍየል ልጁን የሌባ እጁን
• የፍየል ጅራት ቂጥ አይከድን ከብርድ አያድን
• የፍየል ጅራት ብልት አይከድን ከብርድ አያድን
• የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን ብልት አይከድን
• የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን አፍረት አይከድን
• የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን እፍረት አይከድን
• የፍየል ጭራና የሰው ሀሳብ ሁልጊዜ ወደ ላይ ነው
• የፍጅት ወራት እሳት በወንፊት
• የፖሊስ ዘመድና የቤንዚን አመድ
• የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም
• ዪዪዪዪዪ ………አለ !አምቡላንስ (የቁጭት አባባል)
• ያህያ ስጋ አልጋ ቢሉት አመድ
• ያህያ ባል ቀለበት አያስርም
• ያህያ ባል ከጅብ ጉቦ በላ
• ያህያ ባል ከዥብ አያስጥል
• ያህያ ውሀ ጠጭ ሳይታወቅ መጣጭ
• ያህያ ልጅ ጥሎ ይረግጣል የፈረስ ልጅ ጥሎ ይደነግጣል
• ያህያ ስጋ ካልጋ ሲሉት ካመድ
• ያህያ ካልጋ ሲሉት እምድር
• ያህያ ስጋ ውርደተኛ አልጋ ላይ ቢያኖሩት እመሬት ይተኛ
• ያህያ ቀበጥ ከጅብ ጡት ይጣባል
• ያህያ ባል ከጅብ አያስጥል
• ያህያ እንግዳ የጅብ እራት ነው
• ያህያ ደግነት ጭነት ማብዛት
• ያህያ ውሀ ጠጭ ሳይታወቅ መጣጭ
• ያህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ የሹም ዘፋፋ አገር ያጠፋ
• ያህያ ፍለጋና የጥሬ እራት በግዜ ነው
• ያህያ ፍሪዳ የእባብ ለማዳ የለውም
• ያለባለቤቱ አይነድም እሳቱ
• ያለአንድ የላት በዘነዘና ትነቀስ
• ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም
• ያለውን የወረወረ ንፉግ አይባልም
• ያለአዋቂ ተራች የራሱን አመልካች
• ያለ ዝናብ ነጎዳ ያለ ብድር እዳ
• ያለ ወጉ አህዮች ተዋጉ
• ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ
• ያለ የሚኖር ይመስላል የሞተ ያልነበረ ይመስላል
• ያለ ይበዛል (አለ ወፍጮ)
• ያለህ ምዘዝ የሌለህ ፍዘዝ
• ያለ መሰረት ቤት ያለ ትምህርት እውቀት የለም
• ያለ መከራ አይገኝም እንጀራ
• ያለ መከራ ጸጋ ያለ ድካም ዋጋ አይገኝም
• ያለ መጥረቢያ እንጨት ሰባሪ የቆማጣ ዘንግ ወርዋሪ
• ያለ ምቀኛ አይገኝ ፍቅረኛ
• ያለ ሴት ምን ያደርጋል ቤት
• ያለ ሴት ቤት ያለበሬ መሬት
• ያለ ስራ መብል ያለዳኛ ውል
• ያለ ስራ መብል ያለዳኛ ውል አይቻልም
• ያለ ስራ አይበላ እንጀራ
• ያለ ስራ አይበላ እንጀራ አለባል ቆጥ አይሰራ
• ያለስፍራው የተስበረ ሲጠግኑት አስቸገረ
• ያለስፍራው የተስበረ ሲጠግኑት ያስቸግራል
• ያለ በሬ ምን ያደርጋል ገበሬ
• ያለበት ይብላላበት
• ያለበት ይጉላላበት
• ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ
• ያላባቱ ቢዛቁን አባክኖ ያባክን
• ያለአቻ ጋብቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ
• ያለ እዳው መዝመት ዋ ብሎ መቅረት
• ያለ እዳው ዘማች ዋ ብሎ መቅረት
• ያለ ክንፍ መብረር ያለ ስራ መክበር
• ያለው ሳይዋደድ ለሞተው መናደድ
• ያለው ይምዘዝ የሌለው ይፍዘዝ
• ያለው ይመዛል የሌለው ይፈዛል
• ያለው ይበላል የሌለው ያፈጣል
• ያለውን ካልሰቱ በስም አይበሉ
• ያለ ዘዴ ጋሻ እንቅብ ነው
• ያለ ዘመድ ነግሶ ያለ አቡን ቀስሶ
• ያለ ዝናብ ነጎዳ ያለብድር እዳ
• ያለ የሚኖር ይመስላል የሞተ ያልነበረ ይመስላል
• ያለ ጊዜው የተወለደ ልጅ አባቱን ጥሎ አያቱን ያስረጅ
• ያለ ጎረቤት ቡና ያለ ሙያ ዝና
• ያለ ጎታ ደረባ ያለልብስ ካባ
• ያለ ጎተራ ደረባ ያለልብስ ካባ
• ያለ ጎታ ደረባ ምንድን ነው
• ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ
• ያለ ጥርስ ቆሎ ያለ ጓድ አምባጓሮ
• ያለ ጨው በርበሬ ያለሞፈር በሬ
• ያለ ፊቱ አይቆርስ ያለባለቤቱ አይወርስ
• ያለ ፍርድ ማሰር በፈጣሪ ማማረር
• ያለ ፍቅር ሰላም ያለ ደመና ዝናብ
• ያለ ፍቅር ጸሎት ያለ እንጨት እሳት
• ያሉሽን በስማሽ ኖርዌይ ባልመጣሽ
• ያሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ
• ያላማረ ሰርግ ጉልቻው ይሽረፋል
• ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል
• ያላዩት አገር አይናፍቅም
• ያላረፈች ምላስ ሸማ ትልስ
• ያላረፈች እግር ከዘንዶ ጉድጓድ ትገባለች
• ያላሰብከውን አግኝ መረገመም ምርቃን አይደል
• ያላስደጉት ውሻ ቤት ዘግተው ቢመቱት ዞሮ ይናከሳል
• ያላባቱ ቢዛቁን አባክኖ ያባክን
• ያላዋቂ ሳሚ ምላስ ይነክሳል
• ያላወቁ አለቁ
• ያላዞረ ሲዞር አደረ
• ያላዋቂ ቆራሽ ማእድ አበላሽ
• ያላየ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
• ያላዩት አገር አይናፍቅም
• ያላዩት ነገር ክፉ አይደለም መልካምም አይደለም
• ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
• ያልበላህን አትከክ
• ያልበላ ዳኛ አያሟግት ያልጠጣ እንግዳ አይጫወት
• ያልተመካ ግልግል ያውቃል
• ያልተማረ ዋናተኛ ከዳኛ ፊት እንቢተኛ
• ያልተነካ ግልግል ያውቃል
• ያልተገላበጠ ያራል
• ያልታደለ ቆዳ ሲላፋ ያድራል
• ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል
• ያልታደለች ከንፈር ሳትሳም ታድራለች
• ያልታደለ ከንፈር ሊፕስቲክ ያበዛል
• ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል
• ያልነበረ ያፈርሳል ቀዳዳ ያፈሳል
• ያልወለደ አጋድሞ አረደ
• ያልወለድኩት ልጅ አባባ ቢለኝ ሆዴን ባርባር አለኝ
• ያልወለድኩት ልጅ አባዬ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
• ያልጠረጠረ ተመነጠረ
• ያልሟል ይተረጉሟል
• ያልሞላ ተርፎ አይፈስም
• ያልሞተና ያልተኛ ብዙ ይሰማል
• ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
• ያልሰማ ጥኑ ነው ባልሽ ወዳጄ ነው
• ያልሰሙት ነገር ክፉም መልካምም አይደለም
• ያልሰጡት ተቀባይ ያልጠሩት አቤት ባይ
• ያልሳሉት አይላጭ ያላዩት አይቆጭ
• ያልቆረጠ እግብ አይደርስም
• ያልበሉት እዳ ያልጠሩት እንግዳ
• ያልበላ ሬሳ ያልለበሰ እንሰሳ
• ያልበላ ዳኛ አያሟግት ያልጠጣ እንግዳ አያጫውት
• ያልበላኝን ቢያከኝ አይገባኝ
• ያልበጀው እሳት ፈጀው
• ያልተማረ አይጸድቅ ያልተወቀረ አያደቅ
• ያልተማረ አይምርም ያልተወቀረ አያደቅም
• ያልተመታ ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል
• ያልተማረ ዋናተኛ ከዳኛ ፊት እንቢተኛ
• ያልተረታ አይረታ ያልጠገበ አይማታ
• ያልተሾመ አያዝ ያልቀሰሰ አያናዝዝ
• ያልተሾመ አያዝ ያልቀሰሰ አይናዝዝ
• ያልተቀጣ ልጅ ቢቆጡት ያለቅሳል
• ያልተቀጣ ልጅ ያልታጠበ እጅ
• ያልተነካ ግልግል ያውቃል
• ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል
• ያልተገላበጠ ያራል
• ያልተገላበጠ ያራል ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ
• ያልተገራ ፈረስ ይጥላል በደንደስ
• ያልተጠናከረ ድንገት ተሰበረ
• ያልተፈተነ ወዳጅ ያልተተኮሰ ሸክላ
• ያልተፈተነ ወዳጅ ያልተተኮሰ ሸክላ ነው
• ያልታረመ አፍ ከዋንጫ ይሰፋል
• ያልታየ እንጂ ያልተሰማ ያልተደረገ እንጂ ያልተባለ ነገር የለም
• ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል
• ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል
• ያልታደች ወፍ አይኗ በጥቅምት ይጠፋል
• ያልነበረ ያፈርሳል ቀዳዳ ያፈሳል
• ያልወለደ አንጀት ጨካኝ ነው
• ያልወለደ አይነሳ የሽምብራ ማሳ
• ያልወለደ አጋድሞ አረደ
• ያልወለዱ ሁሉ ጊደሮች ይባላሉ
• ያልወለደኩት ልጅ አባባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
• ያልወለደኩት ልጅ አባ አባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
• ያልዘሩት አይበቅልም
• ያልዘራሁት በቀለብኝ ዱባ ያልኩት ቅል ሆነብኝ
• ያልዘራውን የሚበላ ዝንጀሮ ነው
• ያልገደለ በሽታ ምስጋና የለውም
• ያልገደለ ዘማች ያልወለደ አማች
• ያልጋ ሴሰኛ ሶስት ያስተኛ
• ያልጠረጠረ ተመነጠረ
• ያልጠሩት መካሪ ያልሾሙት ፊታውራሪ
• ያልጠሩት ሰርገኛ በትረኛ
• ያልጫ ድንፋታ እንጀራ እስኪቀርብ
• ያልጫ ድንፋታ እንጀራ እስኪቀርብ ነው
• ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል
• ያመል ትንሽ ይጥላል በጭራሽ
• ያመሰገኗት ቅል ባፏ ታፈሳለች
• ያሞሌ ጥጃ በወንዙዋ ትናፋ
• ያመነታ ተመታ
• ያመኑት ሲከዳ ይቀላል እዳ
• ያመኑት ፈረስ ጣለ በደንደስ
• ያመጣሁት ውሻ ነከሰኝ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ
• ያመጣል አንበሴ ይበላል ኮሳሴ
• ያማከሩት ዳኛ ያግዛል የመተሩበት እጅ ይወዛል
• ያምላክን ነገር ምኑን አውቀሽው ወይ እኔ እበላው አንቺ አርመሽው
• ያምላክን ነገር ስንቱን አውቀሽው ወይ እኔ እበላው አንቺ አርመሽው
• ያምራል ብለው ለነብር ልጅ አይድሩም
• ያምራል ብለው ከተናገሩት ይከፋል ብለው ያስቀሩት
• ያምራል ብለው ከመናገር ይከፋል ብሎ መተው
• ያምራል ብሎ ይሸልሟል ያውቃል ብሎ ይሾሟል
• ያምሩዋል ይታደሏል
• ያምና ሞኝ ዘንድሮም ደገመኝ
• ያምናውን ዘንድሮ የአዋጁን በጆሮ
• ያሞላቀቁት ልጅ አይሆንም ወዳጅ
• ያሞሌ ጥጃ በወንዙዋ ትነፋ
• ያረረበት ያማስል
• ያረሮ ልጅ ጠለፋ
• ያረሰ እንደ ልቡ ጎረሰ
• ያረገዘች ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ
• ያረጀን ሹም ገባር ይከሰዋል ያረጀን ጅብ አህያ ይጥለዋል
• ያራስ ክፉ መበለት ያደጋ ክፉ እሳት
• ያራሷን በርጉዙዋ
• ያራሷን ገንፎ እርጉዙዋ ውጣ ሞተች
• ያርጋጅ አናጋጅ
• ያርጋጅ አንጓጅ
• ያሳደግሁት ውሻ ነከሰኝ ያነደድሁት እሳት ጠበሰኝ
• ያስረ ይፈታል የሰጠ ይረታል
• ያስለመዱት ሰው ሁልጊዜ እጅ ያያል
• ያሰቡት አይገድም ጎኔን ላርገው ጋደም
• ያሳደግኋት ጥጃ አለችኝ በርግጫ
• ያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ
• ያስታርቀኛል ሙተራ እያንዳንዱ እየኮራ
• ያሽላል ያሉት ኩል አይን ያጠፋል
• ያቀረቡልህን ጉረስ የተረፈህን መልስ
• ያበረ ወገኑን አስከበረ
• ያበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም
• ያ በሬ ባላገደደ ያ በሬ ገደል ባልገባ
• ያ በሬ ባገደደ ያ በሬ ገደል ገባ
• ያ በሬ ባገደደ ያ በሬ ገደል ገባ ያበጠው ይፈንዳ
• ያበደ ለኑሮው የፈረደ ለጉሮሮው
• ያበደች ጋለሞታ እናቷን ትመታ
• ያበደና የወደደ አንድ ነው
• ያበጠው ይፈንዳ
• ያባ ሆይ መቋሚያ ላዩ ባላ ታቹ ዱላ
• ያባ ጎፍናኔ ቤቱ በሪድ
• ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ
• ያባት ወዳጅ የድንጊያ ገድጋጅ
• ያባቱን ቢሰጡት ህይወቱ ያባቱን ቢነሱት ሞቱ
• ያባቱን ያገኘ ህይወቱ ያባቱን ያጣ ሞቱ
• ያባት ልጅ የደንደስ ስጋ
• ያባት ልጅና ጆሮ አንድ ነው
• ያባት ምርቃት አያስገባም ጥቃት
• ያባት ልጅ የማድጋ ዶሮ ነው
• ያባት ልጅ የማድጋ ዶሮ አንድ ነው
• ያባት ሞቱን አይወዱ ረጃቱን አይሰዱ
• ያባት ሞቱን አይወዱ ረድኤቱን አይሰዱ
• ያባት ሲቀር ምሰህ ቅበር
• ያባት አገር ከሞት አያስጥልም
• ያባት እርግማን ሲዳሩ ማልቀስ
• ያባት እዳ ለልጅ ያፍንጫ እድፍ ለእጅ የወፍጮ እዳ ለመጅ
• ያባት ወርቅ ባለዝና እህል ለቀጠና
• ያባት ያምራል የባእድ ያናግራል
• ያባት ያምራል የባእድ ያኖራል
• ያባት ደግ ይደልላል ያባት ክፉ ለእንጀራ ልጅ ያደላል
• ያባትህ ቤት ሲበዘበዝ አብረህ ዝረፍ
• ያባትህና የናትህ ወገኖች ሲጣሉ ጥግህን ያዝ
• ያባያ ልጅ ወዳቂ ያራኝ ልጅ አጥባቂ
• ያባያ እናት አትታረድም
• ያባያ ወንድሙ አይታረድም
• ያባይ ምልክቱ አንደበቱ የገዳይ ምልክቱ ሽልማቱ
• ያባይ እንባ አይታገድም
• ያባይን እናት ውሀ ጠማት
• ያባይ ውሀ ተለያየ ሲሉ ተገናኘ
• ያባይን ልጅ ውሀ ጠማው የላጭን ልጅ ቅማል በላው
• የአብሮ አደግ ልብ በቁና ይሰፈራል
• ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ላከከ
• ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ልክክ
• ያተር ክምር የጭሰኛ ክብር
• ያናጢን ልጅ ጅብ በላው የላጭን ልጅ ቅማል ፈጀው
• ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ ነው
• ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ የቄስ ልመና አናዞ
• ያንበሳ ማላጅ ጋማ ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተጎዝጉዞ
• ያንበሳ ማላጅ ጋማ ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተገን ይዞ
• ያንበሳ አማላጅ ጋም ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተገን ይዞ
• ያንበሳ ኮርዲዳና የጨዋ ልጅ ሞግዚት ከመሆን ይሰውርህ
• ያንበሳ ገራም ይውላል ከላም
• ያንተን የሚመስል የኔም አለኝ ቁስል
• ያንቺን አትበይ ገንዘብ የለሽ የሰው አትበይ ምግባር የለሽ
• ያንካሳ ልቡ ኢየሩሳሌም
• ያንዱ በሬ ሲሞት ላንዱ አጋዘኑ ፍስሀው ላንዱ ሀዘኑ
• ያንዱ ቤት ሲቃጠል ላንዱ ቋያው ነው
• ያንዱ ቤት ሳይጠፋ ያንዱ ቤት አይለማ
• ያንዱ ቤት ካልጠፋ ያንዱ ቤት አይለማም
• ያንዱ ነገር ላንዱ የእንጀራ ልጁ ነው
• ያንዱ አገር መልከኛ ላንዱ አገር ገባር ነው
• ያንዱ ላም ወተት ያንድ እርሻ እሸት
• ያንድ ሚስቱን የሺ ከብቱን
• ያንድ ሰው ፍቅር ባንድ እጅ እንደማጨብጨብ ያለ ነው
• ያንድ ሰው ነገር ሰምተህ አትፍረድ
• ያንድ በሬ እሸት ያንድ ላም ወተት
• ያንድ እርሻ እሸት ያንድ ላም ወተት
• ያንድ ቀን ስህተት ለዘላለም እውቀት ነው
• ያንድ ቀን ስህተት የዘላለም ጸጸት ነው
• ያንድዋ እለት አንድዋ ባልቴት
• ያንጎርጓሪ ጉልበት የተራጋጭ ወተት
• ያኖሩት እንቅርት መለያ ይሆናል
• ያኖሩት እንቅርት ያገለግላል
• ያኩራፊ ምሳ እራት ይሆነዋል
• ያኩራፊ ምሳው የነበረ እራት ይሆነዋል
• ያኮረፈ ልብሱን አራገፈ
• ያኮረፈ ምሳው እራቱ ነው
• ያወረደ መአቱን ያመጣ ምህረቱን
• ያወቀ ተጠነቀቀ የዘነጋ ተነጠቀ
• ያወቀ ተጠነቀቀ የዘነጋ ተወጋ
• ያወቀ ተጠነቀቀ ያላወቀ ተነጠቀ
• ያወቀ ናቀ
• ያወቀ ዘለቀ ያላወቀ አለቀ
• ያወቁ ሲታጠቁ ያላወቁ ተሳቀቁ
• ያዋቂ ሴት ቤት አለው ውበት
• ያዋቂ አጥፊ የእስራኤል ጣፊ
• ያዋቂ አጥፊ የጾመኛ ገዳፊ
• ያዋጁን በጆሮ የእለቱን በቀጠሮ
• ያውሬ ስጋ ለወሬ
• ያውቃል ብሎ ያሟል ያምራል ብሎ ይሸልሟል
• ያውቃል ብሎ ይሾሟል ያምራል ብሎ ይሸልሟል
• ያው እንዳያችሁኝ ቅዳሜ የወጣሁ ይቆጡኛል ብዪ አርብ ማታ መጣሁ
• ያዙኝ ልቀቁኝ
• ያዛዥ ቤተ ክርስቲያን ሳሚ ያጋፋሪ ራስጌ ቋሚ
• ያየ ላውራ ቢል ያልሰማ አወራ
• ያየ ላውራ ቢል የሰማ አወራ
• ያየ ልናገር ቢል የሰማ ላውራ አለ
• ያየ ቢሄድ የሰማ ይመጣል
• ያየ ቢሄድ ያልሰማ ይመጣል
• ያየ ይናገራል የተወለደ ይወርሳል
• ያዩትን ሊሰሩ አይናቸውን ታወሩ
• ያዩትን ቢያጡ ያላዩትን ይቀላውጡ
• ያያን ጨንቋራ ሁሉ ያየዋል
• ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ
• ያይጥ ሞት የድመት ሰርግ
• ያይጥ እርዳታ በጭራንፎ ያልቃል
• ያይጥ ፉከራ ለመከራ ድመት ምን ሊበላ
• ያይጦች ዝላይ ለነአቶ ውሮ ሲሳይ
• ያደረገችውን ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ
• ያደፈ በእንዶድ የጎለደፈ በሞረድ
• ያደፈውን በእንዶድ የጎለደፈውን በሞረድ
• ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም
• ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም
• ያዳቆነ ሰይጣን የግል ኮሌጅ ከፈተ
• ያዛቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም
• ያዳኝ ውሻ ጠጉር ባፉ ብትር ትርፉ
• ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ
• ያገሩን ሰርዶ ያገሩ በሬ ይወጣዋል
• ያገር ልማት የገበሬ ሀብት
• ያገር ልጅ በምን ይመታል በኩበት ያም እንዳይሄድ ያም እንዳይሞት
• ያገር ልጅ በምን ይማታል በኩበት ያ እንዳይሄድ ያ እንዳይሞት
• ያገር ልጅ የማር እጅ
• ያገር ልጅ የማር ጠጅ
• ያገር እድር ለንጉስ ያስቸግር
• ያገር እድር ጦም ያሳድር
• ያገርህ ልጅ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እህትህ
• ያገርህ ልጅ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እትህ
• ያገርህ ዱር ፍራትን ያስወግዳል እንጂ ከሞት አያድንም
• ያገርን ሰርዶ ያገር በሬ ያወጣዋል
• ያገባሽስ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ
• ያገባሽ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ
• ያገባሽ ይፈታሻል ወዮለት ለወለደሽ
• ያገኘ ከራሱ ያጣ ከዋሱ
• ያጓኑት ድንጋይ ተመልሶ ራስን
• ያጓኑት ድንጋይ ተመልሶ ራስን ይመታል
• ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል
• ያጣጣመ የቆረጠመ
• ያጣ ሰው ያገኝ አይመስለውም
• ያጥንት ፍላጭ የስጋ ቁራጭ
• ያፍ እማኝ አደረገኝ ለማኝ
• ያፌን እስክውጥ እድሜ ይስጠኝ ይላል እርኩም
• ያፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
• ያፍ ዘመድ በመንገድ አይገድ
• ያፍላ ለማኝ አደረገኝ ለማኝ
• ያፍላ የለው ቀርፋፋ
• ያፍላ የለው ቀፋፋ
• ይሄ እንግዳ ቸኮለ ሊያድር ነው መሰለኝ
• ይህ ሁሉ ከርከሬሻ ባንቺ የተነሳ
• ይህ ሁሉ ጠባሳ ባንቺ የተነሳ
• ይህ አንበሳ ደም ደም አገሳ
• ይህ እንግዳ ቸኮለ ሊያድር ነው መሰለኝ
• ይህ ከርከሬሻ ዳቦዬን ለማንሻ
• ይህን ብሰጥ ምን እውጥ
• ይህን ብትሰጥ ምን ትውጥ
• ይህንን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
• ይህን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
• ይህች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም
• ይህች ተፍተፍ እኔን ለመመንተፍ
• ይሆናል ብዬ ጎሽ ጠመድኩ የማይሆን ቢሆን ፈትቼ ሰደድኩ
• ይሆን ቢሆን ዝሆን ይበላ ቢሆን
• ይሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ
• ይሉሽን ባልሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ
• ይሉሽን ባወቅሽ ገበያም ባልወጣሽ
• ይሉ አይሉ የት አለ ቅሉ
• ይሉሽን ብትሰሚ ጎንደር ላይ ክረሚ
• ይሉኝ አይል ውሽማ ዶሮ ሲጮህ ይማለላል
• ይሉኝ አይል የኋላውን አያይ
• ይሉኝ አይል ጸሀፊ ከሙሴ ይገድፋል
• ይሉኝታ ተፈርቶ እስከመቼ ተቆራምቶ
• ይሉኝታና መጠቀም ባንድነት አይገኙም
• ይሉኝታ የራስ አሊን ቤት ፈታ
• ይመሰክረዋል ለነፍሱ ይፈተፍተዋል ለከርሱ
• ይመስል አይመስል የጠይብ እጅ ተከሰል
• ይመታሉ የሚጠሉ ይመስል ይስማሉ የሚወዱ ይመስል
• ይሙት የገደለ ይካስ የበደለ
• ይማሩኝ እያልክ ከምትታማበት አትገኝ
• ይማሰላል ካሉ ይዛመዳል አይገድም
• ይሰጠኝ መስሎ ሊሸጠኝ
• ይሰጡኛል ብሎ ከሰጠ ቆጥቦ የበላ በለጠ
• ይስጡ ብሎ ከሰጠ ቆጥቦ የበላ በለጠ
• ይሰጣል መስሎ ይሸጣል
• ይስብረኝ ይሰንጥረኝ የሚሉ የሰውን ልብ ሊሰብሩ
• ይቅር ለእግዜር ወድቆ እማይሰበር
• ይቅር ለእግዜር ወድቆ አይሰበር ሞቶ አይቀበር
• ይቅደም ደግነት ይከተል ቸርነት
• ይበላ እንደ ቤቱ ይሰራ እንደ ጉልበቱ
• ይበላ እንደ ቤቱ ይሰራ እንደ ጎረቤቱ
• ይበላው ካጣ ይበላበት ያጣ
• ይበጃል ያሉት መድሀኒት አይን አጠፋ
• ይበጃል ያሉት ኩል አይን አጠፋ
• ይብላ እንደ ቤቱ ይስራ እንደ ጎረቤቱ
• ይብላኝ ለወለደሽ ያገባሽስ ይፈታሻል
• ይብራና ይብራ ተጣሉ በሰው ሽንብራ
• ይታደሏል እንጂ ይታገሏል
• ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም
• ይቺ ባቄላ ያደረች እንደሆን አትቆረጠምም
• ይቺ ጎንበስ ጎንበስ አንድም ለመፍሳት አንድም እቃ ለማንሳት
• ይቺን ለኛ ጥሬን ለጌኛ
• ይቺም ቂንጥር ሆና ቡታንታ አማራት
• ይቺን በላህ ብለህ ጦሜን አታሳድረኝ አለ አሉ
• ይውደደኝ የጀርባዪ ቅማል አለች አንዷ
• ይገርማል አህያ ከዥብ ይከርማል
• ይደንቃል ይገርማል አህያ ከዥብ ይከርማል
• ይኖሩዋል በደጋ ይተኙዋል በአልጋ
• ይወልደዋል ካሉ ይመሰለዋል አይገድም
• ይውጋሽ ብሎ ይማርሽ
• ይጥሉህ አትጥላቸው ይበድሉህ አትበድላቸው
• ይጠላኝ ይመስል ይመታኛል ይወደኝ ይመስል ይስመኛል
• ይወደዋል ካሉ ይመክሩዋል ይወልደዋል ካሉ ይመስሏል
• ይውጋህ ብሎ ይማርህ
• ይውጋህ ብሎ ይማርክህ
• ይገርመኛል ገንፎ ከራቴ ተርፎ
• ተረትና ምሳሌ