February 15, 2021

May be an image of 1 person, sitting and text that says 'እን Ethiopian Press Agency 80 Gebabo Gebere'

ህወሓትን ከመሰረቱ ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ግደይ ዘርዓጽዮን ይናገራሉ፡-

👉ህወሓቶች የዘመናት ድርጊታቸው ለዚህ አሁን ላሉበት ውርደት፣  ሞትና መደበቅ ዳርጓቸዋል፤ በተንኮልና በሴራ ራሱን አጥፍቷል፤

👉ትግሉ የተጀመረው ደርግ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት ተራማጅ  በሆኑ የትግራይ ተወላጅ ወጣቶች አማካይነት ማህበረ ገስገስቲ ብሔረ  ትግራይ (ማገብት) የሚል ማህበርን በመመስረት ነው፤

👉በህወሓት ውስጥ ማርክሲስት ሌሊኒስት ርዕዮተ ዓለም ሲመሰረት  በወቅቱ በተለይም ጥቂቶች የስልጣን መወጣጫ ነበር ያደረጉት፤

👉ስልጣናቸውን ለማሰንበት ሲሉ መወንጀል ጀመሩ፣ እንኳን በድርጅቱ  ውስጥ ሃሳብን አንስቶ የመከራከር መብቱ ይቅርና የሚነሱ ሀሳቦችን  በማዋደቅ ልዩነቶች እንዲሰፉ ይደረግ ነበር፣

👉የአልባንያ ተከታዮች ነን፤ እኛ ማርክሲስት ሌሊኒስት ነን፤ ብለን  አላማችንን ለዓለም ህዝብ ማሳወቅ አለብን የሚል አመለካከት ነበራቸው፤

👉ድርጅቱ ውስጥ የምንሰራው በእምነት ነው፤ ጓደኞቻችን በእኛ ላይ  እንደዚህ ዓይነት ሴራ ይሸርባሉ ብለንም በፍጹም አናስብም ነበር፤

👉ሴራቸውማ በጣም ከባድ ነው፤ እርስ በእርሳቸውም እየተባሉ ነው  እዚህ የደረሱት፤ ኢ- ዲሞክራቲክ፤ አፋኝ ሌላ ተቃዋሚ እንዳይታይ  የሚያደርግ፤ ለይስሙላ ምርጫ የሚያደርግ፤

👉በጎን ደግሞ ግልጽና ፍትሃዊ እንዳይሆን ጠንካራ ስራን የሚሰራ፤  ሀገሪቱ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ስር እንድትወድቅ ያደረገ  የተቃወሙትን የገደለ፤ ያፈነ፤ ያሰረ፤ ያሰደደ ነበር፣

👉ለውጡን አብዛኛው የአገሪቱ ህዝብና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንድም  ይሁን በሌላ ምክንያት ተቀብለዋል፣

ዝርዝር ዘገባውን ሊንኩን ተጭነው ያገኙታል
https://www.press.et/Ama/?p=41395