ፌብሩወሪ 17, 2021

ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሱዳን አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋር ጅቡቲ ውስጥ ታህሳስ 20 ቀን 2020፣ በ38 ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በጎን ለብቻቸው ተገናኝተው ነበር፡፡

ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሱዳን አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋር ጅቡቲ ውስጥ ታህሳስ 20 ቀን 2020፣ በ38 ኛው የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በጎን ለብቻቸው ተገናኝተው ነበር፡፡

ዋሽንግተን ዲሲ — የኢትዮጵያ ወታደሮች የድንበሬን ወሰን ተሻግረው ገብተዋል ስትል፣ ሱዳን፣ በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያን ከሳለች፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ደግሞ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተፈጠረው የድንበር ውዝግብ በመካረሩና ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በምታስገነባው ግድብ ዙሪያ ያለው ሁኔታ ለመምከር ሱዳን በኢትዮጵያ የሚገኘው አምባሳደሯን መጥራቷን አስታውቋል፡፡

የዛሬው የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ የወጣው፣ በሁለቱ ጎረቤት አገሮች መካከል የመሬት ይገባኛል ውዝግብ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡

የድንበር ውዝግቡ፣ ግብጽና ሱዳን “የተፈጥሮ ውሃ አቅርቦታችንን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል” በሚል ፣ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በምትገነባው ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ግድብ ዙሪያ፣ በሚያነሱት ክርክር ላይ፣ ሌላ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቃል አቀባይ መንሱር ቡላድ አብደላ፣ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደተናገሩት፣ ሱዳን በሁለቱ አገሮች ግንኙነት ዙሪያ ለመምከር በኢትዮጵያ የሚገኙት አባሳደሯን ወደ ካርቱም ጠርታለች፡፡ የውይይቱን ምንነት በዝርዝር ባያብራሩም ምክክሩ እንደተጠናቀቀ መልዕክተኛው አምባሳደር ወደ ሥራቸው ቦታ እንደሚመለሱ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና ሱዳን ውጥረት አይሏል
የኢትዮጵያ እና ሱዳን ውጥረት አይሏል

By ቪኦኤ