logo

ፌብሩወሪ 22, 2021

ለጥያቄዎ መልስ ዝግጅት/አቶ ፍሰሃ ተክሌ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አጥኚ ፣ አቶ ዳን ይርጋ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዲሬክተር

ለጥያቄዎ መልስ ዝግጅት/አቶ ፍሰሃ ተክሌ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አጥኚ ፣ አቶ ዳን ይርጋ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዲሬክተር አጋሩ

Print ዋሽንግተን ዲሲ — የሰብዓዊ መብቶች ላይ ጥቃት በሚፈፀምበት ግዜ፤ ጥቃቱ በራስ ላይ እንደተፈፀመ መቆጠር እንዳለበት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ኃላፊዎች ገለፁ። በጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን ከአድማጮች ለተነሱ ጥያቄው ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ዲሬክተር አቶ ዳን ይርጋና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ አጥኚ አቶ ፍሰሃ ተክሌ የሰዎች ሰብዓዊ መብቶች በሚጣስበት ጊዜ ጉዳዩን በተለያየ ጠርዝ ውስጥ በማስገባት ለፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ሃገሪቷን ከአዙሪት ውስጥ እንዳትወጣ ያደርጋታል ብለዋል።

በትግራይ ክልል የሚገኘውን የሰብዓዊ ሁኔታ አያያዝ እና ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተያያዙ ጉዳዮ ላይ አተኩሮ በተዘጋጀው በዚህ ውይይት ፤ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪዎቹ፤ የሰዎች ሰብዓዊ መብቶች መጣስ ማንኛውንም ሰው ሊያሳስበው ይገባል የሚል ሐሳብ አንፀባርቀዋል።

(ሙሉ ውይይቱን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

“የሰብዓዊ ጥቃት በሚፈፀምበት ግዜ በራስ ላይ እንደተፈፀመ ጥቃት መቆጠር አለበት” – የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች

By ቪኦኤ