No photo description available.

የሲዳማ ክልል በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሚኖረው መቀመጫ 19

– የደቡብ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና 104 ደቡብ ክልል ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው ውክልና ወይም መቀመጫ 123 ነበር፤ ሲዳማ ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን ከቻለ በኃላ ፣ ደቡብ የሚኖረው መቀመጫ ብዛት 104 ሆኗል።

– ኦሮሚያ ክልል በነበረበት 178፣

– አማራ ክልል በነበረበት 138፣

– ሶማሌ ክልል በነበረበት 23፣

– አዲስ አበባ ከተማ በነበረበት 23፣

– ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በነበረበት 9፣

– አፋር ክልል በነበረበት 8፣

– ጋምቤላ ክልል በነበረበት 3፣

– ሐረሪ ክልል በነበረበት 2 እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ በነበረበት 2 ሆነው ይቀጥላሉ።

6ኛው አጠቃላይ ምርጫ በትግራይ ክልል እንደማይከናወን ምርጫ ቦርድ ቀድሞ ያስታወቀ ሲሆን፣ ከሰሞኑ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው የክልሎች የፓርላማ ውክልና ድርሻ ውስጥም የትግራይ ክልል አልተገለጸም።

ይሁን እንጂ ላለፉት አሥርት ዓመታት የትግራይ ክልል የፓርላማ ውክልና 38 እንደሆነ ይታወቃል።

ይህንን ከግምት በማስገባት ሥሌት ሲደረግ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አጠቃላይ መቀመጫ ብዛት ከነበረበት 547 አልተለወጠም፤ ሊለወጥ የሚችለው ሕገመንግሥታዊ ለውጥ ወይም መሻሻል ከመጣ ብቻ ነው።

~ልብ በሉ፦ በዚህ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ውስጥ ነው የዜግነት ፖለቲካ አራማጆች ቦታ አለን ብለው ሕዝብ ሲያደነቁሩ የሚውሉት።

(ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ)