February 24, 2021

መንግሥት ቢቢሲ እና ሮይተርስን ጨምሮ 7 ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ትግራይ ክልል ገብተው ስላለው ሁኔታ መዘገብ እንዲችሉ ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ

በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ በተለያዩ አካላት የሚሰራጩ መሠረተ-ቢስ እና እና በፖለቲካ ሴራ የተሞሉ ሐሰተኛ መረጃዎች መንግስት እንዳሳሰበውም መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ለትግራይ ሕዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የሚቀርበው ጥሪ የመንግሥትን ሉዓላዊ ሥልጣን እና ኃላፊነትን ከማንኳሰስ ከሚደረጉ የፖለቲካ ፍላጎቶች እና ወገንተኝነት የፀዱ ሊሆኑ እንደሚገባም መንግሥት አሳስቧል።

በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሰብአዊ ድጋፍ፣ ሰብአዊ ተደራሽነት፣ የሚዲያ ተደራሽነት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራዎች እና በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳድር እያከናወነ ስላለው ሥራም በመግለጫው ተብራርቷል።

የሰብአዊ ድጋፍን በተመለከተ በአብዛኛው ከሚነዛው የሐሰት ወሬ በተቃራኒ መንግሥት ከሀገር ውስጥ ከውጭ ድርጅቶች ጋር በሠራው የቅንጅት ሥራ እስካሁን በክልሉ ከሚገኙ 36 ወረዳዎች መካከል በ34 ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ 3.1 ሚሊዮን ዜጎች ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።

በክልሉ የሰብአዊ ዕርዳታ ለማድረግ ላመለከቱ እና ዓለም አቀፍ መመዘኛውን አሟልተው ለተገኙ 135 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሠራተኞች በክልሉ ተንቀሳቅሰው የሰብአዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ መሰጠቱንም ገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት 29 ዓለም አቀፍ ተቋማት በአስቸኳይ አስተባባሪ ኮሚቴ ሥር ተዋቅረው ክልሉ ውስጥ በሥራ ላይ ይገኛሉ ብሏል።

No photo description available.
No photo description available.
May be an image of text that says 'Disinformation: The Government Ethiopia is cognizant of the overt and covert misinformation campaigns that have been launched against relation the law operations undertaken. The criminal clique's well financed etworks abroad continue employ use digital media other means, portray exaggerated misleading account events unfolding the ground. Statements and press releases being issued disinformation campaigr show ground. Rather, they need eflect partner agencies and countries that reflect uptake and indifference prevailing reality on the progress made ground. Government strongly citizens Tigray beware of launched against by those hidden political motives. Il commitment the አዲሲቷ ኢትዮጵያ፡አዲሲቷየተስፋአድማስ የተስፋ አድማስ Ethiopia: New Horizon Hope'