እጩ ዶ/ር ሲሳይ ሀብታሙ እባላለሁ።
የትምህርት ዝግጅቴ እስከ Ph D. ትምህርት በጥናትና ምርምር የተደገፈ ዘላቂ የከተማ ልማት ፕላኒንግ /Sustainable Urban Development Planning ሲሆን
ከማስትሬት ዲግሪ ጀምሮ እስከ PhD ትምህርት ድረስ ያደረኩት የጥናትና ምርምር ቦታውም በአዲስ አበባ የከተማ ልማት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጌ ነው።
ከማስትሬት እስከ ዶክትሬት ትምህርት ዝግጅት ሂደቴ የተማርኩት በአውሮፓ አህጉር በሚገኙት ሃገራት በስዊድን እና በቤልጅየም ሃገር ነው።
የአዲስ አበባ ከተማንና ችግሮቿን ፣ የህዝቦቿን ፍላጎት ጭምር በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በደንብ ጠንቅቄ አውቃለሁ። አዲስ አበባ ከተማችን ያሉባትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ሁሉ የማስወገጃ የመፍትሄ መንገዱን እና ሂደቱን ጭምር አስቤበት በእውቀት የተደገፈ ዝግጅት አድርጌበታለሁ ። የአዲስ አበቤዎችን ጥያቄዎችና ችግሮች ሁሉ በዘላቂነትና በአመርቂ ሁኔታ ለመፍታት ለረጅም አመታት በዘርፉ ላይ በሳይንሳዊ ትምህርትና የጥናትና ምርምር ሂደቶችን አድርጌ በጥናት ሰርቼ ጭምር አዲስ አበቤዎችን በሚያስደስትና ለ29 ዓመታት የተነጠቁትን መብቶቻቸውን ሁሉ በሚያስከብር ሁኔታ ለማገልገል እንዲሁም የአዲስ አበባን ዘርፈ ብዙ ችግሮቿን ለመፍታት በደንብ ተዘጋጅቼበታለሁ።
ፓርቲዬ ኢህአፓን ወክዬ ለአዲስ አበባ ክልል ተወካዮች ምክር ቤት በየካ ክ/ከተማ የምርጫ ክልል በእጩ ተፎካካሪነት በምርጫ ቦርድ ተመዝግቤያለሁ።
በ2013 ምርጫ ኢህአፓ ካቀረባቸው እጩ ተፎካካሪዎች ውስጥ የአዲስ አበባ ክልል መስተዳድር እጩ ከንቲባ ሆኜ የቀረብኩት እኔ ነኝ።
*የተሰራ አእምሮ የፈረሰ ከተማን ይሰራል*
የኢህአፓን ውክልና በመተማመን መንፈስ ሆነው ይምረጡ !
የአዲስ አበባችን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በጥናትና በምርምር በተደገፈ ሁኔታና በዘላቂነት በሚፈታ መልኩ እንዲሁም በጥንቃቄ በታቀደ ፕላን ፣ ከተለያዪ የባለድርሻ አካላትና አዲስ አበባ የኔ ነው ይገባኛል ብለው ከሚከራከሩ የይገባኛል ጥያቄ አንሺ ጠያቂዎች ጋር ሁሉ በሰከነ መንፈስ በመነጋገር እና በመግባባት እንዲሁም የመተሳሰብ መንፈስን በመፍጠር በፖለቲካው ተዋናይ ባለድርሻ አካላት እና በፖለቲከኞች መካከል እርስ በእርስ የመከባበር መንፈስን በማጎልበት ተያያዥ ችግሮቻችን ሁሉ በዘላቂነት እንዲፈቱ የሚፈልጉ ከሆነ በምርጫ ካርድዎ እኔን ይምረጡኝ ? ያስመርጡኝ ? በሚችሉት አቅም ሁሉ በምርጫ ቅስቀሳው ሂደት ሁሉ እንዳሸንፍ ይደግፉኝ?
አመሰግናለሁ
እጩ ዶ/ር ሲሳይ ሀብታሙ
ከየካ የምርጫ ክልል
አዲስ አበባ