ኤርትራ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በትግራይ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ የሐሰት ስትል ውድቅ አደረገችው
ኤርትራ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ያወጣውን የሐሰት ዘገባ ውድቅ አደረገች ፡፡ አስመሳይ መግለጫ አስመሳይ ውንጀላ ነው ስትል የሀሰት ክሱ ላይ ያላትን ቁጣ ገልጻለች። የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው የሃገራቸውን አቋም ይፋ አድርገዋል ሪፖርቱ በአብዛኛው የተመሰረተው በሱዳን ከሚገኘው የሃምዳይት የስደተኞች መጠለያ ካምፕ የመጡ 31 ያህል ግለሰቦች በሚሰጡት ምስክርነት ነው ስትል ኤርትራ መግለጫውን አጣጥላዋለች።
ባለፈው ህዳር ወር መጀመሪያ ላይ ማይ፡ካድራ ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በተፈፀመባቸው እልቂትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ከተሳተፉ በኋላ ወደ ሱዳን የሸሹ በዚህ ካምፕ ውስጥ የሚገኙት ብዙዎች መሆናቸው ይታወቃል ሲሉ አቶ የማነ የ ኤርትራን አቋም ይፋ አድርገዋል።

#Eritrea is outraged and categorically rejects the preposterous accusations levelled against it by Amnesty International in a fallacious report issued today. The report is largely based on testimonies of some 31 individuals from the Hamdayet Refugee camp in the Sudan.
አምነስቲ ከኤርትራ ማንኛውንም መረጃ ለመፈለግ በፍጹም ምንም ሙከራ አለመደረጉ ሊሰመርበት ይገባል ፡፡ በተጨማሪም ፣ የተፈበረከው የአክሱም የውሸት ክስ ባለፈው ወር ውስጥ “ከቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ላይ ከተፈፀመ ጭፍጨፋ” እስከ የዜጎች “ከቤት ወደ ቤት” መገደል ተለውጧል ፡፡ ስትል የሀሰት ክሱ ላይ ያላትን ቁጣ ገልጻለች ኤርትራ።

አምነስቲ፤ «በአክሱም በኤርትራ ወታደሮች የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን ይችላል»በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች በኅዳር ወር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ገድለዋል ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዉ ድርጅት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መግለጫ አስታወቀ። አክሱም ከተማ በኅዳር 10 እና 20፤ 2013 ዓ.ም መካከል የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊሆን እንደሚችል ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል። ድርጅቱ በመግጫዉ በአክሱም ከተማ በደረሰዉ ጥቃት በህይወት የተረፉ 41 የዓይን ምስክሮችን ማነጋገሩን እንዲሁም በከተማዉ የታየዉን ግጭት ሸሽተዉ ወደ ምስራቅ ሱዳን የገቡ ስደተኞችን በአካል አግኝቶ ማነጋገሩን ብሎም ስለጉዳዩ በአክሱም ከተማ ካሉ ሌሎች 20 ሰዎች ጋር የስልክ ቃለመጠይቆችን ማድረጉን አመልክቶአል። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች ኅዳር ወር አጋማሽ ላይ ከተማዋን ለመቆጣጠር ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ / ህወሃት / ጋር ዉግያ ከገጠሙ በኋላ በከተማዋ ግድያ ተፈጽመዋል፤ ፍንዳታዋች ደርሰዋል፤ ሰፊ ዝርፊያዎች ተፈጽመዋል ማለታቸዉን የከተማዋን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አምነስቲ በመግለጫዉ አመልክቶአል። አምነስቲ እንዳለዉ በድርጅቱ የሳተላይት ምስል ትንተና የጅምላ ግድያ እና ዘረፋ መካሄዱን ዘግቦአል። ትንተናዉ በከተማዋ በሚገኙ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት አቅራቢያ አዳዲስ የጅምላ መቃብር ምልክቶች እንደታዩ ምልክቶችን እንደሚያሳይ ገልጾአል።አምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና የደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮዘ ሙቼና «ማስረጃው ዘግናኝ ሁኔታ ስለመከሰቱ አሳማኝ መሆኑን ያያመላክታል » ማለታቸዉ በመግለጫዉ ተካቶዋል። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች አክሱምን ለመቆጣጠር በተካሄደዉ ጥቃት በርካታ የጦር ወንጀሎችን ፈጽመዋል ፡፡ ከዚያ በላይ የኤርትራ ወታደሮች በአመጽ በመሄድ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በግፍ መግደላቸዉ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል የተፈፀመ ይመስላል ”ሲሉ መናገራቸዉን መግለጫዉ አመልክቶአል። ዳይሬክተር ዴፕሮዘ ሙቼና «በአክሱም የታየዉ ሁኔታ እስካሁን በትግራይ ዉስጥ በነበረዉ ግጭት ከተመዘገቡት እጅግ የከፋ ነዉ። እየጨመረ ከሚሄደው የሟቾች ቁጥር በተጨማሪ የአክሱም ነዋሪዎች በሁከት ፣ በሐዘንና ስሜት ቀውስ ውስጥ ገብተዋል» ብለዋል። በአክሱም ከተማ የታየዉ ይህ የጅምላ ግድያ የተከሰተዉ በአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ በዓል ኅዳር 21 ከመከበሩ ከጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ መሆኑም የአምነስቲ መግለጫ ያመለክታል።
