የኢሕአፓ የኢንዱስትሪ ክፍለ ኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረታዊ ነጥቦች !

1.የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ መርህ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ !

2.የግል ባለሀብቶች ስላልተሰማሩባቸዉና ለሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ በመንግሥት ቁጥጥር ና አስተዳደር ስር እንዲዉሉ ከተደረጉት በስተቀር በኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የግል ባለንብረትነት መብት እንዲከበር ማድረግ !

3.የሀገር ዉስጥ ባለሀብቶች የኢንዱስትሪ መስክ ተሳትፎ እንዲያድግ የተጠና ድጋፍ ማድረግ ፤ሚዛናዊ (የተመጣጠነ ) የግብር ስርዓት በማዉጣት የሀገር ዉስጥ የኢንዱስትሪ ባለሀብቶችን መደገፍ !

4.በሀገሪቱ ዉስጥ የሚገኙ በመካከለኛ ና በከፍተኛ ደረጃ የተማሩ የሰው ሀይል ሀብቶችን አቅም በሰፊው የሚፈልጉ ና የሀገር ዉስጥ ጥሬ እቃዎችን በግብአትነት የሚጠቀሙ ለወጣቶች ና ለወጣት ሴቶች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥሩ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት ና ማዘመን!

5.ኢንዱስትሪዎች ና ፋብሪካዎች በተወሰኑ ቦታዎች ብቻ ሳይከማቹ ጥሬ እቃዎች ና ሊያሰሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ባሉባቸው በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲቋቋሙ ማድረግ !

7.በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ በግል ባለሀብቶች ና በመንግሥት ማካሄድ !

8.የዉጪ ሀገር ባለሀብቶች ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጥቅም ጋር በማይጋጭ መልኩ በተለያዩ የኢንዱስትሪ መስኮች ና የስራ ዘርፎች እንዲሰማሩ ማበረታታት !

#ኢሕአፓ ለተሻለች ኢትዮጵያ !

#ኢሕአፓ ለተሻለ ነገ!

#ኢሕአፓን ይምረጡ!

ለነገዋ ብሩህ ኢትዮጵያችን – ኢሕአፓ ይሁን ምርጫችን