የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዬታዊ ፓርታ (ኢሕአፓ )

ለመላ ኢትዬጲያውያን ና ለዓለም ጥቁር ህዝቦች ፣እንኳን ለ125 ኛ አመት የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል አደረሳችሁ !አደረሰን ! እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል !

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሀገር ዉስጥ የቀድሞው ጁንታ ህወሃት በፈፀመው የፖለቲካ ሴራና የጥላቻ ፖለቲካ ፣ጫፍ በወጣ መንግስታዊ ሙስና ና ብልሹ አሰራር ፣ማንነትን ባተኮሩ ጅምላ ጭፍጨፋዎች ወዘተ.በዉጭ ታሪካዊ ባላንጣዎቻችን በተለይ ግብፅ ና ሰሜን ሱዳን እንዲሁም የነጮችን የበላይነት በማቀንቀን ላይ የተጠመዱ ምዕራባውያን ሚዲያዎች ና በበጎአድራት ስም የተደራጁ ክፉ ዘረኞች በሚያናፍሱት ሚዛናዊ ያልሆነ ዘገባና ፍረጃ ወዘተ. በከባድ አደጋ ዉስጥ ትገኛለች ፤
ስለዚህ ሁሉም ሀገር ወዳድ የሆነ ኢትዮጵያዊ በሰላማዊ የዉይይት መድረክ የዉስጥ ችግሮቻችንን መፍታት የምንችልባቸው በርካታ ጊዚያት ከፊታችን እንዳሉ ተረድቶ የዉስጥ አንድነታችን መላላትን ተመልክተው የወረሩንና ያስወረሩንን ፣ሉዓላዊነታችንን የደፈሩትን ሀይሎች መክተን ና በሚፈልጉት የትግል ስልት አጫዉተን የአድዋ ን ድል እንድንደግም ጥሪውን ያቀርባል!
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ታጋድሎ ሉአላዊነቷ ለዘላለም ተከብሮ ይኖራል !
ሚኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ አበሻ!
ኢሕአፓ ለተሻለች ኢትዮጵያ !
ኢሕአፓን ይምረጡ !

