March 3, 2021


May be an image of one or more people, people standing and people sitting

በትናንትናው ዕለት ሱዳን እና ግብፅ ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡–የሱዳን ጦርሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሙሃመድ አልሁሴን እና የግብጹ አቻቸው ሞሃመድ ፋሪድ ናቸው ካርቱም ላይ ስምምነቱን የደረሱት ተብሏል፡፡ስምምነቱን ባኖሩበት ወቅት ሁለቱም ሃገራት ብሄራዊ የደህንነት ስጋት እንደተደቀነባቸው አስታውቀዋል፡፡የሱዳኑ የጦርሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ስምምነቱ ከብሄራዊ የደህንነት ጉዳይ ባሻገር ልምድ ያለው ጦር ለመገንባት ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡–ግብጽ ለሱዳን ለምታደርገው ድጋፍም ጠቅላይ ኢታማዡር ሹሙ ምስጋነናአቅርበዋል፡፡የግብጹ አቻቸው በበኩላቸው ሃገራቸው ከሱዳን ጋር በሁሉም መስኮች ትብብር ለማድረግ ማቀዷን ገልጸዋል፡፡ በተለይም በወታደራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ግንኙነቷን እንደምታጠናከርም አስረድተዋል፡፡

የግብፅ ጦር አዛዥ ካርቱም ፤ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካይሮ ናቸው።

ካርቱም ላይ ፦

ሰኞ ወደ ካርቱም ያመሩት የግብፅ ጦር አዛዥ ሌ/ጀ ሞሀመድ ፋሪድ ከሱዳን አቻቸው ሌ/ጀ ሞሀመድ አል ሁሴን ጋር የተለያዩ ወታደራዊ ስምምነቶችን ፈፅመዋል።

የግብፁ ጦር አዛዥ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ግብፅ እና ሱዳን ተመሳሳይ ብሄራዊ የደህንነት ስጋት ተደቅኖባቸዋል ፤ በጋራ መስራት የሚገባን ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። እንዲሁም “ሱዳን ለምታቀርብልን ወታደራዊ ነክ ጥያቄዎች ሁሉ ምላሽ ለመስጠት ግብፅ ዝግጁ ናት” ሲሉ ተናግረዋል ።

የሰዳኑ አቻቸው እንዳሉት ደግሞ ሃገራቱ የጋራ አደጋ የተደቀነባቸው በመሆኑ በወታደራዊ መስክ ትብብራቸው ጠንክሯል ብለዋል።

ካይሮ ላይ ፦

የሱዳን ው/ጉ/ሚኒስትር ማርየም አል ሳዲቅ ግብፅ በማቅናት በዋናነት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከግብፅ መንግስት ሃላፊዎች ጋር ሲመክሩ ዉለዋል።

የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን እንዳይካሄድ ለማድረግ ያስችላል ያሉትን ምክክር አድርገዋል።

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርየም አል ሳዲቅ ፥ ኢትዮጵያ ለብቻዋን የምታደርገውን ነገር እንድታቆም እንነግራታለን ፥ አካሄዷ ወደአላስፈላጊ አቅጣጫ ይዞን ሊሄድ ይችላልም ሲሉ ማስፈራሪያ አዘል ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል።

የግብፅ እና ሱዳን ሚኒስትሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ አለም አቀፍ አሸማጋዮች በድርድሩ እንዲገቡ ግፊት ለማድረግ ተስማምተዋል።

(Selam Mulgeta ,Ustath Jemal Bashir)

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርየም ሳዲቅ ኣልመሃዲ የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ከከፍተኛ የሀገሪቱ ልዕካን ጋር በመጪዎቹ ቀናት ሱዳንን እንደሚጎበኙ አሳውቀዋል።

በጉብኝቱ አል ሲ ሲ ከአብድል ፈታህ አልቡርሃን ጋርም ይመክራሉ ተብሏል።

ምክክር የሚያደርጉትም ስለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ፣ ስለ አካባቢ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንደሆነ ተሰምቷል።

አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ በመጭው ቅዳሜ ነው ሱዳንን ይጎበኛሉ የተባለው።

በትላንትናው ዕለት የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ግብፅ ካይሮ ላይ በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያላቸውን አቋም መግለፃቸው ፤ ካርቱም ላይ ደግሞ በጦር ኢታማዦር ሹሞቻቸው ወታደራዊ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወቃል።