March 5, 202

No photo description available.

በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ ሶደሬ ሪዞርት ውስጥ ሕገ ወጥ ስልጠና ሲወስዱ ከነበሩ 68 ሰዎች ውስጥ 53 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዳይሬክተር ኮማንደር ጸጋዬ ቶላ፣ እነዚህ ግለሰቦች “ፎሌ የጥበቃ፣ ጽዳትና ስልጠና” የተባለ ተቋም ሲያሰለጥናቸው ነበር ብለዋል፡፡

“ሶደሬ ሪዞርት ስልጠና የሚሰጥበት ቦታ አይደለም፣ ሲሰጥ የነበረው ስልጠናም ሕገ ወጥ ነበር” ብለዋል ኮማንደሩ፡፡

May be an image of 1 person

ኮማንደር ጸጋዬ፣ ለጥበቃ ስራ ከሚውሉ የጦር መሳሪያዎች ውጪ ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ተከማችተው መገኘታቸውን ገልጸው፣ የቡድን ጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ 29 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

ፎሌ የጥበቃ፣ ጽዳትና ስልጠና ተቋም እነዚህን ግለሰቦች ለጥበቃ ስራ እንደሚያሰለጥናቸው የገለጸ ቢሆንም፣ እንደዚህ ዓይነት ስልጠና ሲሰጥ በፖሊስ መምሪያ እውቅና መሆን ነበረበት፤ በስልጠና ላይ የነበሩ ሰዎች ማንነትና እንዴት ለስልጠናው እንደተመረጡ መገለጽ ነበረበት ብለዋል ኮማንደር ጸጋዬ፡፡

ኮማንደር ጸጋዬ ስልጠናው በሌሊት ሲሰጥ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ሕጋዊ ፍቃድና እንዳለውና እንደሌለው፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች እየተጣሩ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር ጸጋዬ፣ ጉዳዩን መከታተል ሲገባቸው ክትትል ያላደረጉ የመንግስት አካላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

No photo description available.