
ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርነት በአፍሪካ ህብረት በእጩነት ቀረቡ
ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ ብቸኛው አፍሪካዊ እጩ በማድረግ በሙሉ ድምጽ መምረጡን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታወቀ።
የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት 38ኛ መደበኛ ስብሰባ በየካቲት 24 እና 25 2013 ባደረገበት ወቅት ኢትዮጵያን ወክለው ለተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ተፎካካሪ የሆኑትን ዶክተር አርከበ ዕቁባይን በብቸኛ አፍሪካዊ እጩነት አጽድቋል ፡፡
ዶ/ር አርከበ ባለፉት ሰላሳ አመታት ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትና ቀጣይነት ላለው ሁሉን አቀፍ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያግዙ ፖሊሲዎችን በማውጣትና በማስተግበር ስኬታማ እንደሆኑ ህብረቱ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።
