March 7, 2021

አለማየሁ (አል) ገብረማሪያም በካልፎርኒያ እስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ፕሮፌሰር፣ ሳን በርናርዲኖ የህግ ጠበቃ፣ በበተለያ ጊዜያት ኢትዮጵያን በሚመለክቱ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ፅሑፎችን የሚፅፉ ምሁር ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር በሚታተመው ዘ ኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ ላይም የተለያዩ አርቲክሎችን በመጻፍ ይታወቃሉ። ዛሬም በወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ የጁንታው ወዳጆች የሚያደርጉት እንቅቃሴን ድብቅ ዓላማ በመግለጥ፤ የአሜሪካንና መሰል አገራትን አቋም የሚሞግት አስተያየታቸውን ጽፈዋል፤

👉 የህወሓት ቀንደኛ ደጋፊዎች ህወሓት ላለፉት 27 አመታት የፈጸመቻውን የጭካኔ ድርጊቶች በማለባበስ የተበደልን ጩህት እያሰሙ ናቸው፤

👉 የጁንታው ወዳጆች ድምጽ ሌላኛው ፍላጎት የለውጡን መንግስት ከስልጣን በማውረድ በምትኩ የእነሱን ኢ-ዲሞክራሲያዊ የነበረውን አገዛዛቸውን መመለስ ነው፤

👉 ይህንኑ እቅዳቸውንም በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ አረሜናዊ ጥቃት በመፈጸም ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል፤

👉 እነዚህ እውነታዎች በአሜሪካኖች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው በማስመሰል መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሳካት እየጣሩ ይገኛሉ፤

👉 እነዚህ የቀድሞውን አገዛዝ ለመመስረት፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመገዳደር የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈጸም፤ እንዲሁም የቀጠናውን ሰላም ማወክ ነው፤

👉 ኢትዮጵያዊያን፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በሁለቱ ሀገራት ፍላጎት እና መከባበር ላይ የተመሰረተ መሆኑን በግልፅ ማስረዳት አለባቸው፤

👉 ኢትዮጵያ ቀደምት ሀገር በመሆኗ ይህንን ሉዓላዊነቷ ማንም ሊደፍረው እንደማይችል ማስገንዘብም ይገባል ብለዋል፤

ሙሉውን የፕሮፌሰሩን አርቲክል ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ያገኙታል