March 11, 2021

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ፦

የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ በዛሬው እለት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መገለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፦

– ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች 49 ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ውስደዋል።

– ምርጫ ምልከት ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች ውስጥ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል።

– 47ቱ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 8209 እጩዎች አስመዝግበዋል።

– ከፍተኛ እጩ ካስመዘገቡ ፓርቲዎች መካከል የመጀመሪያው ብልፅግና ፓርቲ ሲሆን 2,432 እጩዎች አስመዝግቧል ፣ 2ተኛ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1,385 እጩዎች አስመዝግቧል ፣ 3ተኛ ደግሞ እናት ፓርቲ ሲሆን 573 እጩዎች አስመዝግቧል።

– የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እጩዎቻቸውን ያላስመዘገቡ ፓርቲዎች ናቸው።

– በአጠቃላይ እጩ ካስመዘገቡት 47 ፓርቲዎች ውስጥ 4 ለክልል 2 ደግሞ ለፓርላማ የሚወዳደሩ ናቸው።

– 125 እጩ ተወዳዳሪዎች በግል ተመዝግበዋል።

– በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ችግሮች አጋጥመው ነበር ፤ ከ16 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታዎችን አቅርበው መፍትሄ ተሰጥቷቸዋል።

(Al AIN፣ Ethiopia Insider)

በመጪው ምርጫ ለመወዳደር ከስምንት ሺህ በላይ ዕጩዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

March 11, 2021 14

በግንቦት ወር መጨረሻ ለሚደረገው ሀገር አቀፍ ምርጫ በፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ 8,209 ዕጩዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ። ቦርዱ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 2 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው 125 የግል ተወዳዳሪዎችም በምርጫው ለመወዳደር በዕጩነት ተመዝግበዋል።  

የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቶች ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች መካከል 47ቱ ዕጩዎችን ማስመዝገባቸውን ቦርዱ በመግለጫው ጠቅሷል። አራት ፓርቲዎች ለክልል ምክር ቤት ብቻ የሚወዳደሩ ሲሆን ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ለተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ዕጩዎችን ያቀረቡ ናቸው ተብሏል። 

በምርጫው ከሚሳተፉ 47 ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ከፍተኛውን ዕጩ ያስመዘገበው ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ነው። ብልጽግና 2,432 ዕጩዎች ለውድድር አቅርቧል። በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ የዕጩዎች ቁጥር ያቀረበው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ደግሞ 1,385 ዕጩዎችን አስመዝግቧል። እናት ፓርቲ 573 ዕጩዎችን በማስመዘገብ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ለምርጫው የተመዘገቡ ዕጩዎች ቁጥር አሁን ይፋ ከተደረገው ሊቀንስም ሆነ ሊጨምር እንደሚችል የገለጸው ምርጫ ቦርድ፤ የዛሬው አሃዝ “ጊዜያዊ” መሆኑን አስገንዝቧል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)