March 12, 2021

“ልማቱ ይቅርና የሚታረዱ ህጻናትን እና አዛውንቶችን ብቻ ታደጉልን”(ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ)

ሊበቃ ይገባል። Stop the bleeding! Stop the bloodshed!! ይህ መረጃ እንደሚደርሳችሁ አውቃለሁ። የሚፈሰውን ደም ማቆም አለባችሁ። የሚታረዱትን ሰዎች ደም ማቆም ካልቻላችሁ አበባ ብትነሰንሱ ፣ ሽቶ ብታርከፈክፉ ጉዳያችን አይደለም። አይቻልም ልትሉ ትችላላችሁ። ሙስጠፌ ችሏል። በጣም ያስፈራ የነበረንን ዘመን አሳልፎናል። እናንተም ሌላውን ነገር ተውት ካስፈለገ። ልማቱም እድገቱም ይቅር። የሚታረዱትን አሮጊቶች አድኑ!! የሚታረዱ ህጻናትን አድኑ። This is your primary responsibility!

በጣም ደከመን ሰለቸን። ጨለማ ቀን፣ ሳምንት ፣ ወር ይሰለቻል። የወረዳ አስተዳዳሪዎች ቆማችሁ ገጀራ የምታቀብሉ እግዚአብሄር ይፈርድባችኃል፣ የትም አታመልጡ፣ ከሰው ብታመልጡም

ስለዚህ ይብቃን። ካስፈለገ ሌላውን ስራችሁን ተውትና አሮጊት እና ህጻናት የሚያርዱትን ሰዎች ያዙ።”

ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ