15 መጋቢት 2021

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ

NATIONAL ELECTION BOARD OF ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ስድስተኛ አገር አቀፍ ምርጫን ለማካሄድ ቀን ቆርጣ በዝግጅት ላይ ናት። በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ምርጫ ቦርድ በያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ተወዳዳሪዎችን የማስመዝገቢያ ጊዜ ተጠናቋል።

በ673 የምርጫ ክልሎች ላይ ለሚከናወነው ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ የቀረው ጊዜ 12 ሳምንታት ገደማ ነው።

ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቷን የመራው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በ1984 የብሔራዊ፣ ክልላዊ፣ የዞን እና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ተካሂዷል።

ይህም በሽግግር መንግሥቱ ለነበረው የተወካዮች ምክር ቤት አባልነት መንግሥት ምስረታ ሲሆን በወቅቱ የነበረው የብሔራዊ፣ ክልላዊና የወረዳ ምክር ቤት አባላት ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅም ምርጫውን አስተባብሯል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ መንግሥቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አገሪቷ በአጠቃላይ አምስት ጠቅላላ ምርጫዎችን አካሂዳለች። ከዚህም በተጨማሪ የማሟያና የአካባቢ ምርጫዎችን ጨምሮ ስድስት ሕዝበ ውሳኔዎች በአጠቃላይ 14 ምርጫዎች ተካሂደዋል።

ወደ ኋላ መለስ ብለን አገሪቱ ባደረገቻቸው አምስት ጠቅላላ ምርጫዎች ምን ያህል ሕዝብ መርጧል፣ የተወዳዳሪ ፓርቲዎች ብዛት፣ በምርጫዎቹስ ማን አሸነፈ የሚለውን ታሪካዊ ዳራ እንቃኛለን።

ምርጫ 2007

ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ለማካሄድ እየተዘጋጀችበት ካለው ምርጫ በፊት ያደረገችው የመጨረሻ ምርጫ ነው።

ምርጫ 2002

ታሪካዊ የሚባለውን ምርጫ 1997ን አልፎ የተደረገው የ2002 አራተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ የተከናወነው ግንቦት 15/2002 ነበር። ምርጫው በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተከናውኗል።

ምርጫ 1997

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የ1997 ዓ.ም ምርጫ እንደ ትልቅ ምዕራፍ የሚታይ ነበር።

የፖለቲካ ምሀዳሩ ከሌላው ጊዜ በተለየ ከፈት ማለቱና በተለያዩ የፖሊሲ አማራጮች ዙሪያ የተካሄዱት የጦፉ ክርክሮች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጣምረው ጥምረቶችን ፈጥረው መምጣትና የምርጫ ቅስቀሳዎች ሂደቱን አጓጊ አድርገውት ነበር።

ምርጫ 1992

ምርጫ 1987

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ