
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጰያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአሁኑ ሰአት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መግባቱን በመቃወምና በአገር ቤት እየተካሄደ ያለውን ስራ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፈ እያካሄዱ ናቸው።
ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ ሉአላዊነትን እንዲከበር፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በህወሓት ጥቅመኛች የውሸት ፕሮፖጋንዳ እንዳይታለሉ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።
እነዚህ ሰልፈኞች ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባችሌት ጄሪአ ደብዳቤ ጽፈዋል።
በዚህ ደብዳቤያቸውም ህወሓት ላለፉት ሶስት አስርት አመታት በኢትዮጵያ ላይ የፈጸማቸውን ግፎችና በደሎች ዘርዝረው አስረድተዋል።
ይህ ገዳይና ጨካኝ ያሉት የህወሓት አገዛዝ በህዝብ ትግልና ከፍተኛ መስዋዕትነት ከስልጣን ተወግዶ ቂም የዞ በትግራይ መሽጎ መቆየቱን በመጥቀስ፣ በምርጫ ስም የውሸት ምርጫ በማካሄድ የፌዴራል መንግስቱንን እንደማይቀበል አብሮም እንደማይሰራ ማወጁን፣ ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ሃይሌ ገብረሰላሴ የተካተተበት የአገር ሽማግሌዎች ቢላኩም በእንቢተኝነቱ መቀጠሉን፣ የሰላም እናቶች በሚል ወደ ትግራይ ተልከው የነበሩ እናቶችን ሳይቀር አቃሎ መመለሱን፣ ከዚህና ሌሎች መሰል ጥረቶች በኋላ ህወሓት በመከላካያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ደብዳቤው አብራርቷል። በሰራዊቱ ላይ የተፈጸሙ ግፎችንም ዘርዝሮ ገልጿል።
ለድርጅቱ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር የተጻፈው ደብዳቤ ህወሓት ባደራጃቸው ወጣቶች አማካኝነት በማይካድራ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋም አብራርቷል። ጭፈጨፋውን የፈጸሙት ወጣቶችና ታጣቂዎች ዛሬ በስደተኛ ስም በሱዳን መጠለያ ካምፖ ውስጥ እንደሚገኙም ገልጿል።
ህወሓት የወጠነው ሴራ ሁሉ ሲከሽፍበትና የፈጸመው ዘር ማጥፋት ወንጀል ሲጋለጥበት ራሱን ተበዳይ በማስመሰል በዓለም አቀፍ ደረጃ ባዘጋጃቸው ወዳጆቹ አማካኝነት የሀሰት ዘመቻ መክፈቱን የጠቀሰው ይሄው ደብዳቤ፤ በአምንስቲ ኢንተርናሽናል በኩል የምስራቅ አፍሪካ ተመራማሪ የሆነው ፍስሃ ተክሌ በተባለው ወዳጁ አማካኝነት፤ እንዲሁም የጨፍጫፊው ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በነበሩት በዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በኩል የተቀነባበረ ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑን አብራርቷል።
በትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ተፈጽሟል የሚለው ክስ ላይ የማጣራት ፍላጎት ካለው ቢሮው ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና መሰል ተቋማት ጋር የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት በማይጋፋ መልኩ እንዲያጣራ ነው ኢትዮጵያዊያኑ በደብዳቤያቸው የጠየቁት።
በተጨማሪም ኢትዮጵያና መንግስቷን እንደ አንድ አባል አገር ልትታገዝና ልትደገፍ ይገባታልም ሲሉ ነው የጠየቁት።
መንግስት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ በተነመለከተም ደብዳቤው ዘርዝሮ አስረድቷል።
∞ ∞To: Her Excellency Mrs. Michelle Bachelet Jeria ,
United Nations High Commissioner for Human Rights
Palais Wilson
52 rue des Pâquis
CH-1201 Geneva, Switzerland
(15, March 2021)
Dear Mrs, High Commissioner,
For the past three decades, we Ethiopians and Swiss citizens of Ethiopian origin were protesting in front of your office to condemn the human right abuses perpetrated by the now defunct TPLF regime and to demand justice for victims of the Tigray People Liberation Front (TPLF) brutal regime and the victims of countless ethnic conflicts that were deliberately fanned by the TPLF security apparatus with a purpose of dividing and ruling.
Your office has all our protest letters that we addressed to your predecessors enumerating genocides, massacres, extra judicial executions, random assassinations, forced disappearances, tortures etc. perpetrated by the TPLF brutal regime.
Thanks to the relentless fight and selfless sacrifice that our people paid, the brutal ethnic tyranny of TPLF is totally defeated and a new dawn is born through which we are hoping to see an elected government through a free and fair election in few months’ time.
With the hope of having sustainable peace and development and with well-rooted age-old wisdom, our people, instead of retribution and revenge, granted TPLF a total amnesty for their three decades of brutality.
Unfortunately, while Ethiopians were hoping that TPLF will use the amnesty and work for peace and development, they retreated to Tigray where they managed to subdue genuine popular grievances for four decades through harsh and militaristic control. They organized a huge military force that includes thousands of child soldiers that they trained and shamelessly paraded on each occasion to bully the federal government to accept their terms.
From their hideout in Tigray, they organized an illegal sham election and shamelessly proclaimed that they won all seats. They declared that they will no longer recognize the federal government and called for other opposition groups to do the same. They paraded tens of thousands of heavily armed troops and declared that they are ready for war.
Worried with this dangerous development, all the top religious leaders from all denominations together with traditional leaders and national figures like athlete Haile Gebresellasie headed for Tigray to beg the TPLF leadership to deescalate the venomous rhetoric and open a door for dialogue but TPLF chased them out on the same day and they returned heartbroken.