የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሴናተር ክሪስ ኮንስን ወደ ኢትዮጵያ መላካቸው ተሰማ።
Biden Dispatches Senate Ally to Ethiopia to Address Crisis
Chris Coons to deliver a tough message to Abiy Ahmed.
የደላዌር ሴናተር እና የቢደን የቅርብ አጋር የሆኑት ክሪስ ኮንስ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ለመገናኘት የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መንቀሳቀሳቸው ፎርይን ፖሊሲ የተሰኘው ድረገጽ ጽፏል።
ኮንስ ዛሬ ሐሙስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ የሚጠበቅ ሲሆን ፣ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኋይት ሀውስ ከፍተኛ ባለሥልጣን እንዳሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ እና ከአፍሪካ ህብረት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ ብለዋል።
ሴናተር ኮንስ ፎርይን ፖሊሲ ለተሰኘው ድረገጽ በሰጡት መግለጫ የአስተዳደሩን ሥጋቶች የትግራይ ሁኔታ መባባስ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥለዋል የሚለውን አባባል እንደሚጋሩ ገልጸዋል ፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋር ለመገናኘት እና የፕሬዚዳንቱን ጭንቀት ለማስተላለፍ በጉጉት እጠብቃለሁ ብለዋል ፡፡
ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ – https://foreignpolicy.com/2021/03/18/biden-chris-coons-senator-ethiopia-tigray-crisis/
Delaware Sen. Chris Coons visits Ethiopia