
አጣየ ይኸ ሁሉ ሲሆን የፌዴራል መንግስት የደህንነቱ መስሪያ ቤትም ሆነ የክልሉ የመረጃ ክትትል ክፍል ምን ሲሰሩ ነበር? – ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ
አጣየ አካባቢው ላይ ለተከሰተው ግጭት የአንድ ሰው በአልታወቁ ሰዎች መገደል ነው ” የሚለው ሀሳብ ብዙም አሳማኝ ሆኖ አላገኘሁትም። ምክንያቱም በየትኛውም ቦታ ግለሰብ ሊገደል ይችላል፣ ሆኖም በዚህ መልኩ የቡድን መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ምሽግ ይዘውና ተራሮችን ተቆጣጥረው ህዝብን ለመጨፍጨፍ እንቅስቃሴ የሚደረግበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ሰምተን አናውቅም።
በዚህ አካባቢ ከአመት በፊት ተመሳሳይ ደም አፋሳሽ ግጭት ተከስቶ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶ እንደነበረ ይታወቃል። ሰሞኑንም እንዲሁ፣ ይኸ ቡድን ከየት መጣ? በየት አድርጎ ወደ አካባቢው ደረሰ? ይኸ ሁሉ ሲሆን የፌዴራል መንግስት የደህንነቱ መስሪያ ቤትም ሆነ የክልሉ የመረጃ ክትትል ክፍል ምን ሲሰሩ ነበር? መረጃው ቀድሞ የደረሰው አካልስ ለምንድነው ፈጣን እርምጃ ያልወሰደው ወዘተ. የሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት ያለባቸው ይመስለኛል።
የሚያሳዝነው ነገር ከተሞችን የሚያጠቃና ዋና መንገድን ዘግቶ የጸጥታ ሀይል ወደ ቦታው ደርሶ እንዳያከሽፍ እስከማድረግ የሚደርስ የተቀናጀ እርምጃ የሚወስድ የታጠቀ ሀይል በአካባቢው እንዳሻው ሲፏልል መመልከት በእጅጉ ያማል። ካለፈው ስህተት ተምሮ የዚህ አይነት ሁኔታ እንዳይከሰት አለመስራት ደግሞ ልብን ይበልጥ ያደማል።