March 21, 2021

May be an image of 1 person

ብላቴን ጌታ ወልደማሪያም አየለ ዘመናዊ ትምህርትን ከቀሰሙ ቀደምት ኢትዮጵያዊያን አንዱ ነበሩ፤ ብላቴን ጌታ ወልደማሪያም አየለ በስዊዝ እና በፈረንሳይ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን ከ 10 አመት የአውሮፓ ቆይታ በሁዋላ ወደ ሀገራቸው ተመልስዋል።ብላቴን ጌታ ወልደማሪያም አየለ ከጠላት ወረራ በፊት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አንባሳደር ሆነው ተሾመው የስሩ ሲሆን የአገልግሎታቸውን ጊዜም ሲጨርሱ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል ፤ ብዙም ሳይቆይ ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በመውረሯ በኢጣልያ ወታደሮች ተይዘው ወደ አዚናራ እስር ቤት ተግዘው ለተወሰነ ጊዜ በእስር ቆይተዋል ።

ብላቴን ጌታ ወልደማሪያም ከነፃነት በሁላ በመኖሪያ ቤታችው በእንግሊዝ የአፍሪካ ወታደሮች ( Jambo) እንደተገደሉ ይታወሳል አሟሟታቸውን በአይኑ የተመለከተው ልጃቸው ፓስካል ወልደማሪያም “የሚሰማ ጆሮ ቢኖር ኖሮ “በሚለው መፅሀፋቸው ላይ ሁኔታውን እንደሚከተለው ይገልፀዋል.. .

May be an image of 2 people and people standing

” አንድ ቀን ከአባቴ ጋር በረንዳ ላይ ተቀምጠን ስንጫወት የግቢያችን በር በስርኣት ሳይንኳኳ መደብደብ ጀመረ፤ ከመክፈታችን በፊት ተስብሮ ኖሮ ጥቁር የእንግሊዝ የአፍሪካ ወታደሮች ( ጃምቦ የሚባሉት) ወደ ውስጥ ዘለቁ ፤ ጠመንጃቸውን ወደኛ እንደመቃጣት እያሉ አልፈው ወደ ትልቁ ቤታችን ገቡ፤ እቃውን ሁሉ እያተራመሱ ሲፈትሹ አባቴ ለማነጋገር ቢሞክሩም ዝም ብለዋቸው ቤታችንን በርብረው አንዳችም ነገር ሳይወስዱ ተመልሰው ሄዱ ። ቤታችን የተበረበረው ሀሙስ ቀን እንደነበር ትዝ ይለኛል ከ ሶስት ቀን በሁላ ስኛ ከቀኑ ሰባት ሰአት ላይ አንድ የእንግሊዝ ጥቁር ወታደር መጣ ፤ እኔና አባቴ አሁንም በረንዳው ላይ ነበርን ፤ ወታደሩ ጠመንጃውን ከትከሻው አውርዶ እያቀባበለ እኔና አባቴ ወዳለንበት በረንዳ መጣ ። መሳሪያውን ወደ አባቴ በማዞር አፈሙዙን ደቀነበት ። አባቴ ወታደሩን ቋንቋ እየለዋወጠ ለማናገር ሞከረ:: ወታደሩ ግን መልስ ሳይሰጥ ቀረ። በዚህ ጊዜ እኔ ” አባባ ይሄ ስውዬ ሊገልህ ነው” ብዬ ጮህኩ ” የለም አይገለኝም ይልቅ አንተ የክርስትና አባትህ ቤት ተጫወት ” አሉኝ ።ወዲያው ጆሮ የሚያደነቁር ተኩስ ተሰማ ። አባቴ ሽንጣቸው ላይ ተመትተው ከመውደቃቸው በፊት ሁለተኛ ጥይት ተተኩሶ ጭንቅላታቸውን ሲመታቸው መሬት ላይ ተደፋ” በማለት በእለቱ የተፈፀመውን ድርጊት በእዚህ መልኩ ፅፏል ።

እንደ ፓስካል ወልደማሪያም ገለፃ ከግድያው በሁላ 3 ኢትዮጵያዊያን መኮንኖች ቤታቸውን ለመፈተሽ ሞክረዋል በዚህ ድርጊታቸው ቤተስብ ምንድን ነው እምትፈልጉት ብለው ሲጠይቋቸው ” አንዳንድ ስነዶችና አባታችሁ ከኢትዮጵያ የተሽለሟቸው ኒሻኖች ለአይነት ስለሚፈለጉ ነው የሚል መልስ እንደሰጡ ልጃቸው ፓስካል ወልደማሪያም አየለ ይገልፃል ።

ብላታ ወልደማሪያም አየለ በእንግሊዝ መንግስት ወይንም በወቅቱ በነበረው መንግስት እንደተገደሉ እሙን ነው ሆኖም ግን ለምን ተገደሉ የሚለው ግን ዛሬም ድርስ ግልፅ አየደለም.. ….

‹የሚሰማ ጆሮ ቢኖር ኖሮ›› የተሰኘ መጽሐፍ ብላቴን ጌታ ወልደ ማሪያም ከልጅነት እስከ እውቀት ያሳለፉትን የትምህርት የስራ፣ የሃላፊነት፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ያከናወኗቸውን በርካታ አይነት የሕይወት ዘርፎች የሚተነትን ነው:: የመጽሐፉ አዘጋጅ ታሪካቸውን በጽሑፍ ከመግለጽ ባለፈም በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከዲፕሎማቶች፣ ከቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴና በተለያዩ አገራት የነበራቸውን የሥራ እንቅስቃሴ በፎቶ ለመግለጽ ሞክሯል፡፡