March 22, 2021 – Konjit Sitotaw

በትናትናው እለት በአሀዱ ሬድዮ ልሳነ ምርጫ 2013 በነበረው ፕሮግራም ላይ ባለፈው የመንግስት ስርዓት ጨቋኝ ናቸው የሚባል ቢሆንም በየወረዳው ፖሊስ ባልነበረበት ጊዜ ሰዎች ሰዓት እላፊ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው ይንቀሳቀሱ ነበር ያሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ናቸው፡፡–ዛሬ የሚታየው ነባራዊ ሁኔታ ግን ዜጎች ከ12 ሰዓት በኋላ ለመንቀሳቀስ ስጋት ውስጥ ገብተዋል ያሉት አቶ ቀጀላ በተለያየ መልኩ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡የመንግስት የጸጥታ ወይም የደህንነት ሀይሎች የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው ቢሆንም ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል፡፡–የጸጥታ አካላት ወንጀለኛውን ከመያዝና ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ሰላማዊውን ሰው ከቤት አስወጥቶ በመያዝ ግድያ እንደሚፈጽሙባቸውም ለግንባሩ መረጃ እንደሚደርስውም ተናግረዋል፡፡–አሀዱም ይህን ችግር እንዴት መቅረፍ ይቻላል ብሎ ለአቶ ቀጀላ ላነሳላቸው ጥያቄም መንግስት የጸጥታ ሀይሉን መዋቅሩንም በመፈተሸና በማስተካከል የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡–አሐዱ ራዲዮ 94.3