National Electoral Board of Ethiopia- NEBE -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አጭር መረጃ

በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት በትላንትናው እለት በተጻፈ ደብዳቤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአፋር እና በሶማሌ ክልላዊ መንግስታት መሀከል ላለው የአስተዳደር ወሰን አለመግባባት ብሎም በሁለቱ ማህበረሰቦች መሀከል በየወቅቱ ለሚያገረሽ ግጭት መነሻ በሆኑ ቀበሌዎች ስር የታቀፉ ጣቢያዎች ተከፍተው የምርጫ ሂደት እንዳይደረግባቸው የወሰነውን ውሳኔ በመቃወም እንደማይቀበለው በደብዳቤ ለቦርዱ ከማሳወቁም በላይ ቦርዱ “ውሳኔውን እንደገና አይቶ ካልለወጠም በምርጫው ለመሳተፍ እንቸገራለን” ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የደረሰውን ደብዳቤ በተመለከተ በዛሬው እለት የሚከተለውን ምላሽ ለክልል መስተዳድሩ መስጠቱን ያሳውቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ላነሳው ቅሬታ ምላሽ ሰጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ላነሳው ቅሬታ ምላሽ ሰጠ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ

መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

አዲስ አበባ ሸዋ

መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለምርጫቦርድ በደብዳቤ ለጻፈው ቅሬታ ምላሽ ተሰጥቷል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአፋር እና በሶማሌ ክልላዊ መንግስታት መካከል የአስተዳደር ወሰን አለመግባባት ባለባቸው አካባቢዎች ያቋቋማቸውን ከ30 በላይ የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎችን በአፋር ክልላዊ መንግስት ቅሬታ ምክንያት መሰረዙ ይታወቃል።

ምርጫ ለግጭት መንስኤ እንዳይሆን በሚል ጣቢያዎቹ እንዲዘጉና ተሳታፊዎችም በሌላ ቦታ እንዲመርጡ ይደረግ በሚል ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ የሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አልተቀበለውም።

ከፍ ሲልም ቦርዱ “ውሳኔውን እንደገና አይቶ ካልለወጠም በምርጫው ለመሳተፍ እንቸገራለን” ብሏል።

ቦርዱ ይህን ውሳኔ ከመስጠቱ በፊትም በፌዴራሉ የምርጫ ደህንነት ስራ ከታቀፉት የፌደራል ህግ አስፈፃሚ አካላት እገዛ እና ምክረ ሀሳብ መጠየቁንና የምርጫ ግጭትን ለመከላከል እንዲያስችለው ያደራጀው የግጭት ስጋት ካርታም ይህንኑ የሚሳይ ሆኖ ተገኝቷል ነው ያለው።

ስለሆነም የሶማሌ ክልላዊ መስተዳደር ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ቦርዱ ከዚህ እኳያ የሰጠው ውሳኔ የአፋር ክልልን ወይም የሶማሌ ክልልን የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የተሰጠ ውሳኔ እንዳልሆነ ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።

በመጨረሻም የምርጫ ተወዳዳሪዎች ፓርቲዎች እና እጩዎቻቸው እንጂ ክልላዊ መንግስታት እንዳልሆኑ እየታወቀ የሶማሌ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር በምርጫው ለመሳተፍ እንቸገራለን ሲሉ የገለፁት በህግ እይታ ምንም ትርጉም የማይሰጥ ሆኖ አግኝተነዋል ሲል ነው ቦርዱ የገለፀው።

በመሆኑም የሶማሊ ክልላዊ መንግስት ተቃውሞ ያቀረበበት የቦርዱ ውሳኔ የመራጮች እና የምርጫ ሂደትን በተለይም የምርጫ ሰላምን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ተረድቶ እንደ መንግስት አካል የምርጫ ህጉን ለማስተግባር ከቦርዱ ጋር ያለበትን የመተባበር ግዴታ በመወጣት እንዲቀጥል እንዲሁም በክልሉ የሚወዳደሩት ፓርቲዎችን ያለአድልዎ የሚያግዝ እስቻይ ሁኔታ እንዲፈጥር እናስገነዝባለን ሲል ቦርዱ በደብዳቤው ገልጧል።