
ፈረንሳይ ለሱዳን የሽግግር መንግሥት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ #ፓሪስ ላይ ጉባዔ አዘጋጅታ ነበር።
ጉባኤው ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተሳተፉበት ነው።
በዚሁ ጉባኤ ላይ የሱዳን ሉዓላዊ ም/ቤት ሊቀመንበር አብድል ፈተህ አል-ቡርሃን ከኢትዮጵያ ጋር ላለን ግንኙነት እና ትስስር በህዳሴ ግድብ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ያስፈልጋል ሲሉ መናገራቸውን አል ዓይን አስነብቧል።
አል-ቡርሃን በሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበር ጉደይ “ከኢትዮጵያ ጋር የመዋጋት ፍላጎት የለንም ፥ የጦርነት ሁኔታ የማይታሰብ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።
በኢትዮጵያ በኩል በፓሪሱ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተገኙ ሲሆን ንግግርም አድርገወል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ባደረጉት ንግግር ፥ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ስላለው ዘመናትን የተሻገረ እና በደም የተሳሰረ ወዳጅነት እና የሕዝቦች ትስስር አንስተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ግድቡ የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ኢትዮጵያ የዜጎቿን የኃይል ፍላጎት ከሟሟላት ባሻገር የቀጠናውን ሀገራትን ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ እየተገነባ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ከሱዳን ጋር በድንበር ጉዳይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች ሆነ ማንኛውም ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶች ሊፈቱ የሚገባው በውይይት እና በመርሕ ላይ ተመሥርቶ ሊሆን እንደሚገባው አፅዕኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
በፓሪሱ ጉባኤ ፥ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ እና የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ንግግር አድርገዋል።
መረጃው የተሰባሰበው ከአል-ዓይን እና ኢቲቪ ነው።