የአማራ ምሁራን መማክርት የአሜሪካ መንግሥት ያወጣውን መግለጫ ኢፍትሐዊ እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የሚጥስ ሲል ገልጾታል፡፡ መማክርቱ በመግለጫው አሸባሪው ትህነግ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አካባቢዎች ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ሲያካሂድ እንደነበር ጠቅሷል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ጄ ብሊንከን ሰሞኑን የተሰጠው መግለጫ ኢፍትሐዊና በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት እና ሉዓላዊነትን ያለመጣስ የተባበሩት መንግሥታት መርህን የሚቃረን ነው ብሏል፡፡

