አሻራ ሚዲያ 15/09/13/ዓ.ም ባህር ዳር ቀደም ሲል ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የ…
- Post published:May 23, 2021
አሁን የደረሰን መረጃ!! ተዘግቶ የነበረው የአባይ በረሀ መንገድ መከፈቱን አሻራ ሚዲያ ለማወቅ ችሏል
አሻራ ሚዲያ 15/09/13/ዓ.ም
ባህር ዳር ቀደም ሲል ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በትዕናንትናው ዕለት የኦሮሚያ ክልል የልዩ ሀይል አባላትና ታጣቂ ቡድኖች በአሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ የተዘጋው መንገድ የአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ባደረጉት እርብርብ መከፈቱን ከአሽከርካሪዎች እና ከተሳፋሪዎች አንደበት ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም ተሸከርካሪ ከአዲስ አበባም ወደ አማራ ክልል ከአማራ ክልልም ወደ አዲስ አበባ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከተሳፋሪዎችና ከጸጥታ ሀይሎች ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአባይ በረሃ እና በጎሃጽዮን አካባቢ ተደጋጋሚ ጥቃቶች ስለሚፈጸሙ የሚመለከተው ሁሉ እልባት ሊሰጠው እንደሚገባ አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡