Exclusive: Ethiopians suffer horrific burns in suspected white phosphorus attacks
Weapons experts said images obtained by the Telegraph show injuries consistent with the chemical
የቴሌግራፍ ሪፖርትና የመንግስት ምላሽ :
‘ቴሌግራፍ’ ጋዜጣ ባወጣው ሪፖርት በሰሜን ኢትዮጵያ (ትግራይ) የሚገኙ ሲቪሎች ከ ‘ነጭ ፎስፈረስ’ ጋር ተመሳሳይ የሆነ አሰቃቂ የቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸዋል፥ይህም የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል ብሏል።
Civilians in northern Ethiopia have suffered horrific burns consistent with the use of white phosphorus, a potential war crime, the Telegraph can disclose. Exclusive footage and accounts of witnesses and victims smuggled out of the war in Tigray suggests the Ethiopian and Eritrean armies may have used powerful incendiary weapons in civilian areas. Leading chemical weapons experts said the footage is consistent with white phosphorus, which is banned from use against human targets under international law.
ቴሌግራፍ ጋዜጣ ከትግራይ ተገኙ ባላቸው ምስክሮችን፣ ተጎጂዎች እና ልዩ ምስሎች የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦር በሲቪል አከባቢዎች ኃይለኛ የሆነና በከፍተኛ ሁኔታ የሚነድ መሳሪያ ተጠቅመው ሊሆን ይችላል ሲል ገልጿል።
አናገርኳቸው ያላቸው የኬሚካል የጦር መሣሪያ ባለሞያዎች ከትግራይ ተቀረፀው የወጡህ ምስሎች በዓለም አቀፍ ሕግ በሰው ዒላማዎች ላይ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከሚከለከለው ከ ‘ነጭ ፎስፈረስ’ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው ስለማለታቸው አስነብቧል።
ከተጎጂዎቹ መካከል በማዕከላዊ ትግራይ የ ‘አዲአይቆሮ’ መንደር ነዋሪ የሆነች የ13 ዓመት ታዳጊ ኪሳነት ገብረሚካኤል የምትገኝበት ሲሆን ሚያዚያ 20 ቤቷ ጥቃት ሲሰነዘርበት ከፍተኛ ቃጠሎ ደርሶባታል ብሏል።
ሌላኛው ተጎጂ፥በምስራቅ ትግራይ አዲዎልዎ መንደር ነዋሪ የሆነው የ18 ዓመት ወጣት የማነ ወልደሚካኤል ሲሆን እሱም በተመሳሳይ ከፍተኛ ቃጠሎ ደርሶበታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ‘የኬሚካል ጦር መሳሪያ’ አጠቃቀምን አስመልክቶ ‘ቴሌግራፍ’ ያወጣውን ዘገባ መመልከቱ ገልጿል።
የቀረበውን ክስም ውድቅ አድርጓል ። ኢትዮጵያ የታገዱ መሳሪያዎችን አልተጠቀመችም፤ በጭራሽ አትጠቀምም ብሏል።