በአማራ ክልል “ሰሜን ሸዋ ዞን” በቅርቡ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ አካባቢውን መልሶ ለማቋቋም በክልል ደረጃ የተዋቀረው የቴክኒክ ኮሚቴ የምልከታ ሪፖርቱን ለአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አቅርቦ ነበር።
በሪፖርቱ መሰረት ፦
– በሰሜን ሸዋ 3 ወረዳዎች ብቻ 281 ሰዎች ተገድለዋል።
– 197 ዜጎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
– 246 ሺህ 818 ሰዎች እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል ፤ 9,661 ዜጎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።
– በሸዋ ሮቢት፣ ቀወትና ኤፍራታ ግድም 4 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፤ 7 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ንብረታቸው ወድሟል።
– ሶስት የጤና ተቋማት ወድመዋል፤ አንድ ጤና ተቋም ተዘርፏል።
– 7 የእምነት ተቋማት ተቃጥለዋል።
– የውሃ መሰረተ ልማቶች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
– አስራ አንድ ሆቴሎች እና አርባ ዘጠኝ የግል መጋዘኖች ተቃጥለዋል።
– እንስሳት መዘረፋቸውና የግብርና መሰረተ ልማቶች ላይ የከፋ ጉዳት ደርሷል።
– የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋምና አካባቢውን መልሶ ለመገንባት ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል።
በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የደረሰውን ጉዳት የቴክኒክ ኮሚቴው እያጠናው የሚገኝ ሲሆን ባጭር ጊዜ ሪፖርቱን ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።