- Post published:May 26, 2021
የአሸባሪው ትሕነግ ታጣቂዎች እስካሁን በ46 የጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ላይ የግድያ፣የማቁሰልና የእገታ ወንጀል መፈጸማቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ግንቦት 18 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
በቅርቡ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ትሕነግ ባሰማራቸው ርዝራዥ ታጣቂዎቹ በኩል እስካሁን 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን መግደሉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ቡድኑ እስካሁን 20 የሚሆኑትን የአስተዳደሩ አባላትን አግቷል፤ 4 አባላትን ደግሞ ጉዳት ስላደረሰባቸው ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጧል።
በድምሩ 46 የጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ያጋራው መረጃ አመልክቷል።