ኢትዮጵያ ውስጥና በተለያዩ አገሮች ውስጥ አማራዎች ባደረጉት ትዕይንተ ህዝብና የተለያዩ የማሳወቅ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የነበሩት የዜና ማሰራጫዎች አሁን በአማራው ላይ የደረሰውን የዘር ማጥፋት፣ ማፈናቀል፣ ንብረት ማውደምና ማሰቃየት መዘገብ ጀምረዋል። አማራው ህዝብ ላይ በሀሰት በፈጠሩት ስር የሰደደ ጥላቻ ብልጽግና ፓርቲ፣ ህወሃትና ኦነግ የተናበበ በመሚመስል መልክ የሚያደርሱትን ጭፍጭፋ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳውቅ በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል ይኖርበታል። ይህንን እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙትን በአሜሪካና አውሮፓ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የአማራ ድርጅቶችና ስብብስቦችን ማህበረሰቡ እርዳታ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው እየተገለጸ ነው።
ፎክስ ኒውስ የተባለው ግዙፍ የአሜሪካ የሚዲያ ተቋም በአማራው ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ጭፍጨፋና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ያወጣውን ዘግባ ለክትትል እንዲረዳ እዚህ ላይ አቅርበንላችኋል። እዚህ ላይ ይጫኑ https://www.foxnews.com/politics/ethiopias-war-the-administration-will-not-mention