May 28, 2021


ሰሞኑን ጎንደር ከተማ እና አካባቢው ሰው በማገት ገንዘብ ሲሰበስብ፣ ጥይት እየተኮሰ ሕዝብ ለማሸበር ሲጥር የሰነበተ ኃይል ነበር። የዚህ አሸባሪ ኃይል ትንኮሳ፣ ግድያ፣ እገታ ትኩረት ተነፍጎት የቆየ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሕግ ማስከበር ስራ ተሰርቶ አካባቢውን ሰላም ማድረግ ተችሏል።

ዛሬ በተደረገ አሰሳ ከጎንደር ወጣ ብለው በተሰሩ ሕገወጥ ቤቶችና አካባቢው የዚህ የሽብር ቡድን በርከት ያለ አባል በቁጥጥር ስር ውሏል። ከዚህ ኃይል መካከል አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ ቀሪው በአካባቢው በማንነት ሰበብ ለትህነግ የሚላላክ ነው። ይህ ቡድን ዱቄት፣ ዘይት፣ ስኳርና ሌሎች ስንቆችን ከጎንደር ከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ ሕገወጥ ቤቶች አስጠግቶ፣ የሽብር ቡድን አባላቱን በሕገ ወጥ ቤቶቹ አስጠልሎ ተይዟል። በርካታ ጥይቶች፣ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳርያዎችም ተይዘውበታል።

የቡድኑ አባላት የጎንደር ከተማ፣ የጎንደር ዞኖች ወረዳዎችን የሀሰት መታወቂያ አሳትሞ በገፍ መያዙንም ታውቋል።–ሰሞኑን ጎንደርና አካባቢው ላይ ሽብር ለመፍጠር የሞከረው ኃይል ሰዎችን እያገተ በማንነት ስም ለትህነግ አሸባሪ ኃይል የሚላላክ ቡድን ዋነኛ መነሃሪያ የሆነች ሮቢት የተባለች ቦታ ከወሰደ በኋላ ገንዘብ ሲጠይቅ ሰንብቷል። መኪና እና ባጃጅ አናቆምም ያሉ የቅማንት ተወላጆችን ገድሏል።

በሰሞኑ መጠጊያ አንሆንም ያሉ የቅማንት ተወላጆች ላይ እርምጃ ወስዷል፣ ቤታቸውን አቃጥሏል፣ ሕግ የሚያስከብር ኃይል ሲገባ የቅማንት የገበሬዎችን ቤት እያቃጠለ ለመሸሽ ሞክሯል። ከአንድ ወር በፊት ከሱዳን የገባው የትህነግ ኃይል ጭልጋ አካባቢ መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈፀመ በኋላ እርምጃ እንደተወሰደበት ይታወሳል።

ይህ ኃይል ጥቃት እየፈፀመ ያለው በተቀናጀ መንገድ ነው። ባለፈው ጭልጋ ላይ ጥቃት ሲፈፀም፣ ከሚሴና ሌሎች አካባቢዎችም ጥቃቶች ነበሩ። የትህነግ ተላላኪ ኃይል ጎንደር አካባቢ ጥይት መተኮስ ቀናት ሌሎች ቦታዎችም የተቀናጁ ጥቃቶችን ለመፍጠር ተሞክሯል። ለአብነት ያህል ከሚሴ አካባቢ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ሲደርስ ሕግ ለማስከበር የጣረ የመከላከያ ሰራዊቱ ላይ የጥቃት ሙከራ ተደርጓል። በተመሳሳይ የአማራ ልዩ ኃይል ላይ ጥቃት ለማድረስ ጥረት ተደርጓል።

ከትናንት ጀምሮ ደራና አካባቢው የኦነግ ሸኔ ኃይል እንቅስቃሴ አለ ተብሏል። ጉራፈርዳ ላይ አማራዎች እንደ አዲስ ጥቃት ተከፍቶባቸዋል። እንቅስቃሴው የተራ ወንበዴዎች እንቅስቃሴ አይደለም። ምርጫው ሲደርስ ይጠናከራል። የግድቡ ሙሊት ሰሞን ከትህነግ ብቻ ሳይሆን እንደ ግብፅ ካሉ ላኪዎቻቸው የተሰጣቸውን የቤት ስራ ለመወጣት ብዙ ይደክማሉ።

ከጎንደር ወጣ ብለው በርካታ ሕገወጥ ቤቶች እየተሰሩ ዝም ተብለዋል። እነዚህ ቤቶች የአሸባሪ ምሽግ ሆነው ተገኝተዋል። እነዚህ ቤቶች የትህነግ ተላላኪ ኃይል ጎንደርን ለማጥቃት እንደምሽግ ያስገነባቸው ናቸው። አስጠልለው የተገኙት የኪስ ሌባ አይደለም። አሸባሪ ነው። ያውም ከውጭ ሀገር የሰለጠነ።

በእነዚህ አካባቢዎች ላይ የከተማ አስተዳደሩ በፈዛዛነቱ የሚቀጥል ከሆነ ሕዝብ ጥያቄ ማንሳት አለበት። የአማራ ፀጥታ ኃይል፣ መከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ለሚፈፅሙበት አካላት መጠለያ የሆነን መንደርና ቤቶች ጉዳይ ዝም ብሎ ማየት የለበትም። መመቻ ምሽጎችን ዝም ማለት የለባቸውም።

Source –  Getachew Shiferaw