28/05/2021

ቅዱስ ሲኖዶስ ትልልቅ ውሳኔዎችን አሳለፈ!

አባይ ነህ ካሴ

የሚከተሉት ውሣኔዎቹ ይጠቀሳሉ

፩. የቅብዓት ጳጳሳት ነን ያሉትን አወገዘ

፪. አቡነ ማርቆስን በማንሣት አቡነ ያሬድን የምሥራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ አድርጎ ሾመ። ከዘር አመዳደብ የጸዳ ግሩም ውሣኔ።

፫. መንግሥት በመስቀል ዐደባባይ እና ጃን ሜዳ በተቀሩት የዐደባባይ በዓላት ማክበሪያዎቻችን ላይ ካሳየው ዳተኝነት እንዲነቃ፣ መዳፈሩን እንዲያቆም በታላቅ ቁጣ አስጠነቀቀ፣ አፋጣኝ ውሣኔም እንዲሰጥ አሳሰበ።

፬. በእምነት ተቋም ስም የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ማንነት የተዳፈረ የይዞታን ስም በመለወጥ የተደረገው ጽርፈት በአስቸኳይ እንዲታረም አስጠነቀቀ።

፭. የዐዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስን የቆይታ ጊዜ ገደበ። እስከ ጥቅምት ብቻ ይቆያሉ።

፮. ከዐዲስ አበባ ሀ/ስብከት ኃላፊዎች የፈጸሙትን ኢቀኖናዊ ነውር አወገዘ። በቋሚ ሲኖዶሱ በኩል ጉዳያቸው ታይቶ ከኃላፊነታቸው እንዲነሡ አቅጣጫ አስቀመጠ።

፯. የፖትርያርኩን የጉባኤ መክፈቻ ቃል ሙሉ በሙሉ አጸደቀ።

የዘንዶው አፎች አሰፍስፈው ነበረ። መንፈስ ቅዱስ ዘጋው። ታሪክ ተሠራ። ሲኖዶሳዊ አንድነት ቀጠለ። ይደመሙበታል እንጅ ሌላ ምን ይባላል? ቡራኬአችሁ ይድረሰን!

ለዝርዝሩ :-  https://youtu.be/gGYVkrQ9E3M