29 ግንቦት 2021

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አንድ የራያንኤር አውሮፕላን ወደ ቤላሩስ ዋና ከተማ እንዲያመራ ተገዶ አንድ ተቃዋሚ እና የሴት ጓደኛው በመያዛቸው ምዕራባውያን ያሰሙትን ቁጣ ውድቅ አደረጉ፡፡
በሩሲያ የመዝናኛ ከተማ ሶቺ ባደረጉት ውይይት ፑቲን እና የቤላሩስ አቻቸው አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ስለ “ስሜታዊ መገንፈል” ተናግረዋል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት ይህን ተከትሎ መቀመጫቸውን አውሮፓ ያደረጉ አየር መንገዶች የቤላሩስን አየር ክልል እንዳይጠቀሙ አሳስቧል፡፡
ጋዜጠኛው ሮማን ፕሮታሴቪች እና ሴት ጓደኛው ሶፊያ ሳፔጋ እንዲለቀቁም ጠይቀዋል፡፡
- ጀርመን ናሚቢያን ቅኝ በገዛችበት ወቅት የዘር ጭፍጨፋ ማካሄዷን አመነች
- ተቃዋሚዎች “ቧልት” ባሉት ምርጫ የሶሪያው ባሻር አል አሳድ አሸነፉ
- ናይኪ ከኔይማር ጋር የተለያየው ከወሲባዊ ጥቃት ምርመራ ጋር በተያያዘ ነው አለ
ባለፈው እሁድ ጥንዶቹ ከአቴንስ ወደ የአውሮፓ ሕብረት ዋና ከተማ ቪልኒየስ ሲበሩ ነበር አንድ ተዋጊ ጄት የቦንብ አደጋ መኖሩን አሳውቆ አውሮፕላኑን በማጀብ ሚንስክ አየር ማረፊያ እንዲያርፉ ያደረገው። በኋላ ላይ ቦንብ አደጋው ውሸት ሆኖ ተገኝቷል።
የተባበሩት መንግሥታት ሲቪል አቪዬሽን ኤጀንሲ የቤላሩስ ድርጊት ዓለም አቀፉን የአቪዬሽን ሕግ ስለመጣሱ “የሚያጣራ” ምርመራ እጀምራለሁ ብሏል፡፡
የአውሮፓ ሕብረት አየር መንገዶች የቤላሩስ አየር ክልልን እንዳይጠቀሙ ጥሪ ካደረገ በኋላ ሩሲያ ወደ ሞስኮ የሚጓዙትን የኤይር ፍራንስ እና የኦስትሪያ አየር መንገድ በረራዎች አግዳለች።
ፑቲቲን እና ሉካሼንኮ ምዕራባውያንን በምን ከሰሱ?
ምንም እንኳን ለረዥም ጊዜ ፕሬዚዳንት በመሆን የቆዩት መሪዎች መካከል ያለው የግል ግንኙነት አንዳንድ ጊዜ የተበላሸ ነው ቢባልም ሩሲያ የቤላሩሱ መሪ ጠንካራ የፖለቲካ አጋር ነች፡፡
ፑቲን የአውሮፓ ሕብረት በባለ ሁለት ስለት ቢላ እየበላ ነው ሲሉ ይከሳሉ። ምክንያቱ ደግሞ ኤድዋርድ ስኖውደን በሩሲያ ጥገኝነት መጠየቁን ተከትሎ እአአ በ2013 የቦሊቪያው ፕሬዝዳንት ኢቮ ሞራሌስን የያዘው አውሮፕላን ከሞስኮ በመነሳት በተለያዩ የጎረቤት አገራት ለማረፈፍ ቢሞክርም አገራቱ ፈቃደኛ አልሆኑም።
ፑቲን አክለውም በወቅቱ የቦሊቪያውን መሪ የያዘው አውሮፕላን ወደ ቪየና አውሮፕላን ማረፊያ አንዲዞር ሲገደድ የአውሮፓ ሕብረት “ዝምታን መርጦ ነበር” ብለዋል፡፡
የቤላሩሱ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ምዕራባውያኑ በአገራቸው አዲስ ብጥብጥ ለመቀስቀስ እየፈለጉ እንደሆነ ለፑቲን ተናግረዋል፡፡
“ጀልባው ያለፈው ነሐሴ የነበረበት ደረጃ ለማድረስ ሙከራ እየተደረገ ነው” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ከአገሪቱ አወዛጋቢ ምርጫ በኋላ አገዛዙን በመቃወም የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችን አጣቅሰው ገልጸዋል፡፡
ፑቲን በሩሲያ እና ቤላሩስ መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት አድንቀዋል፡፡
የሰሞኑ ቀውስ ለምን ተፈጠረ?
እሁድ ዕለት ራያንኤር በረራ ቁጥር 4978 ከአቴንስ ወደ ቪልኒየስ ሲጓዝ ተገዶ ሚኒስክ አርፏል፡፡
የቤላሩስ ባለሥልጣናት የቦምብ ጥቃት አለ የሚል መልዕከት በስዊዘርላንድ በኩል ደርሶናል ብለዋል። የስዊዘርላንድ የኢሜል አቅራቢ ፕሮቶን ሜይል በበኩሉ አውሮፕላኑ አቅጣጫ ከተቀየረ በኋላ ነው መልዕክቱ የተላከው ይላል፡፡
የ26 ዓመቱ ፕሮታሴቪች እና የሴት ጓደኛው የ23 ዓመቷ ሳፔጋ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው ነበር፡፡ ተሳፋሪዎች ከአውሮፕላኑ ሲወርዱም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ፕሮታሴቪች የስመ ገናናው የቴሌግራም ቻናል ኔክስታ የቀድሞ አዘጋጅ ነው፡፡ በ2019 ከቤላሩስ ወደ ሊትዌኒያ አቅንቶ በስደት ይኖራል፡፡
ኔክስታ እአአ ነሐሴ 2020 በቤላሩስ የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በመቃወም ሰልፈኞችን በማነሳሳት ወሳኝ የነበረ ሲሆን ምርጫው ስለመጭበርበሩም በሰፊው ዘግቧል።
ፕሮታሴቪች ባለፈው ዓመት በቤላሩስ የሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ሲሆን ከባድ ክሶችም ይጠብቁታል፡፡
ሮማን ፕሮታሴቪች ማነው?
ፕሮታሴቪች ጠበቃው ኢንሳ አሌንስካያን ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሙስ ዕለት ማየት ችሏል፡፡ “ደህና ነው። ብርቱ፣ ቀና እና ደስተኛ ነው። ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም” ስትል ጠበቃው ተደምጣለች፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳስታወቁት ሳፔጋ እአአ በነሐሴ እና በመስከረም 2020 ወር የቤላሩስ ሕግን ጥሳለች በሚል ተከሳለች፡፡
ጥንዶቹ ስለ ሞት ወንጀል ሲናዘዙ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ቢለቀቁም በግዳጅ እየተናገሩ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል፡፡
መያዛቸው እና አውሮፕላኑ በግዳጅ ማረፉ ዓለም አቀፍ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡
“ድርጊቱ ድጋሚ እንዳይከሰት እርምጃዎች ሊኖሩን ይገባል” ሲሉ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር ኃላፊ ዊሊ ዋልሽ ለሮይተርስ የዜና ወኪል አስታውቀዋል፡፡