May 31, 2021


ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ; ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ; አቶ ከተማ ይፍሩ እና ዶ/ር ምናሴ ሃይሌ

በመኮንን ከተማ ይፍሩ

ለአንድ የሀገር መሪ ከበስተጀርባው ያሉት ባለስልጣናት የሥራ ብቃት አመራሩ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ይኖረዋል። በተለይ በአንድ ደሃ ሀገር ላይ የበለጠ ተፅእኖ ይኖረዋል። ብዙ ችግሮች ባሉበትና መፍተሄ በሚያስፈልግበት ስዓት ከማንኛውም ነገር በላይ ብቃት ወሳኝ ነዉ። መሪ አንድ ነዉ እና ሁሉም ቦታ ለመሆን ስለማይችል በየስራ ዘርፉ ብቁ የሆኑ ባለስልጣናትን ማስቀመጥ ይኖርበታል።

በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን እንደ ምሳሌ የውጭ ጉዳይን እንውሰድ። ንጉሡ የሾሟቸው ሚንስትሮች እነማን ነበሩ ብለን ብንጠይቅ ብቃት እና ልምድ የነበራቸውና ችሎታቸውን በስራ ያስመሰከሩ ዲፕሎማቶች ነበሩ ብለን መመለስ እንችላለን። ንጉሡ እነ ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድን (1943–1958); አቶ ይልማ ደሬሳን (1958–1960); አቶ ከተማ ይፍሩንና (1961–1971); ዶ/ር ምናሴ ሃይሌን (1971–1974) ይዘው ነበረ የተራመዱት። ከጠቀስኳቸው ስዎች ጋር ሲራመዱ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ አይሆንም።

ንጉሡ የተወለዱት በፈረንጆች አቆጣጠር በ1892 ነበረ። የፊውዳል ዘመን በሚባለው ጊዜ መሆኑ ነዉ። ታሪካችንን ባናውቀው ኖሮ በዛን ጊዜ የተወልደ መሪ ወይ ልጆቹን ባይሆን ዘመድ ወዳጆቹን በየቦታው ይሾማል ብለን ነበረ ምናስበው። ለምን ይገርመናል አረብ ሀገር ያሉት ነገስታትን ብናይ ሹመት ከቤተሰብ አምልጣ አትወጣም።

ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴን ከሁሉም መሪዎች የሚለያቸው ይሄ ነበረ። በዚህ ፎቶግራፍ እንደምናየው ለአንድ የሀገር መሪ ከበስተጀርባው ያሉት ባለስልጣናት የሥራ ብቃት አመራሩ ላይ ትልቅ ተፅእኖ እንደሚኖረው የገባቸው ታላቅ መሪ ነበሩ። እሳቸው ብቃትን ዋናው የሹመት መስፈርት አርገው ስላስቀመጡት እነ ፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉን የመሰሉ ታላቅ መሪዎችን ኢትዮጵያ ልታፈራ ችላለች። ለዢህም መመስገን አለባቸው።

ታሪክን ማንበብና ማወቅ ጥሩ ነዉ። ከሁሉም በላይ ግን ልንማርበት ይገባል።  Makonnen KetemaMay be an image of 1 person, beard and suit

Makonnen Ketema