

ግብፅና ኬንያ በወታደሪያዊ ቴክኒካል ጉዳዮች ላይ አብሮ መስራት የሚያስችል ስምምነት በትላንትናው ዕለት ተፈራረሙ ።
የአባይ ግድብ ግንባታ ወደ መጨረሻ ምዕራፍ መድረሱ እረፍት የነሳት ግብፅ ትናንት ከኬንያ ጋር በወታደሪያዊ ቴክኒካል ጉዳዮች ጋር ለመስራት መስማማቷን ገልፃለች።
የግብፅ መከላከያ ዋና አዛዥ ሞሓመድ ፋሪድ ናይሮቢ ተገኝተው ከኬንያው መከላከያ ሚኒስትር ሞኒካ ጁማ ጋር ሁለቱ ሀገሮች ወታደሪያዊ አቅምን በማሳደግ እና ስልጠና በመስጠት ላይ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አርገዋል ሲሉ የግብፅ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ሁለቱም ሃገራት በጋራ ፍላጎታቸው እና በሀገራዊ ደህንነት ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመከላከል ረገድ የሁለቱን ወገኖች አቅም በሚያጠናክር መንገድ በስልጠና ፣ በልምድ ሽግግር እና በወታደራዊ አቅም ግንባታ ላይ ትብብርን ማጎልበት ላይ ትኩረት የደርጋል ይላል ዘገባው፡፡
ሁለቱም መሪዎች በተጨማሪ ድንበር ተሻጋሪ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ደረጃዎች ላይ በሁለቱም ሀገሮች ብሔራዊ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ የጋራ ተግዳሮቶች እና እድገቶች ላይ ተወያይተዋል ፡፡
የግብፅ መከላከያ ዋና አዛዥ ጀነራል መሓመድ ፈሪደ ከሩዋንዳ መከላከያ ሚኒስትር አልበርት ሙራሲራ ጋር ለመወያየት ወደ ሩዋንዳ አቅንተዋል፡፡
አውሎ ሚድያ ግንቦት 23 / 2013 ዓ.ም