አህመድ የፌደራል መንግሥት ወታደሮቹን ከመቀለ ያስወጣው ተሸንፎ አይደለም አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ትናንትና ሰኔ 22/2013 .ም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለጋዜጠኞች ባደረጉት ገለጻ ነው።

የፌደራል መንግሥት ከትግራይ ክልል ወታደሮቹን ማስወጣቱንና የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን እንዲሁም የትግራይ ኃይሎች መቀለን ጨምሮ አንዳንድ ከተሞችን መቆጣጠራቸው ተዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባደረጉት ንግግር ጦሩ የወጣው በሽንፈት ሳይሆን ኦፕሬሽኑ (ዘመቻው) በመሳካቱ ነውብለዋል።

አሁን የተካሄደው ኦፕሬሽን (ዘመቻ) ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተሳክቷል፤ የምንፈልገውን ሠራዊታችንን አስወጥተናል። ይህም ሌሎች ኃይሎች የሚያስቡት ነገር ካለ ለመዘጋጀት ሰፊ ዕድል አግኝተንበታልሲሉ ተናግረዋል።

ህወሓት በበከኩሉ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ ባወጣው መግለጫ የትግራይ ክልል አስተዳደር በሚል ሲሆን አስደናቂ ድልተገኝቷል ብሏል።

መቀለም በትግራይ መከላከያ ኃይል በሙሉ ቁጥጥር ስር ናትብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው የጁንታው ኃይል መቀለ አልደረሰምብለዋል።

እሳቸው እንደሚሉም ህወሓት ሳይሆን ወደ መቀለ የገባው በአካባቢው የነበረና ጠመንጃውን የደበቀና ጊዜ የሚጠብቅ ኃይል ነው ብለውታል።

እኛ ስንዴ እንየሰጠን እኛ ዞር ስንል የሚጨፍር ከሆነ የጥሞና ጊዜ ያስፈልገዋል ማለት ነውሲሉ ተናግረዋል።

በመቀለ ስለነበረው ጦር ብዛት ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 20 ሺህ ያህል ነው ያሉ ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ ጦሩ ከትግራይ ክልል ሲወጣ የጦር መሳሪያ አስወጥቷል ብለዋል።

በክልሉ ውስጥ ሠራዊቱ ለምን እንደገባና በአሁኑ ወቅትም ለምን እንደወጣ በዚሁ ወቅት አስረድተዋል።

ሠራዊታቸው ወደ ትግራይ ከዘመተ በኋላ የመቆየት አላማ እንዳልነበረው የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ሌላ የሚያሰጋን ኃይል ስላለ ወደእሱ መዞር ያስፈልገን ነበር፤ ይህ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነውሲሉም ጠቅሰዋል።

ይህ ያሰጋል ያሉት ኃይል ማን እንደሆነ በዚህ ወቅት አልጠቀሱም።

በተለይም በባለፉት ሳምንታት ጦርነቱ አቅጣጫውን እንደቀየረ በተናገሩበት በዚህ መግለጫ የክልሉ ሕዝብ በጦርነቱ ተሳትፏል በማለት አስረድተዋል።

አሁን ያለብንን ስጋት ትተን እዚያ ብንጋጋጥ ሁለቱንም ያጣ ከመሆን ያለፈ ጥቅም አይገኝበትም፤ ምክንያቱም መሰላቸት፣ መዳከም ውስጥ ገብተናል። መጀመሪያ የገጠመንን ጦር ከ15 እስከ 20 ቀን ነው የፈጀብን፤ ቀጥሎ የሽፍታ ባህርይ ያለው ተዋጊ ገጥሞን ነበር እሱም ያን ያክል አልከበደንም፤ ይህ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ስለሚስችልብለዋል።

በተጨማሪ አሁን ያለው ጦርነት ይለያልያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ ባለፉት 20 ቀናት ሕዝቡ ራሱ ወታደሩን ማጥቃት ጀምሯልብለዋል።

አክለውም ወታደሩ ከመቀለ ባይወጣ ኖሮ የዚህ ቤት ድንጋጤ የተገለበጠ ይሆናል። ቄሶች የድምጽ ማጉያ እና ጠመንጃ ይዘው ታይታዋል፤ በመቃብር ስፍራዎች ትጥቅ ተቀብሯልብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ መቀለ አሁን በወታደራዊ ዕይታ ምንም የሚያጓጓ አይደለም። ቀድሞውኑም ወታደሮቻችን ተመቱ ብለን እንጂ መቀለን ነጻ እናውጣ ብለን አልነበረም የሄድነውሲሉም ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሉት ከመቀለ ሠራዊቱ መውጣቱን ተከትሎ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አማራ ተካደየሚሉ ሃሳቦች መንሸራሸራቸውን አንስተው ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል።

አማራ ከትግራይ ከሱዳንና ከሌላውም ክፍል ከፍቅር ውጪ፤ በኃይል ማንበርከክ ለሚፈልገው ራሱን መከላከል የሚችል ሕዝብ ነውብለዋል።

ከሰሞኑ ከመቀለ ውጭ በህወሓትና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጊያዎች እንደነበሩ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ዘገባው እንዳስነበበው ሰኞ እለት ባልተጠበቀ ሁኔታ የትግራይ ኃይሎች ክልሉን የተቆጣጠሩ ሲሆን ይህም በባለፈው ወራት የነበረው ጦርነት ሁኔታዎችን ይቀይራል ብሏል።

ይህንንም አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተቀበሉት ሲሆን ጠላት ተሸንፎ አያውቅም፤ በየቀኑ ይደመስሱናል፤ በየቀኑ ነው የምንሸነፈው በፌስቡክና በትዊተርሲሉ ተናግረዋል።

የህወሓት አላማ ማሸነፍ ሳይሆን አመድ ሆኛለሁና ተያይዘንና አመድ እንሁን፤ ተከስክሻለሁና አብረን እንከስከስዓይነት አላማ ነው ያላቸውብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በስምንት ወራት ውስጥ ጦርነት በተካሄደባት ትግራይ በርካታ ወታደሮች እና ሲቪሎች መገደላቸውን መንግሥት ያስታወቀ ሲሆን በዚሁ ወቅትም በክልሉ ስለወጣውም 100 ቢሊዮን ብር ወጪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ወጪው ከወታደራዊ መልክ ካለው ወጪ በተጨማሪ ለመንገድ፣ ለመብራት፣ ለትምህርትና ለጤና መዋሉን አስረድተዋል።

ይህንንም ወጪ ከክልሉ በጀት እንዲሁም ከአገሪቱ በጀትም ጋር ያነፃፀሩት ሲሆን ይህም በዘንድሮ የሚያዘው በጀት 20 በመቶ እንዲሁም ከትግራይ ዓመታዊ በጀት 13 እጥፍ በላይ ነው በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመብራት ጥገና፣ በእርዳታ አቅርቦትና በሌሎች ሥራዎች ላይ እያሉ ሰዎች ተገድለዋል። ግን አንድም ሰው ጥሩ ሰራችሁ ያለን የለም ክሶች ብቻ ነበር ሲቀርቡ የነበሩትሲሉም መገናኛ ብዙኃንን ኮንነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናውም እለት መንግሥታቸው በሰብዓዊ እርዳታ እንዲሁም በመሰረተ ልማት ጥገና ባካሄዱበት ወቅት የተለያዩ ሰዎች ተጎድተዋል እንዲሁም ሞተዋል ብለዋል። መንግሥታቸው ጥሩ ሥራ ቢሰራም ከወቀሳ እንዳልዳነም ሲሉ አስረድተዋል።

አንድም ሰው በርቱ ጥሩ ሥራ እሰየራችሁ ነው ቀጥሉ የሚልን ሰው አልገጠመንም፣ ይልቁኑም በእናንተ ምክንያት ረሃብ ሊመጣ ነው፣ ውጊያ አላቆማችሁም፣ ለኤርትራ ሠራዊት ፈቀዳችሁ ብሎም ፍቃድ ከለከላችሁ የሚል ነበርሲሉ ገልፀዋል።

የተለያዩ ተቋማት በበኩላቸው ጦርነቱ ክልሉን ከፍተኛ ወደ ሆነ ሰብዓዊ ቀውስ ከትቶታል ይላሉ።

በክልሉ አምስት ሚሊዮን ያህል ነዋሪዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መሰረት 350 ሺህ ሕዝብ የሚሆነው በረሃብ ቋፍ ላይ ነው።

ከዚህ ቀደምም ረሃብ አለ የሚለውን የተለያዩ ተቋማት መግለጫ መንግሥት እንደማይቀበለው ያስታወቀ ሲሆን በክልሉም ረሃብ እንደሌለና እርዳታም እየተከፋፈለ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጿል።

በክልሉ ወስጥ ህወሓት በደርግ ወቅት እንዳደረገው በስንቅ እና ትጥቅ ራሱን ማደራጀቱን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ሁኔታ በዚሁ አጋጣሚ መታየቱንም ገልፀዋል።

ነዋሪው አምስት ቤተሰብ ቢኖረው 10 አለኝ ብሎ በማስመዝገብ ግማሹን ለጁንታው ይሰጣል። ረዘም ያለ ጊዜ በፈጁ ጦርነቶች ወቅት መከላከያ ውሃ ይከላከላል፣ ጁንታው ሃይላንድ እና የስ ያገኛልይላሉ።

ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሉት ወታደሩ ጠላትብለው በጠሩት ኃይል ብቻ ሳይሆን የክልሉም ሕዝብ ሠራዊቱን እንዳጠቃ አስረድተዋል።

ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ወታደሩ ሲሄድ ጠላት ሳይሆን ሕዝብ ያያል ያሉት ዐቢይ አነስተኛ ወታደር ያነሰ ሲሆን ከኋላ በርከት ያሉ ሰዎች ወረውት በክላሽም በገጀራም ይጨፈጭፉታል፡በማለት ተከላከሉን ያሉ ሰዎችም ሠራዊቱን አጥቅተዋል በማለት ተናግረዋል።

አንድ መንደር ላይ ጁንታው አልደገፋችሁኝም በሚል ሰዎች ይረሽናል። እየረሸኑን ነው ጥበቃ አታደርጉልንም ብለው ጠየቁ ወታደሩን። በዚያ መንደር መካለከያ በቁጥር ከ20 የማበልጡ ሰዎችን አስቀምጦ ሄደ። ጠዋት ጠብቁን እንዳትሄዱብን ያሉን ሰዎች ከሰአት ወጥተው እዚያን ወታደሮች ፈጇቸውብለዋል።

ይህንንም ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለሳምንታት ውይይት ከተረገ በኋላ ውሳኔ ላይ ተደርሷል ብለዋል።

በተለይም ባለፉት ሦስት ሳምንታት ሕዝቡ በመሳተፉ ሕዝብ ላይ አልተኩስም ብለው ራሳቸውን ያጠፉ አሉ፤ ጥይት ጨርሰው የተገደሉ እና የተያዙም ወታደሮች ነበሩብለዋል።

እኛ የወሰነው የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕዝብን እንደጠላት ወስዶ፣ በታሪክ ውስጥ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ፣ እሱም የሚሸማቀቅበት ዓለምም ኢትዮጵያ ላይ የሚነሳበት ነገር ከሚፈጠር ደጀን ወደሚለው ሕዝብ ጠጋ ብለን፤ በምርጫው የጥሞና ጊዜ እንደተባለው ለሕዝቡ ይህንን የጥሞና ጊዜ እንስጠው ብለን ነው። ሳምንታትን ወይም አንድ ሁለት ወር ስንሰጠው እናየዋለን የመንግሥትን እና የመከላከያን ጥረት በብዙ እጅ መረዳት ሲጀምርሲሉ ተናግረዋል።

ተመድን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በበኩላቸው በክልሉ ውስጥ በወታደሮች ንፁሃን ዜጎች እንደተጨፈጨፉ እንዲሁም ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀማቸውን ይከሳሉ።

የተመድ የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በቅርቡ ለፀጥታው ምክር ቤት ዝግ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት

ሴቶችንና ታዳጊዎችን በተቀናጀ ሁኔታ በመድፈር ለማሸበርና ለማሰቃየት እየተጠቀሙበት ነው። የኤርትራ ወታደሮች ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀሙበት ነው። የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎች ይከበባሉ፣ ይደበደባሉ እንዲሁም ማስፈራሪያዎች ይደርሳቸዋልብለዋል።

ከሰሞኑ የመንግሥት ተናጠል የተኩስ አቁምን ተከትሎም የህወሓት ቃለ አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ በሰጡት መግለጫ ቀልድእንደሆነም ተናግረው ትግራይ ከወራሪ ኃይሎች ነፃ እስክትሆን ድረስውጊያው እንደማያቆም አስረድተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው ቦታዎቹን ባይጠቅሱም ሠራዊቱ ይዟቸው የሚቆዩ ቦታዎች እንዳሉ እና ወደዚያ የሚመጣ ኃይል ካለም አስፈላጊውን ዝግጅት እንደተደረገ ጠቁመዋል።

ቢቢሲ