https://www.ethiopianreporter.com/sites/default/files/inline-images/metropolitan_0.gif

የፀጥታው ምክር ቤት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ  ስብሰባ ሊያካሂድ መሆኑ ተጠቆመ
በተመድ የፈረንሣይ አምባሳደር ነኮላስ ዴ ሪቪዬር

ፖለቲካ

4 July 2021

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት ከታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ስብሰባ ሊያደርግ እንደሚችል ተነገረ፡፡ ምክር ቤቱ ተሰብስቦ ቢወያይም ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ የገጠማቸውን አለመግባባት በውይይት ወይም ወደ ድርድር እንዲመለሱ ከማበረታት ውጪ፣ ሊያደርግ የሚችለው ነገር እንደሌለ ተጠቁሟል፡፡

የምክር ቤቱ የወቅቱ ሰብሳቢ በተመድ የፈረንሣይ አምባሳደር ነኮላስ ዴ ሪቪዬር ለውጭ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት፣ ምክር ቤቱ ሦስቱን አገሮች ወደ ስምምነት ሊያደርስ ወደሚችል ድርድር እንዲመለሱ ከማድረግ ውጪ የጎላ ሚና አይኖረውም፡፡

ምክር ቤቱ ግድቡን በተመለከተ ወይይት ሊያደርግ እንደሚችል ያስታወቁት ሰብሳቢው፣ ሦስቱን አገሮች በመጥራት ሥጋታቸውን እንዲገልጹና ከስምምነት ሊያደርሳቸው ወደሚችለው ድርድር እንዲመለሱ ከማበረታታት ውጪ ሊያደርግ የሚችለው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ምክር ቤቱ ከዚያ የበለጠ ነገር ማድረግ ይችላል ብዬ አላስብም፤›› ሲሉም አስተያየታቸውን አጠናክረዋል፡፡

ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን በተደጋጋሚ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት በመውሰድ፣ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ምክር ቤቱ በግድቡ ላይ ጣልቃ እንዲገባ ሱዳን፣ ግብፅና የዓረብ ሊግ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ኢትዮጵያ ግን፣ ‹‹የአፍሪካውን ችግር በአፍሪካውያን መፈታት አለበት›› በሚለው መርህ ፅኑ አቋም ሲኖራት፣ በቅርቡም ለፀጥታው ምክር ቤት በላከችው ደብዳቤ ይህንኑ ማሳወቋ ይታወሳል። FacebookTwitterTelegramGmail