July 17, 2021 

ኸርማን ኮህን ከህወሓት ወዳጆች የመጀመሪያው ሰው ነው። አሜሪካ ለሕወሓት ስልጣን ባርካ ስትሰጠው ኮህን ዋና ካሕን ነበር።

ይህ ሰው ባሰፈረው የትዊተር መልክት ሕወሓት ስሙን መቀየሩን ጠቁሟል። የትግራይ አማፂ እንጂ የትግራይ መንግስት የሚባል ነገር እንደሌለም በይፋ ፅፏል። የቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣንና ዲፕሎማት የነበረው ኮህን በዚህ ብቻ አላበቃም በረጅም ግዜ ወዳጅነቱ የሚያውቀውን እና የሚከራከርለት የጡት ልጁን ህወሓትን አምባገነንና በሙስና የተዘፈቀ ዘራፊ ድርጅት እንደሆነ አስረግጦ በትግራይ አማፅያን ላይ የኢትዮጵያ ክልሎች ለመንግስት ድጋፍ የሚያደርጉ ወታደሮች እየላኩ መሆኑ ምንም አያስደንቅም ሲል ትዊት አድርጓል።


Herman J. Cohen@CohenOnAfrica
It is not surprising that Ethiopian regions are sending troops to support the government against the Tigray rebels. 

These very rebels, formerly known as TPLF, controlled all of #Ethiopia from 1991 to 2018 as a corrupt authoritarian regime.

2:24 PM · Jul 16, 2021·Twitter for iPhone

ሻእቢያንና ሕወሓትን ከደርግ ያደራደረው ኸርማን ኮህን በሕወሓት ላይ ይህን መሰል የተቃውሞ ፅሁፍ ሲፅፍ የመጀመሪያው ቢሆንም ህወሓትን አማፂ ያለው ሲሆን የአሜሪካ ባለስልጣናትን የዲፕሎማሲ መለኪያ አንዱ የፖለቲካ ሰው መሆኑ ሲታወቅ በስቴት ዲፓርትመት ውስጥ ለረዥም ጊዜ ከፍተኛ ባለስልጣን ሆኖ ሰርቷል።

May be a Twitter screenshot of text that says 'Herman J. Cohen @CohenOnAfrica It is not surprising that Ethiopian regions are sending troops to support the government against the Tigray rebels. These very rebels, formerly known as TPLF, controlled all of #Ethiopia from 1991 to 2018 as a corrupt authoritarian regime. Twitter for iPhone'