የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሥራ ምደባ ሰጡ። የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ለአሚኮ እንዳሳወቀው ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበዋል። ሌሎች ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማትን እንዲመሩ በርእሰ መሥተዳድሩ ምደባ ተሰጥቷል።
በዚህም መሰረት፦
1ኛ. ጀኔራል ተፈራ ማሞ የልዩ ሃይል አዛዥ፣
2ኛ. ጀኔራል መሰለ በለጠ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣
3ኛ.ኮሚ/ ቢሰጥ ጌታሁን ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽን፣
4ኛ. ኮሚ/ አርአያ ካሴ ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣
5ኛ. ጀኔራል ማሞ ግርማይ ም/ አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣
6ኛ.ጀኔራል ዘዉዱ እሸቴ ም/አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣
7ኛ. ጀኔራል አበራ ተ/ዮሃንስ ም/አዛዥ ለአስተዳደር፣
8ኛ. ረ/ ኮሚሽነር መለሰ ደገፋዉ ም/ አዛዥ ለአስተዳደር፣
9ኛ. ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ልዩ ረዳት፣ ሆነው ተመድበዋል።–

