

ByAdmin
August 7, 2021
የኮቪድ 19 መከላከያ ጆንሰን ኤንድ ጆንስ በደቡብ አፍሪካ ዜጎችን ከከባድ ህመም እና ሞት እየታደገ እንደሚገኝ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፤
በግንቦት ወር በተጠናቀቀዉ የምርምር ጥናት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የጤና እንክብካቤ ሰራተኞች ላይ የተሞከረ ሲሆን ይህ ክትባት ከ477 ሺ በላይ ለሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱ መሰጠቱን የምርምር ቡድኑ መሪ ግሌንዳ ግሬይ ተናግረዋል፡፡
ግሬ እንዳሉት በአንድ ጊዜ በተወሰደ ምልከታ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ቤታ የኮሮና ቫይረስ ተለዋዋጭ በሚሆንበት ጊዜ 67 በመቶ ዉጤት ታይቶበታል፡፡
በዴልታ ጊዜ ደግሞ 71 በመቶ ገደማ ዉጤት ታይቷል ነው የተባለው፡፡ በቫይረሱ የመያዝ ዕድልን ከ92- 96 በመቶ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይከላከላል ብለዋል፡፡
ሲጂቲኔ አፍሪካ
ቀን 01/12/2013