2 ህዳር 2021, 07:58 EAT

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ባሉት 19 ወራት በዓለም ዙሪያ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው መረጋገጡን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።
የኮሮና ቫይረስን የመከካከያ ክትባቶች የሞት ቁጥርን እንዲቀንስ እያገዘ መሆኑም የተነገረ ሲሆን አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ግን ትክክለኛው የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊልቅ እንደሚችል ይናገራሉ።
በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች በቫይረሱ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎሽ ከወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እያሻቀበ ነው።
በቫይረሱ ከአምስት በዓለም ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲያልፉ ወደ 250 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተነግሯል።
- የትግራይ ጦርነት እና ለተደራራቢ ችግር የተጋለጡት ኤርትራውያን ስደተኞች
- የዓለም መንግሥታት የደን ምንጣሮን ለማስቀረት ተስማሙ
- ናይጄሪያ ውስጥ 22 ፎቅ ያለው ሕንፃ ተደርምሶ ሰዎች ሞቱ
የዓለም ጤና ድርጅት በወረርሽኙ ምክንያት በሀገራት እየተገለጸ ያለው ቁጥር ትክክለኛ አይደለም ብሎ የሚያምን ሲሆን በዓለም ዙሪያ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የተመዘገበው ቁጥር ከእውነታው ጋር ከሁለት እስከ ሶስት እጥፍ ሊበልጥ እንደሚችል አስታውቋል።
በአሜሪካ በቫይረሱ ከ 745 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሞቱ የተመዘገበ ሲሆን ይህም በዓለም ላይ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ የሞት ቁጥር የተመዘገበባት ሀገር አድርጓታል።
ብራዚል 607 ሺህ እንዲሁም ህንድ 458 ሺህ በኮሮና ቫይረስ የተከሰተ ሞትን የመዘገቡ ሲሆን አሜሪካን በመከተል በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር የያዙ ናቸው።
ሆኖም የጤና ባለሙያዎች በቤት ውስጥ እና በገጠራማ አከባቢዎች በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎችን ለመመዝገብ ያለው ዕድል ጠባብ በመሆኑ እነዚህ ቁጥሮች ትክክለኛውን የሞት ምጣኔ አያንጸባርቅም ብለው ያምናሉ።
ካለፉት ሁለቱ ወራት አንጻር የሞት ምጣኔ በመጨረሻው ወር አንድ ሚሊዮን ለማድረስ ረጅም ጊዜ ወስዷል።
ከአራት ሚሊዮን የተመዘገበ ሞት አምስት ሚሊዮን ለመድረስ ከ110 ቀናት በላይ የፈጀ ሲሆን ከሶስት ሚሊዮን ወደ አራት ሚሊዮን ለማደግ ግን ከ90 ቀናት በታች ብቻ ነው የፈጀው።
ክትባቶች የሞት መጠንን ለመቀነስ የረዱ ቢሆንም፣ የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ሳምንት ወረርሽኙ “አበቃ ለመባል ብዙ ይቀራል” ሲል አስጠንቅቋል።