ከ 2 ሰአት በፊት

ኮሮናቫይረስ

በደቡብ አፍሪካ አገራት የታየው አዲሱ የኮሮናቫይረስ አይነት ተጨማሪ ስጋትን ፈጥሯል።

ይህ አዲስ ዝርያው እስካሁን ከታዩ የኮሮናቫይረስ አይነቶች እጅግ የተለየው ነው ተብሏል።

በበርካታ ብዙ የዘረመል ለውጥ ውስጥ በማለፉ በአንድ ሳይንቲስት “አሰቃቂ” ተብሎ ሲገለጽ ሌላው ደግሞ እስካሁን ከታዩት የከፋ ዝርያ ነው ብለዋል።

ጊዜው ገና ቢሆንም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ በአንድ ግዛት ውስጥ ይገኛሉ። የበለጠ ሊስፋፋ እንደሚችል ግን ፍንጮች አሉ።

አዲሱ ዝርያ በምን ያህል በፍጥነት እንደሚሰራጭ፣ በክትባቶችን የማሸነፍ ችሎታው እና ሊደረግ በሚገባው ጉዳይ ዙሪያ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ።

ብዙ መላምቶች ቢኖሩም በጣም ጥቂት መልሶች ብቻ ናቸው ያሉት።

ስለ አዲሱ ዝርያ ምን እናውቃለን?

ዝርያው B.1.1.529 ይባላል። አልፋ እና ዴልታ እንደሚባሉት የግሪክ ኮድ ስም በዓለም ጤና ድርጅት ሊሰጠው ይችላል።

በብዙ የዘረ መል ለውጥ ውስጥም አልፏል።

የደቡብ አፍሪካው ሴንተር ፎር ኤፒዴሚክ ሪስፖንስ ኤንድ ኢኖቬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ዴ ኦሊቬራ ስለዚህ አዲስ ዝርያ ሲናገሩ፤ “ያልተለመደ የዘረ መል ለውጥ ያለው” ሲሆን ከተሰራጩት ሌሎች ዝርያዎችም “በጣም የተለየ ነው” ብለዋል።

“ይህ ዝርያ አስገርሞናል። ለውጡ በከፍተኛ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን ከምንጠብቀው ብዙ ለውጥ አለው” ብለዋል።

ፕሮፌሰር ዴ ኦሊቬራ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በአጠቃላይ 50 የዘረ መል ለውጦች አሉ።

የብዙዎቹ ክትባቶች ዒላማ ከሆነው ከስፔክ ፕሮቲን ከ30 በላይ ለውጥ ታይቷል። ይህም ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ሴሎች መግቢያ በር ለመክፈት የሚጠቀምበት ቁልፍ ነው።

ቫይረሱ ከሰውነታችን ሴሎች ጋር የመጀመሪያ ግንኙነት ሲያደርግ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ዴልታ ዝርያ ሁለት ሲሆን አዲሱ ዝርያ ደግሞ 10 ለውጥ አለው።

ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም።

አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያ ቫይረስ በእጅጉ የተለየ ነው።

ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያክል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ።

አንዳንዶቹ ለውጦች በሌሎች ዝርያዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ታይተዋል። ይህም በዚህ ለውጥ ውስጥ ያለውን ሚና የተወሰነ ግንዛቤ ይሰጣል። ለምሳሌ N501Y የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ቀላል የሚያደርግ ይመስላል።

የሰውነት የበሽታ መከላከያ ቫይረሱን እንዳያውቁ የሚያከብዱበት እና ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ሌሎች ዝርያዎች አሉ።

በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ሌሰልስ “ይህ ቫይረስ የመተላለፊያ ችሎታውን ከፍ አድርጎ ከሰው ወደ ሰው ከመተላለፍ ባለፈ የበሽታ ተከላካይ ክፍሎችን ማካለል ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮብናል” ብለዋል።

በወረቀት ላይ አስፈሪ የሚመስሉ ነገር ግን ጉዳት ያላደረሱ ብዙ የዝርያ ምሳሌዎች ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ የቤታ ዝርያ የበሽታ መከላከል ስርዓትን ሊያመልጥ ይችላል በሚል በሰዎች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ ነበር።

ኋላ ላይ ግን ዓለምን የተቆጣጠረውና በፍጥነት የተስፋፋው ዴልታ ዝርያ ነበር።

በቤተ ሙከራ ውስጥ ያሉ ሳይንሳዊ ጥናቶች የበለጠ ግልጽ ምስል ይሰጣሉ። ዋናው ግን በገሃዱ ዓለም ቫይረሱን በመከታተል የሚሰጡት መልሶች ናቸው።

መደምደሚያ ላይ ለመድረስ ገና ቢሆንም ስጋት የሚፈጥሩ ምልክቶች አሉ።

በደቡብ አፍሪካዋ ጋውቴንግ ግዛት 77 ሙሉ በሙሉ የተረጋገጡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሉ። በቦትስዋና አራት እና አንድ ደግሞ በሆንግ ኮንግ (ከደቡብ አፍሪካ ጉዞ ጋር በቀጥታ የተገናኘ) በቫይረሱ የተያዙ ተገኝተዋል።

ዝርያው በስፋት ስለመሰራጨቱም ፍንጭ አለ።

ይህ ዝርያ በመደበኛ ምርመራ ወቅት አሻሚ ውጤቶችን የሚሰጥ ይመስላል። በዚህም ሙሉ የዘረመል ትንተና ሳያደርጉ ዝርያውን ለመከታተል ሊያገለግሉ ይችላሉ።

በጋውቴንግ ውስጥ የተገኙ 90 በመቶ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቀድሞውኑም በዚህ ዝርያ ሊሆኑ ይችላሉ።

በዚህም ዝርያው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ “በአብዛኛዎቹ ግዛቶች ውስጥ ሊኖር ይችላል” ይላል።

ይህ ግን ከዴልታ በበለጠ በፍጥነት መስፋፋቱን፣ ከክትባት የሚመጣውን የበሽታ መከላከያ ማምለጡ ምን ያህል እንደሆነ አይነግረንም።

ምንም እንኳን በደቡብ አፍሪካ ብዙ ሰዎች ኮቪድ ቢገኝባቸውም 24 በመቶ ዜጎቿን ብቻ ነው የከተበችው።

ዝርያው ከደቡብ አፍሪካ በላይ በርካታ ክትባት በሰጡ ሃገራት ምን ያህል እንደሚሰራጭ አይታወቅም።