ስለ ደሴ…

ከአዲስ አበባ 401 ኪ/ሜ ከክልሉ ከተማ ባሕር ዳር 481 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው የደሴ ከተማ ካላት ወታደራዊ ጠቀሜታ በተጨማሪ ተስማሚ የአየር ፀባይ፣ ማራኪ የተፈጥሮ ውበትና ልምላሜ የታደለች ሆና በመገኘቷ ለረጅም ዓመታት ለወሎ ባላባቶች መቀመጫ በመሆን ስታገለግል የቆየች ታሪካዊ ከተማ ናት፡፡

አሁን ያላትን ቅርጽ ለመያዝ በከተማነት የተቆረቆረችው ደግሞ በ1885ዓ.ም በወሎው ባላባት ሙሃመድ አሊ(በኋላ ንጉሥ ሚካኤል) ነው፡፡

ደሴ ከባህር ወለል በላይ በአማካኝ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ስትሆን በስተምዕራብ ዙሪያዋን ማራኪው የጦሳ ተራራ ይከባታል፡፡

የጦሳ ተራራ የደሴ ከተማን ከቅርብ ርቀት ወደታች ለመመልከት እጅግ ተስማሚ ቦታ ነው፡፡

ደሴ አሁን የምትጠራበትን ስም ከመያዟ በፊት ላኮመልዛ ትባል ነበር፡፡

ቀደም ባሉ ዓመታት ከተማዋ የወሎ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ የነበረች ሲሆን አሁን ደግሞ የደቡብ ወሎ ዞን እና የደሴ ሜትሮፖሊታንት አስተዳደር መቀመጫ ናት፡፡

ደሴ የሚገኙ የተወሰኑ የመስህብ ቦታዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል፤ ጹሑፉን አንብበው ለዋዳጅዎ ያጋሩ፡፡

1/ የንጉሥ ሚካኤል ቤተ መንግስትደሴ ከተማ ውስጥ በአንድ ወቅት አጼ ቴዎድሮስ ተንቀሳቃሽ ድንኳናቸውን ተክለውበት እንደነበር በሚነገርለት ጀሚ ተብሎ በሚጠራው ኮረብታ አናት ላይ የሚገኝ 2130 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የንጉሥ ሚካኤል ቤተ መንግስት ይገኛል፡፡

ቤተ መንግስቱ ግዙፉን የአይጠየፍ አዳራሽ፣ የልጅ እያሱ እልፍኝ፣ የራስ እምሩ ችሎት ቤትና የንጉሥ ሚካኤል የፀሎት ቤት አካቶ ይይዛል፡፡

ከእነዚህ ቅርሶች መካከል የከተማዋን ዘመናዊ እድሜ የሚጋራው የአይጠየፍ አዳራሽ በ1907ዓ.ም በንጉሥ ሚካኤል መገንባቱ ይነገራል፡፡

የአይጠየፍ አዳራሽ ህንፃው የውስጥ ጣሪያ ጥርብ ጥዶች ጥልፍልፍ ተደርገው ተገጥመውለታል፡፡

እያንዳንዳቸው አንድ ሜትር ያህል ውፍረት ያላቸው 2ዐ የጥድ ምሰሶዎች በአዳራሹ ውስጥ ተተክለው ጣራውን እንዲሸከሙት ተደርገዋል፡፡

አዳራሹ ለስብሰባና ለግብር ማብያ ታስቦ የተሰራ ነበር፡፡በግብር ወቅት ደግሞ ድሃው ከሃብታሙ ጋር እኩል ይሳተፍ ስለነበር አይጠየፍ የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ከረጅም ጊዜ ዕደሜ ቆይታው ባሻገር የሀገራችንን የሥነ ህንፃ ሥራና ጥበብ ዕድገት ጠቋሚ የሆነው አይጠየፍ አዳራሽ የአገራችን ባለሙያዎች በግብረ ህንፃ የዳበረ ዕውቀት የነበራቸው መሆኑን በጉልህ የሚያሳይ ቋሚ ቅርስ ነው፡፡

2/ ደሴ ሙዚየም እና የመርሆ ግቢሙዚየሙ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ መውጫ በስተቀኝ የሚገኘውና በተለምዶ ዲቪዥን በመባል የሚጠራው ኮረብታ “ባሊያን” በተሰኙ የህንድ ጎሳዎች 1909ዓ.ም እንደተሠራ የሚነገርለት የደጅ አዝማች ዮሴፍ ብሩ መኖሪያ የነበረው ህንፃ ውስጥ ተደራጅቶ ለጎብኝዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በክልላችን በዞን ደረጃ ከሚገኙት ሙዚየሞች በይዘቱም ሆነ በአደረጃጀቱ ቀዳሚውን ቦታ የሚይዘው ይህ ሙዚየም ነው፡፡

በሙዚየሙ የተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች በአካል የሚታዩበት ሲሆን በኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙት ብርቅዬ የዱር እንስሳት መካከል የሰሜን ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮ እንዲሁም የተለያዩ እንስሳት የውስጥ አካላቸው ወጥቶ ውጫዊ የተፈጥሮ ቅርፃቸው ሳይዛባ “በታክሲደርሚ” ጥበብ ደርቀው ለእይታ የቀረቡት እና በርካታ ገላጭ ፎቶ ግራፎች የሚገኙበት ሙዚየም ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ለአብነትም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የስልክ መነጋገሪያ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ የነገሥታት ኮረቻ፣ የዳግማዊ ምኒሊክ ጫማ፣ ጥንታዊ የመገልገኛ እቃዎች ወዘተ ይዟል፡፡

የመርሆ ግቢም በሙዚየምነት እያገለገለ የሚገኝ ሲሆን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጅ የአስፋው ወሰን ኃይለ ሥላሴ መኖሪያ የነበረ ጥንታዊ ቅርስ ነው፡፡

ህንፃው በዘመኑ የነበረውን የኪነ ህንፃ ለመረዳት እና የደሴ ከተማን ታሪካዊ ፋይዳ ለመገመት ጠቃሚ እንደሆነ ይታመናል፡፡

3/ ወሎ ባህል አምባፋሽስት ኢጣሊያ በኢትዮጵያ የአምስት አመት /1928-1933 ዓ.ም የወረራ ቆይታው የሰራው አዳራሽ ነው፡፡

አዳራሹ የተሰራበት ቁሳቁስ ከኢጣሊያ በተለይም ከሚላኖ ከተማ እንደመጣ ይነገራል፡፡

የወሎ ባህል አምባ የደሴን ከተማ የቅርብ ጊዜ ታሪክ በገሃድ የሚያሳይ ሲሆን በዚህ ታላቅ የሲኒማ አዳራሽም አዝናኝ ሲኒማዎች፣ የቲያትርና ሙዚቃ ትርኢቶች ይቀርቡበታል፡፡አዳራሹ በአንድ ጊዜ እስከ 1500 ታዳሚዎች ድረስ የማስተናገድ አቅም አለው፡፡

ደሴ ከላይ ከተጠቀሱት የመስህብ ሀብቶቿ በተጨማሪ የበርካታ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የመስህብ ሀብቶች ባለቤት ናት፡፡

የጦሳ ተራራ፣ ታሪካዊ መስጅድ እና ቤተ ክርስቲያኖች፣ ባህላዊ ሙዚቃዎች ወዘተ የደሴ ግርማ ሞገሶቿ ናቸው፡፡

ከተማዋ በወሎ ውስጥ በሚገኙ በሌሎች መስህብ ሀብቶችንም የተከበበች ናት፡፡

ከደሴ በቅርብ ርቀት ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም፣ የገታ ሰይድ ቡሽራ መስጅድ፣ ቦሩ ሜዳ፣ ተድባበ ማርያም፣ ሀይቅ እስጢፋኖስ፣ መቅደላ አንባ፣ ይስማ ንጉሥ፣ ሀርቡ ፍል ውሃ፣ ተንታ ሚካኤል፣ የቦረና ሳይንት ብሔራዊ ፖርክ፣ አርዲቦ ሐይቅ፣ ጐልቦ ሐይቅ፣ ማይባር ሐይቅ፣ ጀማ ንጉሥ እና ሌሎችም ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የመስህብ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡

ደሴን ሲጎበኙ በቅርብ ርቀት የመረጡትን መዳረሻ በአነስተኛ ወጪ የመጎብኘት እድል አለዎት፡፡

የደጋግ ህዝብ መኖሪያ የሆነችውን ታሪካዊቷን የደሴ ከተማ ይጎብኙ!፡፡

ደሴን ይወቁ፤ ደሴን ያስተዋውቁ!፡፡

አማራ ክልልን ይጎብኙ፡፡

ምንጭ – Dessie Communication

43Berhanu Abate, Dessalegn Muche and 41 others10 Comments21 SharesLikeCommentShare

10 Comments

Most relevantActiveWrite a comment…

View 5 more commentsWehib Omer0m10pa3a4l2ns4hu6ra9tdf  · 0:05 / 58:18

43Berhanu Abate, Dessalegn Muche and 41 others10 Comments21 SharesLikeCommentShare

10 Comments

Most relevantActiveWrite a comment…

View 5 more commentsWehib Omer0m10pa3a4l2ns4hu6ra9tdf  · 0:05 / 58:18