11 ታህሳስ 2021, 08:04 EAT

የዓለም ጤና ድርጅት ኦሚክሮን ብሎ የሰየመው አዲሱ የኮሮረናቫይረስ ዝርያ እንደ አዲስ ዓለምን ማስጨነቅ ከጀመረ ሰነባብቷል። በርካታ አገራትም ከወዲሁ ስርጭቱን በመስጋት በራቸውን እየዘጉ ይገኛሉ።
ኦሚክሮን እራሱን የሚለውጥበትና የሚስፋፋበትን መንገድ የተመለከቱ ተመራማሪዎችም በጣም አስፈሪ እንደሆነ እየገለጹ ነው።
ይህ የቫይረስ ዝርያ በብዙ የለውጥ ሂደት ውስጥ ያለፈ ሲሆን ማስረጃዎች ቀደም ሲል ተይዘው የነበሩ ሰዎች በቫይረሱ የመያዝ ምጥኔን እንደሚጨምር ይጠቁማሉ ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
አዲሱ ኦሚክሮን እስካሁን ከ30 በላይ አገራት ውስጥ የተገኘ ሲሆን ሰዎች በክትባትም ሆነ የኮሮረናቫይረስ ሲይዛቸው የሚያዳብሩትን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ የሚችል ነው።
ነገር ግን ከዚህ በፊት ከነበሩት የኮሮረናቫይረስ አይነቶች አንጻር እስካሁን ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ ነው ያሳየው። በዚህም ምክንያት ስለ ቫይረሱ፣ ስለ ስርጭቱ እና ስለሚያደርሰው ጉዳት በርካታ መላ ምቶች እየተሰነዘሩ ነው።
እስካሁን እኛ የምናውቀውን እናካፍላችሁ
ኦሚክሮን እስከዛሬ ከታዩት የኮሮናቫይረስ አይነቶች በሙሉ በፍጥነት እራሱን ማሻሻሻልና መቀየር የቻለው የቫይረስ አይነት ነው።
በበርካታ የዘረመል ለውጥ ውስጥ በማለፉ በአንድ ሳይንቲስት “አሰቃቂ” ተብሎ ሲገለጽ ሌላው ደግሞ እስካሁን ከታዩት “የከፋ” ዝርያ ነው ብለዋል።
አዲሱ ዝርያ በምን ያህል በፍጥነት እንደሚሰራጭ እና ክትባቶችን በመቋቋም አቅሙ ዙሪያ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ። ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።
- የአፍሪካ ሕብረት በኦሚክሮን ምክንያት በአባል አገራቱ ላይ የጉዞ እቀባ መደረጉን አወገዘ
- የዓለም ጤና ድርጅት በአዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት አገራት እንዳይደናገጡ አሳሳበ
- ‘ኦሚክሮን’ ተብሎ የተሰየመው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ‘አሳሳቢ’ ነው ተባለ
አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያው ቫይረስ በእጅጉ የተለየ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ።
በደቡብ አሜሪካ የሚገኘው የተላላፊ በሽታዎች መካለከያና ምላሽ ሰጪ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ቱሊዮ ዴ ኦሊቬራ እንደሚሉት፣ ኦሚክሮን ከዚህ በፊት ከታዩት ቫይረሶች በሙሉ በተለየ መልኩ እራሱን መቀያያርና እንደ ሁኔታዎች መለዋወጥ የሚችል ነው።
“ይህ ዝርያ አስገርሞናል። ለውጡ በከፍተኛ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን ከምንጠብቀው ብዙ ለውጥ አለው” ብለዋል።
ፕሮፌሰር ዴ ኦሊቬራ አክለውም አዲሱ ቫይረስ በአጠቃላይ 50 የዘረ መል ለውጦች አሉት።
የብዙዎቹ ክትባቶች ዒላማ ከሆነው ከስፔክ ፕሮቲን ከ30 በላይ ለውጥ ታይቷል። ይህም ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ህዋሳት መግቢያ በር ለመክፈት የሚጠቀምበት ቁልፍ ነው።
ቫይረሱ ከሰውነታችን ህዋሳት ጋር የመጀመሪያ ግንኙነት ሲያደርግ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ዴልታ ዝርያ ሁለት ሲሆን አዲሱ ዝርያ ደግሞ 10 እጥፍ ለውጥ አለው።
ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ የዝርያ ለውጥ ቫይረሱን ማሸነፍ ካልቻለ አንድ ታካሚ የመጣ ሳይሆን አይቀርም። አሳሳቢው ነገር ይህ ቫይረስ በቻይና ዉሃን ከተፈጠረው የመጀመሪያ ቫይረስ በእጅጉ የተለየ መሆኑ ነው።
ይህም ማለት የመጀመሪያውን ቫይረስ ከግምት በማስገባት የተመረቱት ክትባቶች ለዚህ አዲስ ዝርያ ያን ያህል ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ።
አንዳንዶቹ ለውጦች በሌሎች ዝርያዎች ውስጥ ከዚህ ቀደም ታይተዋል። ይህም በዚህ ለውጥ ውስጥ ያለውን ሚና የተወሰነ ግንዛቤ ይሰጣል። ለምሳሌ ኤን501ዋይ የኮሮናቫይረስ መስፋፋትን ቀላል የሚያደርግ ይመስላል።
የሰውነት የበሽታ መከላከያ ቫይረሱን እንዳያውቁ የሚያከብዱበት እና ክትባቶች ውጤታማ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ሌሎች ዝርያዎች አሉ።
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተመራማሪዎች ቀደም ብለው እንደገለጹት ኦሚክሮን የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም በቀላሉ ማለፍ ይችላል።
በደቡብ አፍሪካ የኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ሌሰልስ “ይህ ቫይረስ የመተላለፍ ችሎታውን ከፍ አድርጎ ከሰው ወደ ሰው ከመተላለፍ ባለፈ የበሽታ ተከላካይ ክፍሎችን ማካለል ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮብናል” ብለዋል።
በወረቀት ላይ አስፈሪ የሚመስሉ ነገር ግን ጉዳት ያላደረሱ ብዙ የዝርያ ምሳሌዎች ነበሩ። በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ የቤታ ዝርያ የበሽታ መከላከል ሥርዓትን ሊያመልጥ ይችላል በሚል በሰዎች ዘንድ ስጋት ፈጥሮ ነበር።
በደቡብ አፍሪካ ኦሚክሮን በእጅጉ እየተስፋፋ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ባሳለፍነው ወር አጋማሽ አካባቢ በየቀኑ እስከ 250 የሚደርሱ አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ እየተያዙ ነበር። ሌሎች የኮሮረናቫይረስ አይነቶች እያስቸገሯት በምትገኘው ደቡብ አፍሪካ አሁን ላይ በኦሚክሮን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በቀን እስከ 8 ሺህ ይደርሳል።
አሁን ላይ ሰዎች ስለአዲሱ ቫይረሰ አይነት ያላቸው እውቀት ውስን ነው። በዚህም ምክንያት ተመራማሪዎችም ሆነ ሌሎች ሰዎች አዲሱን ቫይረስ በንቃት ሊከታተሉትና አካሄዱን በደንብ ሊያውቁት ይገባል። በተለይ የዘርፉ ተመራማሪዎች በዚህ ዙሪያ በርካታ ሥራዎች ይጠብቋቸዋል።
ከኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የተማርነው አንድ ነገር ቢኖር፤ ለጥያቄዎቻችን በሙሉ መልስ እስከምናገኝ ድረስ ዝም ብለን መቀመጥና መጠበቅ እንደሌለብን ነው።