
፠ የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የሕይወታቸው መጨረሻ ሰዓት እና የመቅደላ ዝርፊያ፤በስፍራው በአካል በመገኘት የአሜሪካን ጋዜጠኛ የዘገበው ትርጉም፤ በቆንጂት መሸሻ
ሽጉጡ ሰደፍ ላይ በብር የተለበጠ ጽሑፍ እንዲህ ይላል:-
ይህ አጭር ጽሑፍም የተጻፈው የንጉሡን ሕይወት ማለፍ ተከትሎ እስታንሊ በገጽ 449-464 ያሰፈረውን ሀተታ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ነው።
በተጨማሪም በእውን ያያቸውን ከመቅደላ የተዘረፉትን ቅርሶች ገጽ 454-462 በዝርዝር ያስቀምጣል።
ሰር ናፕዬር በፈረስ ተቀምጠው ሬሳውን ለማየት መጡ፤ ተመለከቱ። ምንም ዓይነት የርህራሄ ቃል አልተናገሩም።
በጠቅላላው ከመቅደላ የተዘረፈውን ቅርስ እንደሚከተለው ይተነትናል:-
ሦስት መቶ ዓመት እድሜ ያካበተው ከንፁህ ወርቅ የተሰራ ምንአልባትም ክብደቱ ከስድስት ወይንም ሰባት ትሮይ አወንስ የማያንስ የአቡኑ አርዌ ብርት፤
.. አራት የነገሥታቱ ዘውዶች ከእነዚህም መሀል ሁለቱ በረቂቅ የፊሊግሪ ጥበብ የተሠሩ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ እና በእንግሊዝ ሙዝየም ሊቀመጡ የበቁ፤
….ቦሂሚያን ብርጭቆዎች፣ ሴቨር ቻይና፣ የእስታፈርድሻየር ሸክላ ሳህኖች፣ የሻምፔን (ፈርንሳይ) ወይን ጠጅ፤
…. የግሪክ፣ የስፔን የእየሩሳሌም ወይንጠጅ፣ በርጋንዲ፣.. የዮርዳኖስ ወንዝ ውሀ፤ .. አረቄ እና ጠጅ በገምቦ፤
…ሳጥን ሙሉ ልዩ ልዩ ዓይነት እቃዎች፤ እንዲሁም ጽጌ ረዳ፣ ነጭ: እና ሌሎች ቀለሞች የሆኑ የሀር ድንኳኖች፤
….የፐርዢያ የኡሻክ ብሮሳ ኪድሚንስትር የሊዮንስ አበባ ምንጣፎች፤
… የጎፈር ካባዎች፤ የአንበሳ ጋማ ለምድ፤ የነብርና የቀበሮ ቆዳዎች፤
…ግሩም ሆነው የተሰሩ በወርቅ በብር ያሸበረቁ ኮርቻዎች፤
…ጎንደርና ጎጃም ያፈራቸው የተዋቡ የክብር ጃንጥላዎች፤
… ሰይፎች፤ ሾተሎች፤ ጎራዴዎች እንዲሁም በሁለት በኩል ስለት ያላቸው የስኮትላንድ ጎራዴዎች፤ ቢላዎች፣ አያሌ የእግርና የእጅ ብረቶች፤
… ሚስተር ሆልምስ፣ የእንግሊዝ ሚዩዚየም ወኪል፤
..ኮለኔል ፍሬዠር፣ የኃብታም ጦር መሪዎች ክበብ ሀብት ገዢና ሰብሳቢ፤ እንዲሁም ለጨረታ ተሰናድተው የመጡ ኃብታም ግለ ሰቦች ነበሩ።
በአስር ዶላር የጀመረው ጨረታ ከሞቀ ውድድር በኋላ ኮሌኔል ፍሬዠር በ200 ዶላር ገዛው።”የሀራጅ ሽያጩ በሁለት ቀናት ተጠናቀቀ::
1. የጦርነቱ ዘመን በእስታንሊ ጽሁፍ እንደሰፈረው በአሮፓውያን አቆጣጣር ነው። ለአንባቢ እንዲመች በማለት በቅንፍ የተቀመጡ ተጨማሪ ማብራሪያዎችም ይገኙበታል።