ብልፅግና ፓርቲ ባለፈው ካወጣው መግለጫ ተቃራኒ የሆነ መግለጫ ዛሬ አውጥቷል ። ባለፈው ሳምንት ህገመንግስቱ ያማልዳል፤ በሕገመንግስቱና በፌዴራሊዝም አልደራደርም ያለው ብልጽግና ዛሬ በህገመንግስቱና በፌዴራሊዝም እደራደራለሁ ብሏል። ትላትን ያለውን ዘሬ የማይደግመው ነገ ሌላ የሚለው ብልጽግ ና ነገ ደግሞ ምን አይነት መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሃገራዊ ምክክሩም ይሁን ብሄራዊ የመግባባት ውይይቱ ተጠልፏል ግልጽነት ይጎለዋል አካታችና ገለልተኛ አይደለም የሚሉ ፖለቲከኞች በርካቶች ናቸው።
መንግሥት በቅርቡ ሊያካሂደው ያሰበው ብሄራዊ ሁሉን ዓቀፍ ምክክር በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች ጋር ድርድር ማድረግ ማለት እንዳልሆነ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው ማብራሪያ ገልጧል። ብልጽግና ጨምሮም፣ የብሄራዊ ውይይቱ ዓላማ ሕገመንግሥት እና ሰንደቅ ዓላማን ጨምሮ በቁልፍ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ በመድረስ እና በሕዝቡ እና በፖለቲካ ልሂቃን መካከል መግባባትን በማምጣት፣ ሰላም እና ብልጽግና የሰፈነባት ሀገር መፍጠር እንደሆነ አብራርቷል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በበኩሉ፣ የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ምርጫ ሂደት ለጊዜው ቆሞ፣ በብሄራዊ ውይይቱ መሠረታዊ ነጥቦች ላይ በቅድሚያ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ከቀናት በፊት መጠየቁ ይታወሳል። ሕወሃት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በብሄራዊ ውይይቱ ይሳተፉ አይሳተፉ ግን መንግሥት እስካሁን ቁርጥ ያለ አቋሙን አልገለጸም።
ያለፈው መግለጫና የዛሬውን መግለጫ ከታች ያገኙታል።
ከሳምንት በፊት

ዛሬ
