February 17, 2022 – Konjit Sitotaw 

ድንበሩ ከወር በፊት ተከፍቷል የሚል ዘገባ መለቀቁ ቢታወስም ዲና ሙፊት ዛሬ የተናገሩት ግራ የሚያጋባ ነው።የመተማ ጋላባት መስመር ለዜጎች ክፍት እንዲደረግ ኢትዮጵያ ሱዳንን መጠየቋን ነው ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ያስታወቁት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አንዳሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ በአማራ እና አፋር ክልል ምልክታ አድርገዋል፤ በሶማሌ ክልልም የተከሰተውን ድርቅ ተመልክተዋል፤ ድርጅቱ ችግሩን ለመቅርፍ በሚደረገው ጥረት አጋዥ መሆኑን ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቀዋል፡፡

አምባሳደር ዲና በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከሱዳን መንግሥት ጋር ውይይት ማድረጋቸውንም ገልጸዋል። በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የድንበር እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን በተመለከተ ምክክር አድርገዋል ብለዋል።

የመተማ ጋላባት መስመር ለዜጎች ክፍት እንዲደረግ ኢትዮጵያ ሱዳንን መጠየቋን ነው ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ያስታወቁት።

አሜሪካ ኤች አር 6600 በሚል በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል የሚደረገው እንቅስቃሴ ልክ እንዳልሆነ ለማስረዳት እና ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ጉዳዮች እየተሻሻሉ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሃሳባቸውን እያቀረቡ እና ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ከወር በፊት የነበረው ዘገባ  https://www.bbc.com/amharic/news-59868773

የመተማ ከተማ