
አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ህብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እንቅስቃሴ ለመጀመር መታሰቡን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ።
አምባሳደር ዲና በዛሬው ዕለት ሳምንታዊ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሥራ ማብራሪያ በተመለከተ የተለያዩ ነጥቦችን አንስተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱ ለሰላም ምክክሩ ገንቢ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።
ህወሃት ጸብ በመጫር የእርዳታ ሥራውን እያስተጓጎለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከተመድ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው የገለጹ ሲሆን፣ በተግባር እያሳየ መሆኑን የተመድ ምክትል ጸሀፊ አሚና መሀመድ መናገራቸውንም አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ከታላቁ ህዳሴ ግድብና ከድንበር ጋር በተያያዘ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
የመተማ ገላባት መንገድ እንደቀደሙ ሁሉ ለዜጎች እንቅስቃሴ ክፍት እንዲሆን ከሱዳን መንግስት ጋር ንግግር መደረጉንም ማንሳታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል፡፡
የአማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን እንቅስቃሴ ለመጀመር መታሰቡንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ኤች አር 6600 ረቂቅ ህግ ላይ የተጠናከረ ዘመቻ እያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል።