· ሁሌ እናስታውሳቸው

ተቀብሮ እንዳይቀር

\አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ጓድ አሸናፊ ሊበን ማን ነው???

..ጓድ አሸናፊ የተወለደው በ1954 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን የአንደኛና የሁለተኛ ትምህርቱን የተማረው በዳግማዊትምህርት ቤት ነበር። በ1967 ዓ.ም.በመሠረተ ትምህርት ፕሮግራም በሐረር ክፍለሀገር ሐብሮ አውራጃ ውስጥ ዘምቶ ለጭቁኑ ሕዝብ አገልግሎቱን አበርክቷል።

ከዚያም በወቅቱ የኢሕአፓ ወጣት ክንፍ በሆነው በኢሕአወሊ ውስጥ አባል በመሆን በማደራጀትና በቅስቀሳ ተግባር ላይ ተሰማርቶ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ጓዱ በርካታ ወጣቶችንወደ ድርጅቱ የመለመለ መሆኑ በመጋለጡ በደርግ ካድሬዎች ተይዞ ለረጅም ዓመታት በእስር ቤት አሳልፏል። ከእስር ከተፈታ በኋላ በ1979 ዓ.ም ወደ ሱዳን ሊወጣ ችሏል።

በሱዳን ብዙ ውጣ ውረድ ቢደርስበትም ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ኢሕአፓን እንደገና ተቀላቅሎ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ዕምነቱን ጠብቆ ቆይቷል። የስደተኛው መብት ሲገፈፍ መብቱን ለማስመለስ የፔቲሽን ሊቀ መንበር በመሆን እንዲሁ “የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ኮሚቴ በሱዳን” የኮሚቴ አባል በመሆን ለወገኑ ታግሏል።

ለረጅም ዓመታት በሱዳን የኢሕአፓ ኮሚቴ አባል የነበረው ጓድ አሸናፊ ለሕዝብና ለሀገር ከፍተኛ ፍቅር ያለው፣ ከሰው ጋር ተግባቢና ለተቸገረ አዛኝ እና እርዳታውን ነፍጎ የማያውቅ ጓድ ነበር።

በኢሕአፓ አባልነት ለረጅም ጊዜ ሲታገል የነበረው ጓድ አሸናፊ ሊበን አመዴ በነበረበት ሕመም ሐሙስ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም በሚኖርበት በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከዚህ ዓለም በሞትተለይቷል።

ክብር የህዝብን ጥያቄ አንግቦ፤ የትግሉ ነው ህይወቴ ብሎ፤ ለኖረ ጀግና ትውልድ!!

ነፍስ ይማር!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!